በውይይት የሚያምን ዜጋ መፍጠር ያስፈልጋል!

“‘ወደ ዮኒቨርስቲው ስመጣ የኔ ብሄር ኩሩ፡፡ የኔ ሐይማኖት ብቻ ትክክለኛ’ ብዬ አስብ ስለነበር ማንንም ለማድመጥ ዝግጁ አልነበርኩም። አሁን ግን የሃሳብ፣ የሃይማኖትና የባህል ብዝሃነት ሁሉ በቀና መንፈስ ማየት ከተቻለ ሁሉም ትክክል በመሆኑ ሊከበርለት ይገባል፡፡”

ባሕርዳር፡ ግንቦት 19/2010 ዓ/ም (አብመድ) በቀና መንፈስ ላይ የተመሰረቱ የውይይትና ክርክር መድረኮች ሃገራዊ መግባባትን ለመፍጠር ሚናቸው የላቀ ነው ።

ስቴዲ ድያሎግ የተባለ ፕሮጀክት በሃገሪቱ ባሉ 5 ዮኒቨርስቲዎች ጋር የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት እየሰራ ነው ።

የተሳሳተ ነው። ደረቅ ነው። እንደዚህ አይደለም? ውይ ትውልድ ወዴት እየሄደ ነው? አልሰማሁም! እኔ ምን አገባኝ! ኤድያ !አሁን እንደዚህ ነው የሚሰራው? እቺ አገር ሰው የላትም? የሚሉ የተለመዱ አባባሎችን አሁን አሁን መስማት ብርቅነቱ አልፎበታል።

ታድያ በዳበሩ ሃሳቦች እና እውነታዎች በውይይት የሚያምን ዜጋ መፍጠር አማራጭ የለውም።

አቶ እንየው እንማው በኢትዮጵያ የሰላምና ልማት ግብረ ሰናይ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ባለፉት ሁለትና ሶስት አመታት በዮኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል ልዮነት ሲፈጥር የነበረው የብሄርና ሐይማኖት ልዮነትን ያለመቀበልና ያለማክበር ባህል እንደነበር በጥናት ተረጋግጧል ይላሉ ።

አቶ እንየው አንማው የውይይት መድረኩን ሲመሩ

ይህንን አሉታዊ እይታ ለማስቀረት በ5 የተመረጡ ዮኒቨርስቲዎች ተማሪዎች በቀና አመለካከት ስለራሳቸው የሚግባቡበት የሚከራከሩበት ክበባት ተቋቁመዋል ።

የተቀመረው ተሞክሮ የብሄር እና ሃይማኖት ግጭቶችን እንዳይባባሱ ስያደርጉ ነበር ። በቀጣይም የተማሪዎችን ተሞክሮ በመላው ሃገሪቱ ህዝቦች በቀና አመለካከት የሰላም ባህል ጎልብቶ የውይይትና ክርክር መድረኮች እንዲለመዱ እንደሚሰሩ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪና የፕሮጀክቱ ተሳታፊ

ከአፋር ክልል የመጣው የባህርዳር ዮኒቨርስቲ ተማሪ አሊ ሳሊህ ወደ ዮኒቨርስቲው ስመጣ የኔ ብሄር ኩሩ፡፡ የኔ ሐይማኖት ብቻ ትክክለኛ ብየ አስብ ስለነበር ማንንም ለማድመጥ ዝግጁ አልነበርኩም ። አሁን ግን የሃሳብ፣ የሃይማኖትና የባህል ብዝሃነት ሁሉ በቀና መንፈስ ማየት ከተቻለ ሁሉም ትክክል በመሆኑ ሊከበርለት ይገባል፡፡ የምፈልገውን ያክል እንድሰጥ የሰላም ባህል ውይይቱ ረድቶኛል ይላል ። የራስን ሃሳብ ብቻ የማይስተካከል እውነታ አድርጎ ማሰብ የብሄር እና የባህል ብዝሃነት ላላት ሃገራችን የግጭት መነሻ እየሆኑ መጥቷል።

እንደ ባህርዳር ዮኒቨርስቲ የሰላም ግንባታ የውይይት መድረኮች ቀና አመለካከት የቱ ነው? ቀና ያልሆነ ስንል ምንድነው የሚሉ የግጭት መነሻችንን በማቅረብ የመፍትሄው አካል በመሆን ለፓሊሲ አውጭዎች ግብአት እየፈጠርን ነው ያለችው ደግሞ ተማሪ ሃብታም ሞገስ ናት። የባህርዳር ዮኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኝ የዮኒቨርሲቲ ተማሪዎች በባለፋት ወቅቶች ብሄርን እና ሃይማኖትን ተገን አድርገው ከፈጠሯቸው ግጭቶች በመማር ህዝብን የሚያስተሳስሩ እና የተሳሳቱ አመለካከቶችን የሚያቃኑ ውይይቶችና ክርክሮች እንዲያደርጉ መክረዋል። በተማሪዎች የተነሱ ሃሳቦችም ለፖሊሲ አውጭዎች ግብአት እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪና የፕሮጀክቱ ተሳታፊ

ቀና ምንድን ነው? ሊደረግልን ለምንፈልገው ሁሉ ፣ሊደረግለት የሚፈልገውን ዜጋ መብት መጠበቅ።
ቀና ያለመሆንስ የራስ የሆነው ሁሉ ትኩረት ያልተሰጠው የተጎዱ ሆኖ ሌሎች ሳይረዱ ላልተፈለገ የብሄር እና ሐይማኖት ግጭት ውስጥ መግባት አይመስላችሁም? እውነትና ሃሰት ቢኖርም ባይኖርም ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም። ማለት ይህ አይደል።


በግርማ ተጫነ

አማራ ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