አብዲ ኢሌ፣ ኦሮሚያ እና የአብይ አህመድ ሪፎርም AND ITS PANDORA’S BOX

መምግሥቱ አሰፋ

አብዲ ኢሌ የፈጸምኩት በደል በእንትና ነው ብሎ ይቅር በሉኝ ካለ ይኸው ምራቁ አልደረቀም። የሶማሌ ልዩ ኃይል በምሥራቅ ሐረርጌና በምዕራብ ሃረርጌ 3 የኢሮሚያ ፖሊስ፣ 1 የመከላከያ ሠራዊት አባል እና 1 ሲቪል በድምሩ 5 ሰዎችን ገድሎ 7 ክፉኛ አቁስሏል።

አሁን በደረሰኝ መረጃ ከመቶ በላይ ሰው በሞያሌ መገደላቸውን ነው።

በሶናሌ ልዩ ኃይል የተገድለ የኦሮሚያ ፖሊስ አባል
ዛሬ በሶማሌ ልዩ ኃይል የተገደለ

ባለፉት ጊዜያት ተመሳሳይ ጥፋቶችን ሲያጠፋ ቆይቷል። የአብዲ ኢሌ ፖለቲካው ውስብስብ ነው። አሁን ግን ይቀጥል ይሆን? ኦህዴድ ግን ምን ያህል እወክላለሁ ለሚለው ሕዝብ ሊቆም ይችላል? አብይ አህመድ የኦሮሚያን ጉዳይ ችላ ብለውታል የሚባለው እንዴት ነው?

እስኪ ለኔ እስከሚገባኝ ድረስ በትንሹ ላውራ….

፩. አብዲ ኢሌ ከባድ የፖለቲካ ቁማር እየተጫወተ ነው (at the cost of the lives of citizens). ፖንዶራ ቦክስ እከፍታለሁ የበለጠ ምስጢር ከማላወጣ እስክትምሩኝ እና እስክትምሩን ጭፍጨፋዬን እቀጥላለሁ እያለ ነው። ምናልባት የመጨረሻ ካርዱን እየመዘዘ ነው። በነገራችን ላይ ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር ያጣላው ይህ ልዩ ኃይል ይፍረስ በማለቱ ነበር። በኋላ ላይ ከሌሎች ጄኔራሎች (ጄኔራል ሳሞራ የኑስ እና ጄኔራል አብረሃ ወልዳይ (ኩዋርተር) ጋር ተባብሮ ይህን ልዩ ኃይል በእጁ አስቀረው። አታ ጌታቸውና ጄነራሉም በዚህብመቃቃራቸው አልቀረም። አሁም ለዚያ ነው እንግዲህ ግማሽ እውነትን የሚይወራው። ምናልባት ምናልባት ደግሞ እነዚያ ጄነራሎችም የመጨረሻ ካርዳቸውን እየመዘዙ ነው። ማን ያውቃል?  አትርፉን እንትረፍ ወይ እንፈጃችኋለን ነው ነገሩ። መቼም ከትላንት ወዲያ የተጣላው አቶ ጌታቸው አሰፋ እንደገና አሁንም እያስገደደው አይመስለኝም።

አቶ አብዲ ሙሐመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ፣ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

በነገራችን ላይ አቶ ጌታቸው አሰፋ ግን አሁን እንኳን ውንጀላውን ለማስተባበል በግልጽ ለሕዝብ እጄ ንጹህብነው ለምን አይልም? አቶ ጌታቸው ግን የማይታየው መንፈስ ነው እንዴ አለ Leta Kenei Aga ሲጨንቀው።

እኔ ግን መንፈስ መኾኑን የምጠረጥረው አቶ በረከት ስምዖንን ነው፣ በአንዴ ብዙ ቦታ ይገኛል እየተባለ ነው (ኹኔትውን Omnipresence ይሉታል የነገረ መለኮት ምሁራን)።እኔ ጠረጠርኩ እንጂ በረከት ስምዖን Omnipresent ነው አላልኩም እንዳትወግሩኝ ፈሪሳውውያን በሕግ አምላክ። ለነገሩ ፈሪሳዊ ሕግም አምላክም አያውቅም።

፪. ኦሕዴድ የራሷን ቤት ንጽህና አታምንም…የአጋሮችዋን ቤትም እንዲሁ። የአብዲ ኡሌ ፓንዶራ ቦክስ ቢከፈት ኦህዴድና ስልታዊ አጋሯ ይተርፋሉ ወይ? ያ ቦክስ የነሱን “መክሊት” እንዳልያዘ ማን ያውቃል? 

