ለሀገር ሰላም፣ ለሕዝብ ደህንነት ሲባል የህወሓት አመራሮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው!

“‘ፍቅር እንዲማሩ’ ብለን የእስር ማዘዣ ካወጡብን ሰዎች ጋር አብረን ማዕድ እየተቋደስን ነው!” ይህ ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው የተመረጡ ሰሞን ለታዋቂ የኦሮሞ ተወላጆች በቤተ-መንግስት ባዘጋጁት የእራት ግብዣ ላይ የተናገሩት ነው። የእስር ማዘዣ የወጣባቸው እሳቸውን ጨምሮ አምስት የኦህዴድ ባለስልጣናት እንደሆኑ ተገልጿል። በእርግጥ እኔ ከአንድ ወር በፊት ህወሓቶች ከፍተኛ የኦህዴድንና ብአዴን አመራሮችን እስር ቤት ለማስገባት አቅደው እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ገልጬ ነበር። ዶ/ር አብይ ተናገሩ ከተባለ በኋላም የኦህዴድና ብአዴን አመራሮችን ጠይቄ ለማረጋገጥ እንደቻልኩት በእርግጥ የእስር ማዘዣው ተቆርጦ ነበር።

“በእነ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው ቡድን ዶ/ር አብይ እና ለማ መገርሳን ጨምሮ በአምስት የኦህዴድ አመራሮች ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቶ ነበር” የሚለው ለብዙዎች አይዋጥላቸውም። ይህ ደግሞ ከሁለት ዓይነት እሳቤ የመነጨ ነው። አንደኛ፡- እንደ ለማ መገርሳና ዶ/ር አብይ ያሉ መሪዎችን ማሰር ከኦሮሚያ አልፎ መላ ሀገሪቱን ምን ዓይነት ቀውስ ውስጥ ሊከታት እንደሚችል በራሳቸው በማሰብ “ሕሊና ያለው ሰው ይህን አያደርግም” የሚል ነው። ሁለተኛ፡- ዶ/ር አብይ “‘ፍቅር የማራሉ’ ብለን የእስር ማዘዣ ካወጡብን ሰዎች ጋር አብረን ማዕድ እየተቋደስን ነው!” የሚለው የዶ/ር አብይ አባባል “ግራህን ሲመታህ ቀኝህን አዙርለት” የሚሉት ዓይነት ነው። ስለዚህ ዶ/ር አብይ የፖለቲካ እንጂ መንፈሳዊ መሪ አይደለም። “ፍቅርን እንዲማሩ ብዬ እስር ቤት ሊያስገቡኝ ከነበሩ ሰዎች ጋር ማዕድ እየተቋደስኩ ነው” ብሎ ሲናገር ማመን ከባድ ነው።

ይሁን እንጂ፣ እነ ዶ/ር አብይ ቢታሰሩ ኖሮ በሀገሪቱ ውስጥ ሊከሰት ይችል የነበረው ሁከትና ብጥብጥ ሆነ የዶ/ር አብይ መንፈሳዊ የሚመስል ፍቅርና ይቅርታ በህወሓቶች ዘንድ ቅንጣት ያህል ዋጋና ትሩጉም አልተሰጠውም፥ አይሰጠውም። በዜጎች ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል፣ በሀገር ላይ የሚያስከትለው ጉዳትና ኪሳራ ወይም ከዶ/ር አብይ ያገኙት ፍቅርና ይቅርታ፣ … ወዘተ በህወሓቶች ዘንድ አሳሳቢ አይደለም። ምክንያቱም የህወሓቶች መነሻና መድረሻ የራሳቸውን የበላይነትና ተጠቃሚነት ማስቀጠል ነው። ለእነሱ የፖለቲካ ትርጉምና ፋይዳ የስልጣን የበላይነትና ተጠቃሚነት ብቻ ነው።

የህወሓትን የስልጣን እና የኢኮኖሚ ብዝበዛ ለማስቀጠል በምድር ላይ ያለ ነገር ሁሉ መስዕዋት ይደረጋል። ለምሳሌ የሀገር ሉዓላዊነትና ነፃነት በስልጣንና ቁሳዊ ሃብት ሊለወጥ ይችላል፣ በስልጣን ላይ ለመቆየት ዜጎችን በተናጠል ከመግደልና ማቁሰል አልፎ በጅምላ-ጨራሽ መሳሪያ እስከመጨፍጨፍ ሊደርስ ይችላል። እንኳን ለሚወክሉት የፖለቲካ ማህብረሰብ ወልዶ-ላሳደጋቸው ቤተሰብ ፍቅር የላቸውም፣ ለባላንጣ ይቅርና ለዕድሜ-ልክ ወዳጅ ምህረት አያደርጉም። ምክንያቱም ከራስ-ወዳድነት የተረፈ እንጥፍጣፊ ፍቅር በውስጣቸው አይገኝም። በተለይ የህወሓት መስራቾችና አንጋፋ አመራሮች ከባርነትና ጭቆና በስተቀር ስለ ሕዝብ ነፃነትና እኩልነት ምንም ነገር አያውቁም።

