የአንድ ብሄር የበላይነት በመገናኛ ብዙሃን፤ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን እንደማሳያ

(ገረሱ- ከፊንፊኔ)
የአንድ ብሄር የበላይነት አለ ወይስ የለም የሚሉ ጉንጭ አልፋ ክርክሮች አሁን ድረስ የማህበራዊ ሚዲያው ትኩስ ርዕሰ ጉዳይ ነው፡፡ ከተቋማት አኳያ “የአንድ ብሄር የበላይነት አለ” ማለት በአጭሩ ብሄርን ወይም ዘርን መሠረት ያደረገ ቅጥር፣ ዕድገት፣ ዝውውርና የሥራ ምደባ… ከማድረግ ጋር በቀጥታ ይያያዛል፡፡ ይህ ሲሆን የትምህርት ዝግጅትና የሥራ ልምድ ወይም ልዩ ሥልጠና መመዘኛዎች አስታዋሽ ያጣሉ፡፡ ሰዎች ያለአቅማቸው ሙያ በሚጠይቁ ቦታዎች ሁሉ በመመደብ የሚሠሩ ሌሎች ባለሙያዎችን ያውካሉ፣ ሞራል ይነካሉ፡፡ በተጨማሪም መንግሥታዊ ተቋማት ለግብር ከፋዩ ሕዝብ መስጠት ያለባቸውን ጥራት ያለው አግልግሎት እንዳይሰጡ አንድ ምክንያት ይሆናል፡፡ ችግሩ ምርታማነትን፣ የሥራ ተነሳሽነትን በመጉዳት በተራዘመ ጊዜ የሚታይ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ያስከትላል፡፡ የገዥውን ፓርቲን ፖለቲካ በሕዝብ ዘንድ የተጠላ ከሚያደርጉ እንከኖች መካከል ዘረኝነት ቀዳሚው ነው፡፡

ከዚህ አንጻር ለዛሬ በመንግሥታዊ ጋዜጦች ማለትም አዲስ ዘመን፣ ዘ ኢትዮጵያን ሄራልድ፣ በሪሳ፣ ዓል-አለም፣ ዘመን መጽሔት አሳታሚ የሆነው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ውስጥ የተንሰራፋውን የአንድ ብሄር የበላይነት ከድርጅቱ ሠራተኞች የደረሰንን መረጃ መሠረት በዝርዝር እናቀርባለን፡፡

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሚፈፀመውን ግፍ፣ በደልና ኢ- ፍትሀዊነት ለሚመለከተው አካል በማህበራዊ ሚዲያው ለማድረስ ስነሳ የጠ/ሚ ዶ/ር ዓቢይ አሕመድ አስተዳደር አፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንደሚወስዱ በመተማመን ነው፡፡
በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ “አለ” ቢባልም በስም እንጂ በተግባር አለ ለማለት አያስደፍርም፡፡ ምክንያቱም በድርጅቱ የሚከናወነውን ሥራ የማያውቅ፣ የሥራ ክፍሎችን ሥራ የማይከታተል፣ የብቃት ማነስና ቸልተኛነት የወረሰው፣ እንደዋና ሥራ አስኪያጅ ውሳኔ መስጠት የማይደፍር፣ በግልፅ የማይናገርል በተንኮለኛ በመሆኑ የእርሱን የሥራ ድርሻ ማንም እንዲወስንበት አሳልፎ በመስጠት እንዲያስተዳድር መንግስት ሃላፊነት የሰጠውን ድርጅት የአንድ ብሄር የበላይነት እንዲንሰራፋበት ለማድረግ እድል የፈጠረ ነው፡፡
በፕሬስ ድርጅት የሚገኙት ሰራተኞች በሁለት አስተዳደር እየተዳደሩና የደሞዝ ልዩነት ቅሬታ ፈጥሮ ባለበት ሁኔታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አንድ የአሰራርና የአመራር ሂደት እንዲፈጠር መስራት ሲኖርባቸው ይህንን ከማስፈፀም በተቃራኒው ሥራቸውን በመተው ሠራተኛውን ለቅሬታ አድርሰውታል፡፡

በምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅነት የተመደበው የትግራይ ተወላጁና የህወሀት አባሉ መብራቱ ኪሮስ በባህሪው መረጃ የሚያነፈንፍ በመሆኑ ወሬ የሚያቀብሉትን የራሱን ብሄር ሰዎች በማደራጀት የዋና ሥራ አስኪያጁን የወሳኝነት ሥራ በማንአለብኝነት በመንጠቅ ሠራተኞችን ከቦታ ቦታ በመቀያየር በርካታ ሰራተኞችን ከትግራይ ብሄረሰብና ከህወሀት አባላት በታች በዝቅተኛ የስራ መደብ ላይ በመመደብ ሞራል የሚነካ ተግባር እፈፀመ ይገኛል፡፡ይህንን ፅሁፍ በማንበብም በፕሬስ ድርጅት ውስጥ ምን እየተፈፀመ እንዳለ በግልፅ መገንዘብ ይችላል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሚያሳትማቸው የሕትመት ውጤቶች አዲስ ዘመን፣ ዘ ኢትዮጵያን ሄራልድ፣ አል-አለምና በሪሳ ጋዜጦች እንዲሁም ዘመን መፅሄት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹን ጋዜጦች የትግራይና የህወሃት አባላት በዋና አዘጋጅነት መምራታቸው አስገራሚ ሲሆን፤ አንዳቸውም እንኳን ለዋና አዘጋጅነት የሚያበቃ ችሎታና ብቃት የላቸውም፣

የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ የተመደበው/ አቶ ፍቃዱ ሞላ ትግሬ (ህወሀት) በጋዜጠኝነት ሙያ የደካሞች ቁንጮ የሆነ፣

የዘኢትዮጵያን ሄራልድጋዜጣዋናአዘጋጅ/ አቶ ሞላ ምትኩ ትግሬ፣ህወሀት/ ነገር ግን በእንግሊዝኛ እራሱን መግለፅ በፍፁም የማይችል፤ጋ ዜጠኞቹን እያስፈራራ ለመምራት የሚሞክር፣

የአል-አለም ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ/አቶ እዮብ ግደይ ትግሬ ፣ ህወሀት/ ቢሮ ውስጥ የማይቀመጥ፣ ለሰራተኛ ምሳሌ የማይሆን፣

በበሪሳ የኦሮምኛ ጋዜጣ ላይ በዋና አዘጋጅነት የህወሀት አባል ያልተመደበውም ኦሮምኛ ቋንቋ የሚችል የህወሀት አባል ባለመኖሩ ብቻ እንጂ ይህንን ከማድረግ የሚያስቸግረው እንዳልሆነ ከሚፈፀመው ሥራ መረዳት ይቻላል፡፡

ኢፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክፍል የረባ ሥራ ማይሰሩ፣ የሥራ ልምዳቸው ከሌሎች ሰራተኞች እጅግ አነስተኛ ነገር ግን ከፍተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው፤ ከአስር አመት ያላነሰ የሥራ ልምድ ለሚጠይቀው የሥራ መደብ ላይ በዜሮ አመት ተቀጥረው እያንዳንዳቸው ከአስራ አንድ ሺህ ብር በላይ ደሞዝ የሚከፈላቸው፡-
1. በሪሁ ብርሀነ
2. አብርሃም ____
3. አርአያ ጌታቸው (ለመብራቱ ኪሮስ በወሬ አቀባይነት በማገልገሉ በዘርፍ አስተባባሪ ደረጃ እድገት የተሰጠው)፣

የእነዚህ የአንድ ብሄር ስብስቦች የሥራ መደብ ድልድል የተካሄደው በምክትል ዋና ሥራ አስኪጁ በመብራቱ ኪሮስ ሲሆን፤ ማንም ሰው የሥራ ብቃት ቢኖረው እርሱ በመጥፎ አይን ካየ በደረጃ ዝቅ አድርጎ በሰው ጉዳት የሚዝናና ክፉና ቂመኛ ነው፡፡

በድርጅቱ ከጥበቃ ሰራተኝነት ተነስተው በሹፌርነት እንዲያገለግሉ ሥልጠና አግኝተው መንጃ ፈቃድ ከያዙት መካከል የትግራይ ተወላጅ የሆነው አንዱ የጥበቃ ሠራተኛ ብቻ ከድርጅቱ መኪኖች አንዱን እንዲሰጠው፤ ሌሎቹ እዚያው በጥበቃ ሥራቸው ላይ የገኛሉ፡፡

በፕሬስ ድርጅት መስሪያ ቤት በር አካባቢ ከሚገኝ የጥበቃ አንድ ክፍል ቤት የድርጅቱን ጥበቃዎች በማስለቀቅ ድርጅቱን በመጠበቅ ሥራ ላይ ላልተሰማራ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ሚስት እንድትኖርበት በመፍቀድ ሴትየዋ በድርጅቱ ግቢ ውስጥ እየኖረች ሲሆን፤ ለምን የሚል ጥያቄ የሚያነሳ ቢኖር የሚደርስበትን ስለሚያውቅ ማንም ለማንሳት አይደፍርም፡፡

የፕሬስ ድርጅት የስራ አመራር ቦርድ አባላትም ሆኑ በተወካዮች ምክር ቤት የድርጅቱ የበላይ ጠባቂዎች ስለድርጅቱ ውስጣዊ ችግር ለመረዳትና አድልዎ ያለበትን አሰራር ለማስወገድ ምንም ጥረት ያለማድረጋቸው የሚያሳዝን ቢሆንም ዛሬም በዚህ ሁኔታ መቀጠል ስለሌለብንና መፍትሄ ማግኘት ስለሚገባን መንግስት ፕሬስ ድርጅት ከታሰረበት የብሄር እስርቤት ሊታደገው ይገባል፡፡