በሌላ በኩል ደግሞ እውነተኛዋውን ጠላት (ከዚህ ጭፍጨፋ በስተጀርባ ያለውን ሥውር እጅ) ከገጠምኩ ባንተርፍስ የሚል ትንሽነት አለባት..መጸሓፉ ከአምላክ ጋር የሚዋጋ ይደቃል ይላል።ኦህዴድስ ከአፈጣሪዋ ጋር ጥሏ እስከመቼ ነው? ይህንን ያለመድቀቅ ነገር ፍርሃት ኦህዴድና ወንድም ጋሼዋ አሁንም የኀረሱት አይመስልም። በግዛታችን ለሚፈጠሩ ችግሮች ተጠያቂዎቹ እኛው እንጂ ፈጣሪያችን አይደለም…የቀድሞ አባቶችን አይሆንም እያሉ ተስምተዋል ኦህዴድና ወድንሟ። 

 አሁን ደግሞ የኦህዴድ  አበሳዋ ብዙ ነው…ቄሮ ወደ ድርጅት እየመጣ አይደለም፤ ዝቅተኛውና መካከለኛው ካድሬ አሀንም መሃይሙ፣ ሌባው እና ባለዝቅተኛ አፈጻጸሙ ሪፎርምን መረዳትም ሆነ መምራት/መመራት የማይችለው ለጥቅም አዳሪ ስብስብ ነው። በዚያ ላይ ደግሞ ሃገርን የመምራት፣ ተቋማዊ ለውጥን የማካሄድና ሃገርን ወደ ሰላም፣ ዴሞክራሲና ብልጽግና የማሸጋገር ፕሮጀክት እየመራች ነው። በኢሕአዴግ መርኅ እየሄደችም አይደለም። በዚህ ደግሞ ፈጣሪዋን ክፉኛ አስክፍታለች። ይህ ፈጣሪዋ ፈርጠም ያለ ነው። ስለዚህ በዚህ አቅሟ ፈጣሪዋን መግጠም ትችል ይሆን? የፈጣሪዋ የወደቁ መላዕክትስ በእጅ አዙር ቢላኩባት አበሳዋ አይከፋም ወይ? እንዳልተላኩባትም ማረጋገጫ የለም። ነቢይ አይደለሁ…የወደቁ መላዕክቱም፣ በሥልጣን ያሉትም እንዳይነግሩኝ እኔ የኦህዴድን ፈጣሪ አላመልክ…ማን ይነግረኛል። እንጃ ብቻ። 
በነገራችን ላይ የኦሮሞን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ተቀናቃኞችዋም እረፍት እየነሱኣት ነው…ምርጫውን አስባችሁታል?…ምፅ ምፅ።

፫. ሪፎርሙ ዋጋ ያስክፍላል…በተለይ የመከላከያና የደኅንነት። ብዙ ጊዜ ሁለቱን በአንዴ ሪፎርም ማድረግ አይመከርም። የመዋቅር ለውጥ ብቻ ስላልሆነ። በመከላከያ ሳይንስ reindoctrination ይሉት ጣጣ አላቸው። ይህ እንግዲህ የስልጣን ሽግሽጉን፣ የቅጥርና ሥልጠና፣ የማላመድ ሥራውን እና ላኮረፉት የሞራል ጥገና ማድረግን ሳይጨምር ነው። ሎጂስትክ፣ የጦር መሳሪያ አቅርቦት፣ የሥልጠና እና ሌሎች ረዲኤት አጋዝ/አጋር የመቀየር ነገርም ይኖራል። አብይን ዋጋ እያስከፈለና ጽጥታን እያናጋው ያለ ነገር ሁለቱን በአንዴ መጀመሩ (ለመጀመር ማሳወቁ) ነው። ይሄ ችግር ይከሰታል…ሕዝብ ዋጋ ይከፍላል፣ ይሄ ፖለቲካ ነው…የመረቀዘ ሥርዓትን ለመቀየር መዳዳትም ነው….ሁለት ከባባድ ሴክተሮችን ከሌላ ብዙ ሴክተር ጋር በአንድ ጊዜ ሪፎርም ለማድረግ መሞከር…ከባድ ዋጋ የሚያስክፍል ፕሮጀክት ነው…..አንዳንዴም ጀብድነት ነው። የአብይስ ከአቅም በላይ መሸከም ወይስ የጀግንነት ድፍረት? እኔ አላውቅም…ባውቅ ምን አስደበቀኝ…ፖለቲከኛ አይደለሁምና። ግን እንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ፤ ሃገር በአንድ ጊዜ ከአንባገነንነት ወደ ዴሞክራሲ እንደማትሻገር። በመሃል ኣናርኪ ይኖራል…ግድ ነው። በተለይ ደግሞ Silent coup d’etat ስታካሄድ ይብሳል። ሳይደፈርስ አይጠራም ይል የለ ጠቢቡ ሃገረ ሰብ?