የትኛውም የፖለቲካ ቡድን ለህወሓቶች መገልገያና መጠቀሚያ ከመሆን የዘለለ ፋይዳ የለውም። ለዚህ ደግሞ በትጥቅ ትግል ወቅት ትግራይ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የነበራቸውን ግንኙነት መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ ኢዲዩና ኢህአፓ ድርግን ከስልጣን ለማስወገድ የሚታገሉ ድርጅቶች ሲሆን ከትግራይ ክልል ለቅቀው የወጡት በደርግ ሳይሆን ህወሓት በከፈተባቸው ጦርነት ነው። ከዚህ በተጨማሪመ አሁን በስም የማላስታውሰውና በምስራቃዊ የትግራይ አከባቢዎች ሲንቀሳቀስ የነበረ የፖለቲካ ቡድን አመራሮችና አባላት ከህወሓት ጋር ለመደራደር መጥተው ሳለ ሌሊት በተኙበት በጥይት መረሸናቸውን እንደ እያሱ መንገሻና አረጋዊ በርሄ ያሉ የቀድሞ የህወሓት አመራሮች በመፅሃፎቻቸው ገልፀዋል።

ህወሓት ኢህአዴግን ሲመሰርት የተቀሩትን ሦስት አባል ድርጅቶች ያቋቋማቸው የህወሓት መገልገያና መጠቀሚያ እንዲሆኑ በማሰብ ነው። ህወሓት ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የሚለውን ድርጅታዊ አሰራር ያመጣው የተቀሩት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የተለየ የፖለቲካ አቋምና አመለካከት እንዳይዙ ለማድረግ ነው። ከዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ልጓምን ለመበጠስ ጥረት ያደረገ የኢህአዴግ አባል ድርጅት ወይም መሪ አይቀጡ-ቅጣት ተቀጥቶ መጨረሻው ውርደት፥ ስደት፥ እስራት… ወዘተ ይሆናል። ከኢህአዴግ ውጪ ያሉ “ተቃዋሚ” የፖለቲካ ድርጅቶችም የህወሓት መገልገያ ካልሆኑ እድሜያቸው አጭር ነው። ምክንያቱም ከህወሓት የተለየ የፖለቲካ አቋምና አመለካከት ያለው ድርጅት በሸርና አሻጥር ወዲያው ይፈርሳል። ለዚህ ደግሞ ኦነግ፥ ቅንጅት፥ አንድነት፥… እያሉ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።

ለህወሓት የፖለቲካ ቡድኖችና ድርጅቶች ቀርቶ የራሱ አባላትና አመራሮች እንኳን ከመገልገያነትና መጠቀሚያነት የዘለለ ፋይዳ የላቸውም። ማንኛውም አባልና አመራር ህወሓት ውስጥ መቆየት የሚችለው ከድርጅቱ መስራቾችና አመራሮች የተለየ አቋምና አመለካከት እስካልያዘ ድረስ ብቻ ነው። ህወሓት ውስጥ የተለየ ሃሳብና አስተያየት ያላቸው አመራሮች መጨረሻቸው ምን እንደሆነ ከእነ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) እስከ እነ ስዬ አብርሃ ያሉትን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። እንደ ኦህዴድ ካሉ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አመራሮች ደግሞ ከእነ ዮናታን ዲቢሳ እና አልማዝ መኮ እስከ ጁነዲን ሳዶ ያሉትን መጥቀስ ይቻላል።

በሀገርና ሕዝብ ጉዳይ ላይም ቢሆን የህወሓቶች አቋም ወጥና ተመሳሳይ ነው። በህወሓቶች ዘንድ “ሀገር” ማለት ከመጠቀሚያነት የዘለለ ፋይዳ የለውም። ለዚህ ደግሞ ከአሰብ ወደብ እስከ ባድመ ድረስ ህወሓቶች የፈፀሙትን ክህደት መጥቀስ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ፣ ህዝብም ቢሆን በህወሓቶች ዘንድ ከስልጣን መወጣጫነትና የሃብት ምንጭነት የዘለለ ፋይዳ የለውም። በፖለቲካው ላይ ያላቸው የስልጣን የበላይነት አደጋ ላይ የወደቀ መስሎ በተሰማቸው ቁጥር የሀገሪቱን ህዝብ በጥይት ያጭዱታል፣ በእስር ቤት ያጉሩታል፣ ከመኖሪያ ቤቱና መሬቱ ያፈናቅሉታል።

ከሌላው በተለየ ደግሞ የትግራይ ሕዝብን የስልጣን መወጣጫ ሆኖ እንዲያገለግላቸው በጥብቅ ይከታተሉታል፥ ይቆጣጠሩታል። ለዚህ የሚሆን ከክልል ጀምሮ እስከ ሰፈርና ጎጥ የሚደርስ የቁጥጥርና ክትትል አደረጃጀት ዘርግተዋል። የትግራይ ህዝብ ለህወሓት የስልጣን መወጣጫ መሆኑ ያበቃ እለት ግን ከተቀረው የኢትዮጲያ እና የጎረቤት ሀገሮች ጋር ደም-አፋሳሽ ግጭትና ዕልቂት ውስጥ እንደሚከቱት አልጠራጠርም። ለዚህ ደግሞ በዙሪያው ካለው የአማራ ሕዝብ ነጥለውታል፣ ከኤርትራ ሕዝብ አቃቅረውታል፣ ከአፋር ሕዝብ ጋር ደግሞ ቂምና በቀል ደግሰውለታል።

