የዲላ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በዜጎች ላይ የሚደረሰውን መፈናቀል በመቃወም ስራ ለቀቁ

ፕሬዝዳንት ዶ/ር ቃልኪዳን ነጋሽ በትምሕርት ስርዓቱ ውስጥ በሚንፀባረቀው ብሄርን መሰረት ያደረገ ማጥላላትና በዜጎች ላይ የሚደረሰውን መፈናቀል በመቃወም ስራቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን አስታወቁ።

በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመምህርነትና በሀላፊነት ያገለገሉት ዶ/ር ቃልኪዳን ለዋዜማ እንደተናገሩት ያለፈውን አንድ ዓመት ተኩል ያህል በፕሬዝዳንትነት በመሩት የዲላ ዩንቨርሲቲ ከተፈጠረው የከረረ ብሄርን ያማከለ ሽኩቻ በተጨማሪ ሰኔ ሁለት ቀን በዩኒቨርሲቲው የደረሰው የቦንብ ጥቃት ለደህንነቴ የሚያሰጋ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብለዋል።

በዚህ እንቆቅልሽ በሆነ የቦንብ ጥቃት ዙሪያ መረጃዎች እንዲድበሰበሱና ተገቢ ምርመራ እንዳይካሄድ መደረጉ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮብኛል ብለዋል።

“ለብሄረሰቦች እኩልነት መረጋገጥ በቅን ልቦና ድጋፍ ሳደርግ ቆይቻለሁ አሁን ግን በብሄር ስም የሚደረጉ ሙስናና የስልጣን መባለግ የሚያስከትሉትን አደጋ በመመልከት እንዲሁም በአካባቢው ሰሚ ያጣው የዜጎች መፈናቀል ትኩረት እንዲያገኝ ስል ከሀላፊነቴ ለመልቀቅ ወስኛለሁ” ይላሉ ዶ/ር ቃልኪዳን።

ለትምህርት ሚንስትሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ በፃፉት ደብዳቤም ችግሩ አሁን ካለበት ደረጃ ተባብሶ የከፋ ቀውስ ከመከተሉ በፊት እርምጃ መወሰድ አለበት ብለዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው በጌዳኦ ዞን ሲሆን ከኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ጋር ይጎራበታል።
በቅርቡም በአካባቢው ስባት መቶ ሺህ የጌድኦ ብሄር አባላት ከሚኖሩበት የኦሮምያ ክልል ተፈናቅለዋል።

በአካባቢው ያለው የብሄር ግጭት እኔንም እንደአካባቢው ማህበረሰብ የሚመለከተኝ በመሆኑና መንግስት ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠቱ ያሳስበኛል ያሉት ዶ/ር ቃልኪዳን የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ይህን አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ትኩረትእንዲስጡት ተማፅነዋል።


ምንጭ፦ ዋዜማ ራዲዮ

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.