ዋናው ጥንቃቄ አሁን የሚታየው ይህ ተፈጥሮኣዊ የሽግግር ጊዜ ክስተት ነው አልሞት ባይ ተጋዳዩ እውነትም አስፈሪ ነገር የያዘ ፓንዶራ ሳጥን ይዞ እያስፈራራ ነው የሚለውን መለየት ነው። ለፖለቲከኛው እና ለውስጥ አዋቂው ንገሩልኝማ። 

፬. መጨረሻ ግን የኔ ጥያቄ። በደቡብ ክልል የጸጥታ ችግር ሲኖር በፍጥነት በቴሌቪዥን የማረጋጋት መልዕክትን ያስተላለፈው በነጋታው በአውሮፕላን ሀዋሳ፣ ከዚያ ወላይታ ቀጥሎ ደግሞ ወልቂጤ የሄደው ትክክለኛ የአመራር ሥራን የሠራው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምነው ዝምታ መረጡ ሰሞኑን?  (በነገራችን ላይ በዚሁ 3 ቀናት ብቻ ከ50 በላይ ሰዎች ሞተዋል)። ዝምታው ትክክል አይመስለኝም። የጤና መኾኑም ያሳስበኛል።

 የክልሉ አመራርስ ፌስቡክ ላይ “Shira Diinaa” የምትለዋን mantra rant ከማድረግ ውጪ ዝም ጭጭ ብለዋል። ኦህዴድ ለራስሽ ስትዪ …..(ሊቀመንበሯ አብይንአህመድን ጨምሮ)። ህዝብ እብደሆነ መንግሥት ግልበጣን ተምሯልና ምሕረትሽ ከአሪያም አይመጣም። ፈጣሪሽ እንደኾነ ያንቺ እንጅ የሕዝብ አይደለምና እኛ እንዳንቺ አንፈራውም።

ግድያ ተፈጽሞ ምክንያቱን እና የገዳይ ማንነትን “እየመረመርን ነው ውጤቱን ጠብቁ” ብላችሁ የነገራችሁን እና እኛ የመዘገብናቸው ክስተቶች እንዳሉ አትርሱ። ጨለንቆ፣ አምቦ፣ ነቀምቴ፣ ሞያሌ…የትየለሌ። የሚያሳዝነው የሞያሌው “በስህተት” የተፈጸመው ግድያ ትጥቅ ፈቱ የተባሉት “ተሳስቶ ገዳዮች” በሕግ እንዳልተጠየቁ እናውቃለን። የጨለንቆውም እንደዚሁ። መዝግበናል ለማለት ነው።

ኦሮሚያን የሚያስተዳድረው ድርጅት አቅሙ ከተወዳጅነቱ በታች ነው። ሕዝቡ በእውነትኛው አምላክ ምሕረትና በጥቂት ሰዎች ጥረት እንደሚደገፍ እናውቃለን። ኢትዮጵያም እንዲሁ። ፓንዶራ ቦክሱን የያዙ ክፉዎችም ሆነ የድርጅቶቹ ፈጣሪ መቸም አፈር ልሶ ለመነሳት ጊዜው አልረፈደም። አቅሙም አለው። 

ኦህዴድ ሆይ ምን ይሻልሻል? 
የልጅ ምክር ትሰሚ እንደሆነ ሁለት ምክር ለግሼልሽ ነበር። ይሄን እና ይሄን ተጭነሽ አንብቢ።

~እና ምን ለማለት ነው? ፖለቲካሽን ከደማችን ዋጋ ጋር ተመን ውስጥ አታገቢ! ፓንዶራ ቦክስ ፍራቻ ሃገር አያስፈጁምና!