ዶ/ር አብይ “‘ፍቅር እንዲማሩ’ ብለን የእስር ማዘዣ ካወጡብን ሰዎች ጋር አብረን ማዕድ እየተቋደስን ነው!” በማለት ፍቅርና ይቅርታ የሚያሳየው ለእነዚህ የህወሓት አመራሮች ነው። ከደርግ የተረከቧትን ሀገር እየከፋፈሉ ለባዕዳን የሸጡ ሰዎች ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ ለምንና እዴት ሊያስቡ ይችላሉ? ወልዶ ላሳደጋቸው የትግራይ ሕዝብ ፍቅርና አክብሮት ያነሳቸው ሰዎች ለተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚሆን ክብርና ፍቅር ከየት ያመጡታል? ለእነ አረጋዊ በርሄ፣ ስዬ አብረሃ፣ ገብሩ አስራት፣ … ከመሳሰሉ የትግል ጓዶቻቸው ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት በውይይትና ይቅርታ ማለፍ የተሳናቸው ሰዎች የዶ/ር አብይን ይቅርታ እንዴት ሊገነዘቡት ይችላሉ። ዘወትር ስለራሳቸው ስልጣንና ጥቅም የሚያስቡ ሰዎች እንዴት ሀገርና ሕዝብ ሕልውና ላይ እንዲወስኑ ዕድል ይሰጣቸዋል?

በአጠቃላይ የህወሓት መስራቾችና አመራሮች እስካሁን በሀገርና ሕዝብ ላይ የፈፀሙት ይበቃል። ከዚህ በኋላ ግን የእነሱ ግፍና በደል ሊያበቃ ይገባል። ለሀገርና ሕዝብ ፍቅር የሌላቸው ሰዎች ይቅርታና ምህረት አይገባቸውም። እስካሁን የፈፀሙት ግፍና በደል መቋጫ የሚያገኘው ለፍርድ ቀርበው ሲዳኙ ብቻ ነው። ስለዚህ በሀገር ላይ ክህደት፣ በህዝብ ላይ በደል የፈጸሙ የህወሓት መስራቾችና አመራሮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው!!

One thought on “ለሀገር ሰላም፣ ለሕዝብ ደህንነት ሲባል የህወሓት አመራሮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው!

 1. ዶ/ር አብይን ልንደግፋቸዉ ብቻ ሳይሆን ልንጠብቃቸዉም ይገባናል!

  ክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶክተር አብይ የመላዉን ህዝብ ተስፋ ያጫረ የለዉጥ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ወደ ስልጣን በወጡ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ለዘመናት ተስፋ ርቆት ለቆየዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ተስፋ በመስጠት ሳይወሰኑ በተግባርም መዉሰድ የጀመሯቸዉ እርምጃዎች በቀላሉ የሚታዩ አይደሉም፡፡ወደፊትም በርካታ ለሀገር ጠቃሚ ስራዎች እንደሚሰሩ የአስካሁኑ አካሄዳቸዉ ምስክር ነዉ፡፡ይሁን እንጂ ጠ/ሚኒስትሩ በርካታ ፈተናዎች እንደተደቀነባቸዉና ከጀመሩት ጠቃሚ ስራ ሊያናደናቅፏቸዉ የሚፈልጉ መሴሪ ኃይሎች እንዳሉ ተረድተን ልንደግፋቸዉ ብቻ ሳይሆን ልንጠብቃቸዉም ይገባናል፡፡ የእነዚህ የጥፋት ኃይሎች አቅማቸዉ በቀላሉ ሊታይ የሚገባዉ ባለመሆኑ ንቀን የምናልፈዉ አይደለም፡፡ለሰላሳ ዓመታት ላላነሰ ጊዜ በስልጣን ላይ መቆየታቸዉ በፈጠረላቸዉ አጋጣሚ ከህዝብ እየዘረፉ ባካበቱት መጠነ-ሰፊ ሀብት ተጠቅመዉ በገንዘብ ኃይል ቅጥረኛ ነፍሰገዳዮችን በመቅጠር በዲሞክራትና ተራማጅ ኃይሎች ላይ ወንጀል ከመፈጸም የማይመለሱ ናቸዉ፡፡በዝርፊያ ካካበቱት መጠኑ የበዛ ሀብት ሌላ የዘረጉት የግኑኝነት ድርና የመሰረቱት መዋቅር በቀላሉ ሊታይ የሚገባዉ አይደለም፡፡እነዚህ ወገኖች የዶ/ር አብይን አመራርነት ለመቀበል ያልፈልጉበት ዋነኛ ምክንያት ለዓመታት የለመዱትን ዝርፊያ የሚገታ ከመሆንም ሌላ በተለያዩ አጋጣሚዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ በሰሩት ግፍ በህግ የሚጠየቁበት ወቅት ላይ መደረሱ በፈጠረባቸዉ ስጋት እንደሆነ በሚገባ እናዉቃለን፡፡ህወኃት የሚባለዉ ነፍሰገዳይ ቡድን በማንኛዉንም ዘዴ ተጠቅሞ በዶክተር አብይ የተጀመረዉን የለዉጥ እርምጃ ለማስቆም ሀገር አስከማፈራረስ ድረስ ከመሄድ የማይመለስ አጥፊ ኃይል መሆኑን መዘንጋት አይኖርብንም፡፡