3 thoughts on “አብዲ ኢሌ፣ ኦሮሚያ እና የአብይ አህመድ ሪፎርም AND ITS PANDORA’S BOX

 1. እህህ አስከ መቼ?ትዕግስት ገደብ የለዉም?
  አሸባሪው ህወሃት (መነበብ ያለበት)
  ምንጭ -golgul
  ጸሃፊዉ-መስፍን ማሞ ተሰማ
  ሠኔ 2010 ዓ/ም (ጁን 2018)
  ሲድኒ አውስትራሊያ

  June 25, 2018 10:03 pm by Editor Leave a Comment
  “ዘረኛ ከሆንክ የዓለማችን ርካሽ ሰው አንተ ነህ” ሠኔ 16 ቀን (ዕለተ ትንሣኤ) 2010 ዓ/ም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድንና የባልደረቦቹን የለውጥ እርምጃ ለማመስገንና ለመደገፍ በሚሊዮን የሚቆጠረው ህዝብ በመስቀል አደባባይ ይዞ ከወጣቸው መልዕክቶች መካከል አንዱ።
  “…መግደል መሸነፍ ነው። መግደል መዋረድ ነው። በደስታ አንድ ሆኖ ሀገሬን የሚልን ህዝብ በራሱ ዜጋ ሠዎች አቅዶ አስቦ እንዲጨነግፍ መሥራት ትንሽነት ነው። ኢትዮጵያውያን ግን ትንሽ አይደለንም። ትልቅ ህዝቦች ነን። ከትንንሾች ጋር ወርደን ትንሽ አንሆንም። ይህንን ቀን ደስታችንን ለማጨለም፤ ፍቅራችንን ለማጨለም፤ አንድነታችንን ለማደፍረስ ያሰባችሁ ሃይሎች አልተሳካላችሁም።…ትላንት አልተሳካላችሁም። ዛሬ አልተሳካላችሁም። ነገም አይሳካላችሁም…” ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ ሠኔ 16/2010 ዓ/ም በእርሱና በባልደረቦቹ የተጀመረውን ለውጥ በማመስገንና በመደገፍ በመስቀል አደባባይ ለተገኘው በሚሊዮን ለሚቆጠር ህዝብ ንግግር ካደረገ በሁዋላ በአሸባሪዎች ከተሰነዘረበት የቦንብ ጥቃት ተርፎ በዛው ዕለት ለኢትዮጵያ ህዝብ ካስተላለፈው መልዕክት የተወሰደ።
  *****************************************************************************
  እናንተ ህወሃቶች በሞት ጣዕር ላይ የምትገኙ አሸባሪዎች ናችሁ። እናንተ የመደመርና የአብሮነት ሳይሆን የመቀናነስና የመገነጣጠል ሣጥናዔላዊ ልብና ደም የተገጠመላችሁ ዘረኞች ናችሁ። ቅድመ ግንቦት 83ን እንኳን ብንተው ከድህረ ግንቦት 83 እስከ ሠኔ 16/2010 ዓ/ም ከተከዜ በታች እስከ ሞያሌ ከጋምቤላ ጥግ እስከ ሀረር ቀንድ ስንትና ስንት ኢትዮጵያውያንን ፈጃችሁ?
  ስንትና ስንት እናቶችን ማቅ አስለበሳችሁ? ስንትና ስንት አባወራዎችን እንደወጡ አስቀራችሁ? ስንትና ስንት ህፃናትን ወላጅ አልባ አደረጋችሁ? ስንትና ስንት ወጣቶችን ገረፋችሁ? ጨለማ ቤት አኖራችሁ? አኮላሻችሁ? ደብዛቸውን አጠፋችሁ? የእናንተ የአሸባሪው ህወሃት ወንጀል እስከ ወዲያኛው ትውልድ ድረስ ገና ይፃፋል።
  ሀገርንና ህዝብን በመንግሥትነት ተደራጅቶ የሚሰርቅና የሚገድል በዓለም መንግሥታት ዘፍጥረት ታሪክ ከናንተ ከህወሃት ሌላ አልነበረም፤ የለም፤ አይኖርምም። ህወሃት ማለት የበቀል የርኩሰት የክፋት የጥፋት የሴራ የምቀኝነት የሌብነትና የዘረኝነት – መገለጫና ትርጉም ማለት ነው።