  የህወኃት ትልቁ ችግር ዲሞክራት አለመሆኑ ወይም አምባገነን መሆኑ ብቻ አይደለም፡፡የህወኃት ዋናዉ ችግር ኢትዮጵያዊ አለመሆኑና ለኢትዮጵያና ለህዝቧ ከፍተኛ ጥላቻ ያለዉ መሆኑ ነዉ፡፡ ይህ የጠላትነት አቋሙ ገና ከምስረታዉ ጀምሮ የተጠነሰሰና አስካሁንም ሊታረም ያልቻለ ነዉ፡፡ህወኃት ኢትዮጵያን እየጠላ ኢትዮጵያን ሲገዛ በኖረበት ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ዉስጥ ይህን ጸረ-ኢትዮጵያ አቋሙን ለመደበቅ መሞከሩ ባይቀርም ነገር ግን በያንዳንዱ ድርጊቱ ራሱን እያጋለጠ እርቃኑን ቀርቷል፡፡ህወኃት አሁን በደረሰበት ደረጃ ድብቅ ባህሪዉን ከዚህ በላይ መደበቅ የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን በመረዳቱ የመጨረሻ አማራጭ አድርጎ የያዘዉ አቋም በቀጥታ ወደግድያ፤ሽብርና ህዝቡን እርስበርስ ማጋጨትን ስራዬ ብሎ በሁሉም አካባቢዎች ማካሄድ ነዉ፡፡

  ህወኃት ሞት የፈረደባቸዉ ብዙ ብሆኑም ቅድሚያ እርምጃ ለመዉሰድ የወጠነዉ በሀገሪቱ ቁንጮ አመራሮች በተለይም በዶ/ር አብይና በአቶ ለማ መገርሳ ላይ ነዉ፡፡ወያኔ ዉጥን መሰረት ከተቻለ ዶክተር አብይን በማገት ለጥቂት ገዜ በመሰወር እንደቅድመ ሁኔታ አስገድዶ ለዉጡን እንዲተዉ ማድረግ፤ይህን ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ ሁለቱን ሰዎች መግደል ነዉ፡፡የግድያ እርምጃዉን ለማስፈጸም ያቀደዉ በከፍተኛ ገንዘብ የተቀጠሩ የኤርትራ ስዴተኞችን በመጠቀም ነዉ፡፡ኤርትራዉያን ስደተኞችን ለመጠቀም የመረጠዉም የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ሁኔታ አስተማማኝ ስለመሆኑ አርግጠኛ ሊሆን ባለመቻላቸዉ ነዉ፡፡አንድቀን ተጸጽተዉ ሊያጋልጡት እንደሚችሉ ገምቷል፡፡ኤርትራዉያኑ ስደተኞችን በተመለከተ ግን ጠቀም ያለ ክፍያ ከተከፈላቸዉ የታዘዙትን ሁሉ ለመፈጸም ወደኋላ የሚጎትታቸዉና የሚጸጽታቸዉ ምክንያት እንደማይኖር እርግጠኛ በመሆኑ ነዉ፡፡ ሌላዉ ለአፈናና ለገዳይነት የተማመነዉ የሶማሌ ክልል ነፍሰ ገዳዮችን ነዉ፡፡ ሙሉ ኦፕረሽኑን በማቀናጀት ረገድም የወያኔ ጄነራሎች ሃላፊነት ወስደዉ በትጋት እየሰሩ ነዉ፡፡ ከሰሞኑ ለአበቱታ አዲስ አበባ ከመጡ የሶማሌ ክልል ሽማግሌዎች መካከል አራቱን አፍነዉ ወዴት እንዳደረሷቸዉም ገና አልታወቀም፡፡ በዶክተር አብይ ብርታት በቅርቡ ከአስር የተለቀቁትን አርበኛዉን አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌን በቅጥረኛ አፋኝ ኃይሎች በመጠቀም ከየመን አፍኖ በማምጣት ለአመታት በአስር ሲያሰቃቸዉ እንደነበረ የሚታወቅ ነዉ፡፡ ወያኔ ህጻናትን፤ ሴቶችን፤ አቅመ ደከማ ሽማግሌዎችና የቤተክርስትያን አባቶችን ሁሉ እያፈነ በስዉር አስርቤት ማሰቃየት የተካነበት በመሆኑ በመንግስት አመራሮች ላይ ተመሳሳይ ተንኮል ከመስራት እንደማይቆጠብ እናዉቃለን፡፡