  እናንተ ህወሃት በተባለው የሽብር ‘ኢንኩቤተር’ የተቀፈቀፋችሁ ‘የጫጨ’ ህሊና ያላችሁ በሙሶሎኒ ፋሽስታዊ መንፈስ የምትኖሩ የክፍለ ዘመኑ ዘረኞችና ክፉ ሰዎች ናችሁ። በህወሃታዊው አብዮታዊ ዲሞክራሲ የተለከፉት ህወሃት ያልሆኑ ህወሃታውያን ደግሞ የዘራፊዎችና የሌቦች የገዳዮችና የሽብርተኞች ቅጥረኞችና አገልጋዮች ናቸው። በደቡብ፤ በጋምቤላ፤ በቤንሻንጉል ጉምዝ፤ በኦሮምያ፤ በሶማሊ፤ በሐረሪ፤ በአፋር፤ በአማራ ህዝብ መኻል የተተከሉ የኢትዮጵያ አረሞች። አረሞቹን ስንመነግልና ከስራቸው ስንነቅል እናንተ – ህወሃት እንደ ስብስብ ትመክናላችሁ። የእናንተ የህወሃት መምከን ደግሞ ለኢትዮጵያ ሠላምንና ፍቅርን፤ አብሮነትንና መደመርን ያሰፍናል፤ ኢትዮጵያዊነትን ያነግሣል!!
  እናንተ ለኢትዮጵያ ውጋት እንጂ ትንፋሽ አይደላችሁም። እናንተ ኢትዮጵያዊነት ሲዘመር ኢትዮጵያዊነት ከፍ ሲል ዛራችሁ ይነሳል። ታብዳላችሁ። ደም ይናፍቃችዃል። ኢትዮጵያ ለእናንተ – ለህወሃት – ላሜ ቦራ እንጂ እናት ሀገር አይደለችም። ስታልቧትና ስታደርቋት እርካታንና ሣጥናዔላው ሀሴትን ታገኛላችሁና። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሲደሰቱና ሲደመሩ ደምስሮቻችሁ ይቆማሉ፤ ዓይኖቻችሁ ይቀላሉ፤ እጆቻችሁ ይገድላሉ።
  ደደቢት ላይ በልባችሁ የተተከለው የርኩሰት ደዌ በዘመን ሂደት እየመዘመዘ እነሆ ከመቃብራችሁ አፋፍ ደርሳችሗል፤ በጣዕረ ሞት ተይዛችሗል። እርግጥ ነው መቃብራችሁ ከተቆፈረ ሰንብቷል። የተጠናቀቀው ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም የጆሮዎቻችሁን ታንቡሮች በታትኖ በትናንሽ ጭንቅላቶቻችሁ ውስጥ እንደ ነጎድጓድ ባስተጋባው የኢትዮጵያዊነት ደወል ነበር፤ እኛ ስንኖር ኢትዮጵያውያን ስንሞት ኢትዮጵያ እንሆናለን – በሚለው በአእላፍ ኢትዮጵያውያን መሥዋዕትነትና በአብይ ፆም ፀሎት ባገኘነው ሙሴያችን አብይ መሪያችን አንደበት በምክር ቤት አዳራሽ ሲያስተጋባ!!
  ከዚህ ወቅት ጀምሮ ለየላችሁ። ትንሽነታችሁ ይበልጥ አነሰ። ድውይ አስተሳሰባችሁ ይበልጥ ድውይ ሆነ። ጡረተኛና አኩራፊ ደደቢቶች ከነምልምል ሎሌዎቻችሁ ተጠራርታችሁ መቀሌ ላይ ለሙሾና ለሴራ ተቀመጣችሁ።
  ገዳዮች ሌቦችና ሀገር ሻጮች ሁላ አብይ መሲሃችንን አብይ መሪያችንን አብይ ሙሴያችንን ለመግደል ስትዶልቱ ከረማችሁ። የከንቱዎች ስብስብ ከንቱ ሴራ! አብይን ገድላችሁ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማንን ልትሾሙብን ነበር የዶለታችሁት? ያሰባችሁት ሆኖ ቢሆን ኖሮ ግን ማዕበሉ መቀሌ በምን ቅፅበት እንደደረሰ ሳታውቁት ይጠራርጋችሁ ነበር!!!
  ሠኔ 16 ቀን 2010 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ አብያችንን ለመግደል የወረወራችሁት/ያስወረወራችሁት ቦንብ ስለምን እንደከሸፈ ታውቃላችሁ? ዕለቱ ከመሲሁ አብያችን ጎን ቆመን ለኢትዮጵያ ትንሳዔ ቃል የገባንበትና የምህረትም ኪዳን ያደረግንበት ቀን በመሆኑ – ዕለተ ኪዳነ ምህረት! የኢትዮጵያ አምላክ በኢትዮጵያ ሠማይ ላይ የሠፈነበት ዕለት በመሆኑ። የርኩሳንን እና የክፉ ሰዎችን ጦር ማምከኛው ቀን በመሆኑ! ሕዝቤን ልቀቁት ያለው ሙሴያችን አብይ የዕለቱን ምስባክ ሲጀምርልን ‘ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ይባርክ’ በማለቱ። ይኸው ነው ምሥጢሩ፤ የፈጣሪ ተዓምሩ፤ የአብይ መዳን ትርጉሙ፤ የኢትዮጵያ ትንሳዔ ይፋ የመሆኑ!!