  የኢትዮጵያ ህዝብ ከዶክተር አብይ ጎን መቆምና በሳቸዉ ላይ የሚሰራዉን ደባ መከላከል ያለበት ለራሳቸዉ በግል ለዶ/ር አብይ ተብሎ ሳይሆን ለራሳችን ስንል የምናደርገዉ ነዉ፡፡ዶክተር አብይን በማንኛዉም መንገድ ከእርምጃቸዉ እንዲታቀቡ የሚደረግ ሙከራ አደጋዉ ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ነዉ፡፡ለዉጡ ድንገት ተቀልብሶ ስልጣን በነዚህ ጅቦች እጅ ቢገባ ህወኃት በለመደዉ መንገድ ጅምላ የበቀል እምጃ መዉሰዱ ሳይታለም የተፈታ ነዉ፡፡ህወኃት ገና በረሃ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ አስቀድሞ ባቀደዉ ዉጥኑ መሰረት ከኢትዮጰያ ለመዉጣት ዝግጅቱን አጠናቆ ጨርሷል፡፡የቀረዉ ነገር ቢኖር ሌላዉን የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል የእርስበርስ ግጭት በመፍጠር ሀገሪቱን እንደሶርያ ማፈራረስ ነዉ፡፡ወያኔ ከቀድሞዉ እቅዱ ያልሰመረለት ነገር ቢኖር ከኤርትራ ጋር በአንድነት ታላቋን ትግራይ የመመስረት እቅዱ ሲሆን እሱም ቢሆን ሊሳካ ያልቻለዉ በኤርትራዉ መሪ ኢሳይስ እምቢተኝነት ነዉ፡፡ስለዚህ የቀረዉ አማራጭ ክልን ገንጥሎ ብቻዉን መሆን ሲሆን ለዚህ ዓላማዉ መሳካት አጋር ክልሎችን በተለይም የሶማሌዉን ክልል አምባገነን ፕረዝደንት ዓሊን በመጠቀም ነዉ፡፡

  ህወኃት መሴሪ ዓላማዉን እዉን ለማድረግ በማሰብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ የጥፋት ተግባር እየፈጸመ ያለዉ በደቡብ ክልል ላይ ነዉ፡፡ከሰሞኑ ሰላማዊ በሆነዉ የሲዳማ ህዝብ የፍቼ ጨምበላላ በዓል አስታኮ የቀሰቀሰዉ የርስበርስ ግጭት ተጠቀሽ ነዉ፡፡ከዓመታት በፊት በሲዳማ ህዝብ ለይ ያደረሰዉን ጭፍጨፋም የሚዘነጋ አይደለም፡፡ በወልቂጤ፤ በኮንሶም እያደረሰ ያለዉ እኩይ ድርጊትም የዚህ ክፉ ዓላማቸዉ አንድ ማስረጃ ነዉ፡፡በመቶ ሺህ የሚቆጠር የኦሮሞችን ከቀያቸዉ በግፍ ያፈናቀለና በርካታ ግድያም በመፈጸም በአለም መገናኛ ብዙሃን በወንጀለኛነቱ የሚታወቀዉን የሶማሌ ክልል ፕሬዝንዳትን ጀግናና ባለ ራእይ መሪ እያለ ወያኔ ሚዲዎች ማሞካሸታቸዉም አለምክንያት አይደለም፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ ከደቡብ ክልል በንጹኃን ዜጎች ላይ ባደረሰዉ መጠነ ሰፊ በደል በወንጀለኝነቱ በህዝብ ክፉኛ የሚጠላዉ ሺፈራዉ ሸጉጤ እንደለመደዉ የወያኔ ዓላማ አስፈጻሚ በመሆን በገዛ ህዝቡ ላይ ከፍተኛ በደል ማድረሱን ገፍቶበታል፡፡ልክ እንደ አቶ ሽፈራዉ የወያኔ ሎሌ ሆነዉ እያለገሉ ያሉ በርካታ የደህዴን አመራሮች ለፍርድ የምትቀርቡበት ቀን ሩቅ አለመሆኑን ተረድታችሁ ስትበድሉት የቆያችሁትን ህዝብ ይቅርታ ጠይቃችሁ ከህዝብ ጎን እንድትቆሙ እንመክራችኋለን፡፡በደቡብ ክልል ባሉ መስተዳድሮች ከላይ አስከታች ተሰግስገዉ ከክልልቻዉ ህዝብ መብት ይልቅ ወያኔን ለማገልገል የቆሙ ባንዳዎች በርካታ መሆናቸዉን እናዉቃለን፡፡ በተጨማሪ ያለችሎታቸዉ ትላልቅ ማእረግ የታደላቸዉ የክልሉ ተወላጅ የሆኑ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች የወያኔ አገልጋይ አለመሆናችሁን በተግባር እንዲታሳዩት ህዝባችሁ ይፈልጋልና እንድታስቡበት እንመክራችኋለን፡፡ወያኔ እንደሆን ዉድቀቱ ከሳምንታት ዕድሜ የማበልጥ መሆኑን አዉቃችሁ ራሳችሁን እንዳታሞኙ ትመከራላችሁ፡፡ምርጫዉም የናንተዉ ነዉ፡፡