  እንግዲህ የደደቢት ህወሃትና አሸርጋጆቹ ህወሃታውያን ሁሉ እነሆ ለመጨረሻ ጊዜ ይህንን እንነግራችሗለን። ከዚህ ወዲህ የመቃብር ስፍራ የማግኘታችሁን ነገር ተጨነቁበት እንጂ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የመግዣና የመግደያ ጊዜያችሁ ማክተሙን እወቁ!!! የገዳዩና የዘራፊው የዘረኛውና የከፋፋዩ የሌባውና የሀገር ሻጩ የህወሃት የበላይነትና የአምባገነንነት ዘመን ከእንግዲህ አይመለስም!! በእናንተው ጣልያናዊ ቋንቋ…አዲዮስ!!!
  እኛ ግን፤
  ሠኔ 16 በሞታችንና በደማችን ሙሴያችንን አብይን ታድገናል።
  ሠኔ 16 በሞታችንና በደማችን የኢትዮጵያን ትንሳኤ በአደባባይ አብስረናል።
  ሠኔ 16 በሞታችንና በደማችን የእናንተን የህወሃትንና ህወሃታውያንን ትንሽነትን እኩይነትንና ሽንፈትን አሳይተናል። መጪው ዘመን የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን የፍቅር የሠላም የመደመር የይቅርታና የትንሣኤ ዘመን መሆኑን እነሆ ከአብይ መሪያችን ጋር ሆነን አውጀናል።
  አብያችን ሆይ! የኢትዮጵያ አምላክ እንኳንም ለሀገርህ ለኢትዮጵያ ለህዝብህ ለኢትዮጵያውያን ለልጆችህ ለባለቤትህና ለወዳጅ ቤተሰቦችህ ሲል ከቀን ጅቦች መንጋጋ አተረፈህ!
  እናንት በአብያችን ዙሪያ ወገባችሁን አጥብቃችሁ ነገን በመደመር አብያዊ ራዕይ ደፋ ቀና የምትሉ የለውጡ አጋሮችና አራማጆች ከእንግዲህ በንቃትና በብቃት ራሳችሁንም ሆነ አብያችንን ከሚታወቁም ሆነ ከተደበቁ የቀን ጅቦች ጠብቁልን! ከእናንተ አንዱስ ስንኳ ቢጎድል ኢትዮጵያን ትጎዳላችሁና። እናንት በተለይ ከአብያችን ጎን የቆማችሁ የኢትዮጵያ የቁርጥ ወቅት የለውጥ አራማጆች በአብይ መትረፍ እንኳን ደስ አላችሁ! ከእንግዲህ አትዘናጉ፤ ተጠንቀቁ፤ የቀን ጅቦቹንም መንጥሩ!!!
  እናንት በደማችሁና በህይወታችሁ ለኛና ለኢትዮጵያ ትንሳዔ መሥዋዕትነት የከፈላችሁ የሠኔ 16 የመስቀል አደባባይ ሠማዕታት ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ሠማይ ላይ እንደሚያበሩት ከዋክብት ትሆናላችሁ! በትውልድ ሁሉ ስትዘከሩም ትኖራላችሁ!
  የተሰዉትን ፈጣሪ ነፍሳቸውን ከገነት ያኑርልን!
  መፅናናት ለተጎዱትና ለመላው ቤተሰብ ሁሉ ይሁን!
  ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ይባርክ!
  ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር
  መስፍን ማሞ ተሰማ
  ሠኔ 2010 ዓ/ም (ጁን 2018)
  ሲድኒ አውስትራሊያ
  mmtessema@gmail.com
  ፎቶ፤ የህወሓት ነፍሰበላ የበረሃ ወንበዴ አዲስ አበባን በተቆጣጠረ ወቅት ሜክሲኮ አደባባይ ላይ አንድ ኢትዮጵዊን በጠራራ ፀሐይ ገድሎ

  Like

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