  የትኛዉንም የዶ/ር አብይን የለዉጥ አርምጃ መለካት የነበረበት ለመላዉ ሀገሪቱ ህዝቦች ከሚሰጠዉ ጠቀሜታ አንጻር መሆን ሲገባዉ እነዚህ ሁሉንም ነገር ከራሳቸዉ ፍላጎትና ጥቀም አንጻር ብቻ የሚመዝኑ፤ ለኢትዮጵያ ቅንጣት ፍቅር የሌላቸዉ እኛ ያልነገስንባትና እኛ የማንገዛት ኢትዮጵያ ስትፈልግ እንደ ሶሪያ ዶግ አመድ ትሁን የሚሉ የሕወኃት ሰዎች ዶክተር አብይ ላይ ሊደብቁት ያልቻሉትን ጥላቻቸዉን እያየን ነዉ፡፡ማንኛዉም ለዉጥ እርምጃ ጠቀሜታዉ የሚለካዉ ለአብዛኛዉ ህዝብ ተብሎ መሆኑ ቀርቶ የህወኃት ሌቦች ለስርቆታቸዉና ለአፈና የማያመች መስሎ ስለታያቸዉ እርምጃዉን ስለተቃወሙ ዶክተር አብይ ከእርምጃቸዉ ለአፍታም እንደማይገቱ ሊያዉቁት ይገባል፡፡ከፌዴራላዊ ስርአቱ አደረጃጃት ጀምሮ ህገመንግስቱና ሌሎች ህጎችና ፖሊሲዎች ሁሉ ሲጫኑብን የነበረዉ ለህዝብ እንዲጠቅም ታስቦ ሳይሆን ለወያኔ አገዛዝ እንዲያመች ተብሎ እንደነበር በሚገባ የሚታወቅ ነዉ፡፡እነዚህ ጸረ -ህዝብ የሆኑ አሳሪ ህጎች አንድባንድ ተሸረዉ በምትካቸዉ በህዝብ ሙሉ ፈቃድ አዳዲስ ህጎችና ፖሊሲዎች እንዲወጡ እንፈልጋለን፡፡ከእንግዲህ ወያኔን ለማስደሰት ተብሎ የሚወጣ ህግም ሆነ የሚፈጠር አደራጃጃት አይኖርም፡፡

  ለዘመናት በህዝቦች መካከል ሰፍኖ የቆየዉ መቻቻልና የርስበርስ ፍቅር ወያኔ ባመጣዉ የዘረኝነት ፖሊሲ ምክንያት ወደ ርስበርስ ግጭት እንዲሁም ዜጎች ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬ በገፍ የሚፈናቀሉበትና የሚገደሉበትና ሌሎች አሳዛኝ ወንጀሎች የሚፈጸምበት ሀገር ሆና ቆይታለች፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሀገሪቱን ከዚህ አሳዛኝ ሁኔታ ለማዉጣ እልህ አስጨራሽ ጥረት ማድረጋቸዉ ያላስደሰዉ ወገን ካለ ህወኃት ብቻ ነዉ፡፡ ህዝብ ከፍተኛ አመኔታ እየሰጣቸዉ ላለዉ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አካሄድ ያሰጋቸዉ አንዳንድ የወያኔ አመራሮችም በግል በዶ/ር አብይና በሳቸዉ በሚመራዉ አስተዳዳር ላይ ህዝባዊ ተቃዉሞ ለመቀስቀስና ብሎም ሰዉ ሰራሽ ብጥብጥ ለማስነሳት ከፍተኛ ደባዎችን በመፈጸም የህዝብ ምሬት በመጨመር መንግስትን ለማስጠላት ከፍተኛ መፍጨርጨር እያደረጉ ነዉ፡፡በወያኔ የሚደጎሙ ማህበራዊ ሚዲያዎች መካከል በተለይ ትግራይ ኦን ላይንና አይጋ ፎሬም የተሰኙት መስኪኑን የትግራይን ህዝብ አሳስተዉ እንደለመዱት በጦርነት ሊማግዱት በማሰብ የጦርነት ቅስቀሳ እያደረጉ ነዉ፡፡

  የኑሮ ዉድነትና የስራ አጥነት የመጨረሻዉ ደረጃ ላይ ደርሶ ህዝቡን ተስፋ ያስቆረጠበት ወቅት በመሆኑ ማንኛዉም አማራጭ መፍትሄ በመጠቀም ህዝቡን ከዚህ ችግር ማዉጣት የመንግስት ሃላፊነት በመሆኑ ዶ/ር አብይ እየወሰዱት ያለዉ ቆራጥ ዉሳኔዎች የህዝብን ፍላጎት መነሻ ያደረገ መሆኑ እየታወቀ ገና ለገና ሰላሳ ዓመት ባስቆጠረዉ የወያኔ አስተዳዳር ዘመን እነሱ ሊሰሩት ያልቻሉትን ዶክተር አብይ በጥቂት ሳምንታት የስልጣን ቆይታቸዉ ሰርተዉ በማሳያታቸዉ የተቸራቸዉን አድናቆትና የህዝብ ፍቅር ቅናት ያሳዳረባቸዉ ወገኖች ሆን ብለዉ አስተዳዳራቸዉን ለማበላሸት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡
  ከሰሞኑ ደግሞ ብሄረ-አማራ ንቅናቄ የሚባል የአማራን መብት ማስከበር ዓላማ ያደረገ የፖለቲካ ድርጅት በይፋ መመስረት በወያኔዎች ላይ አጉል ስጋት የፈጠረዉን መንጫጫት እየታዘብን ነዉ፡፡በሀገሪቱ ባለፉት ሶስት አስርተዓመታት እንደ አሸን የፈሉ ዘዉግ ተኮር ድርጅቶች በሞሉበት ሀገር የዓማራን መብት ለማስከበር አንድ ድርጅት መመሰረት እንደ አዲስ ነገር ተቆጥሮ ለህወኃት ይሄን ያህል ስጋት ለምን ሊፈጥር እንደቻለ ለመረዳት አይከብደንም፡፡ከእንግዲህ “ብአዴን” የሚባለዉ አሳፋሪ ድርጅት ሲያደርግ እንደቆየዉ ለወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚ በመሆን የአማራዉን ህዝብ መብትና ነጻነት ማፈን እንደማይቻል በመረዳታቸዉ ነዉ፡፡የአማራ ህዝብ በወያኔ ትዝዛዝ በብኤዴን ተባባሪነት የተነጠቁበትን የክልሉን መሬትና ያለፈቃዳቸዉ ትግሬ እንዲሆኑ የተፈረደባቸዉ ወልቃይትና ራያን የመሳሰሉ ህዝቦች መብታቸዉን ከማስከበር የሚግደዉ ነገር እንደሌለ በመረዳታቸዉ ቢሰጉ አይፈረድባቸዉም፡፡

  በመጨረሻም ለትግራይ ህዝብ ማሳሰብ የምንፈልገዉ ጥቂት መልእክቶች አሉን፡፡

  የህወኃት ሽፍቶች ከአብራክህ ወጥተዉ በስምህ የሚነግዱብህ ጭቁን የትግራይ ህዝብ ሆይ፤
  ያለፈዉን የደርግ ወታደራዊ አገዛዝ ለማስወገድ አስራሰባት ዓመታት ባደረከዉ እልህ እስጨራሽ ትግል መጠነ ሰፊ መስዋእትነት እንደከፈልክ በሚገባ አናዉቃለን፡፡ትልቅ አክብሮትም አለን፡፡ይሁን እንጂ በስምህ የሚነግደዉ ህወኃት የሚባለዉ ነፍሰገዳይ ሽፍታ ቡድን ስልጣን ከያዘበት ዘመን አንስቶ ባለፉት 27 ዓመታት በቀረዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያደረሰ የቆየዉ በደል በሰሚ ሰሚም ቢሆን ሳትሰማ አትቀርም፡፡እጅግ ጨዋና ጠንካራ የሀገር ፍቅር ያለህ የትግራይ ህዝብ ህወኃት በአንድነታችንና ሉአላዊነታችን ላይ ሲሰራ የነበረዉን አፍራሽ ድርጊትም ትገነዘባለህ ብለን እንገምታለን፡፡እንደምታዉቀዉ ህወሃት ወንድሞችህ በሆኑት በመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጦርነት አዉጇል፡፡በቢሊዮን የሚቆጠር የሀገር ሀብት ያለከልካይ ሲዘርፍና መብቱን የሚጠይቀዉን ህዝብ ያለአንዳች ርህራሄ ሲጨፈጭፍ የነበሩ የህወኃት ወንጀለኞችን ወደአስርቤት መላክ ሲቻል በክብር ጡረታ እንዲወጡ መደረጉን እንደትልቅ ዉሌታ ሊቆጥሩ ሲገባ በደል የደረሰባቸዉ አድርገዉ በመቁጠር የጠ/ሚኒስትር አብይን አስተዳዳር ለማፍረስ ቢሎም የግድያ ወንጀል ለመዉሰድ በጉያህ ስር ሆነዉ እየዶለቱ እንዳሉ በሚገባ ታዉቃለህ፡፡የሀገሪቱን ሀብት በጠራራ ጸሀይ እየዘረፉ “ኢፌርት” የሚባል ድርጅት ስም ያከማቹትን ሀብት በልጆቻቸዉና በዘመድ አዝማድ ስም በዉጭ ባንኮች ማስቀመጣቸዉም ካንተ የተሰወረ አይደለም፡፡እነዚህ ሌቦች እዉነት ለትግራይ ህዝብ ተቆርቋሪ ከሆኑ በዉጭ ያከማቹትን ገንዘብ ለምን የልማት ስራ አይሰሩልህም፡፡”በእኔ ስም ያከማቻችሁትን ገንዘብ አምጡ” ብላችሁ ለምንስ አልጠየቃችሁም?ሌላዉ የአትዮጵያ ህዝብ እየተዘረፈ ትግራይን ማደለብ ተገቢ አለመሆኑን ተቆርቁራችሁ ለምን የሚል ጥያቄስ ጠይቃችሁ ታዉቃላችሁ? በትግራይ በያንዳንዱ ወረዳ መጠነ ሰፊ የልማት ተቋማት ሲቋቋሙ በአንጻሩ በሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች ግን የህዝብ ማሰቃያ አስርቤት በስፋት ሲገነባ እንደነበር አታዉቁም ማለት ነዉ ?መብታቸዉን የጠየቁ ዜጎችን በአደባባይ የሚረሽነዉ አጋዚ ወታደር፤አስሮ ፍርድ ቤት የሚገትረዉ ፖሊሲና አቃቤ ህግ ፤የሚፈርደዉ ዳኛና አስርቤት ዉስጥ የሚያሰቃየዉ መርማሪ ሁሉ ከአናንተዉ አብራክ የወጡ የትግራይ ሰዎች መሆናቸዉን አታዉቁምን?በነዚህ አስርቤቶች አንድም የትግራይ ተወላጅ የሆነ ታሳሪ እንደሌለና የሚታሰረዉ ሁሉ ኦሮሞና አማራ ብቻ መሆኑን አታዉቁም ማለት ነዉ?
  ወያኔ ኢትዮጵያን እንደማይፈልጋት እያወቅን አስካሁን አብረን ዘልቀናል፡፡ከዚህ በላይ ጫንቃችን አይችልም ፤ትእግስታችንም ተሟጧል፡፡ከዚህ በላይ ወያኔ ኢትዮጵያን ሊያጠፋት ሲያሴር በዝምታ ማዬት አንችልም፡፡ወያኔን ከጫንቃችን ለማዉረድ ቆርጠን ተነስተናል፡፡ ህዝብ በዚህ መንገድ መቀጠል እንደማይችል በሚገባ ትገነዘባላችሁ ብልን እናስባለን፡፡የትግራይ ህዝብ ህወኃት የሚባለዉን የህዝብ ጠላት ከጫንቃህ አስወግደህ እንድትገላገል እንጠይቃለን፡፡ስለዚህ አቋምህን ግልጽ ማድረግ ይጠበቅብሃል፡፡ሀገራችንን ከመበታተን ለማዳን ማንኛውንም መስዋእትነት ለመክፈል ቆርጠን መነሳታችን ልታዉቅ ይገባሃል፡፡ስለዚህ ከጎናችን ተሰለፍ፡፡ከዚያ ዉጭ ለሚፈጠረዉ ሁሉ ሃላፊዉ ራሳችሁ መሆናችሁን ልናሳዉቃችሁ እንወዳለን፡፡ወያኔ እኔ ካልገዛኋችሁ በስተቀር ሀገሪቱን እበታትናለሁ፤ እንደ ሶርያም አደርጋለሁ እያለ በተደጋጋሚ ዝቷል፡፡
  ህወኃት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ባለፉት 27 ዓመታት ሲያደርስ የነበረዉ ብዝበዘና አፈና ላንተ ለትግራይ ህዝብ ታስቦ እንዳልሆነ ልታዉቀዉ ይገባል፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ብዙ በደል እየደረሰበት 27 ዓመታታ በትእግስት ኖሯል፡፡የግፍ ጽዋዉ ሞልቶ መፍሰስ በመጀመሩ ህዝቡ መብቱንና ነጻነቱን ለማስከበር ቆርጦ ተነስቷል፡፡የትግራይ ጭቁን ህዝብ ይህን የወያኔ አፋኝ አጋዘዝ ለማስገድ ከተቀረዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ልትቆም ይገባል፡፡ሀገሪቱን ከዉድቀት ለማዳን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የጀመሩትን የለዉጥ እርምጃ ለማደናቀፍ የሚሞክሩ የወያኔ አሽከሮች ከዚህ ድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ አበክረን እናሳስባለን፡፡ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እነ አብይ የጀመሩት ቅዱስ ተግባር እንዳይደናቀፍ ማኛዉንም መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናችንን እንድታዉቁልን እንፈልጋል፡፡እናተም ከእንግዲህ ወዲያ ወያኔን መደበቅና የወያኔን እኩይ ድርጊት መደገፍ ከመላዉ የኢትዮፕያ ሀዝብ ጋር እንደሚያቆራርጣችሁ ለመጨረሻ ጊዜ ለማሻሻብ እንወዳለን፡፡የሶማሌ ክልልን ወንጀላኛ ዐሊን በሚመለከት ግን በቅርብ ጊዜ የእጁን እንደሚያገኝ እንድታወቁት ይሁን፡፡ ጨኑ ጫንያለዉ ነኝ ከታቦር ስር

  Like

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