ወደ አስመራ የሚወስዱት መንገዶች ይፋ ሆኑ

ወደ አስመራ የሚወስዱት መንገዶች ይፋ ሆኑ

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን መነሻቸውን አዲስ አበባ በማድረግ ወደ አስመራ የሚወስዱ አራት የመኪና መስመሮች ይፋ ማድረጉን የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሳምሶን ወንድሙ አስታወቁ፡፡

የመጀመሪያው መንገድ መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ በአዲግራት እና በዛላምበሳ ዘልቆ አስመራ የሚደርሰው መንገድ 933 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲሆን፥ በአስፓልት ኮንክሪት ደረጃ የተገነባ ነው፤ ይህ መስመር ሙሉ ለሙሉ አግልግሎት መስጠትም ይችላል ብለዋል የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ሳምሶን ወንድሙ፡፡

ሁለተኛው አማራጭ መስመር ከአዲስ ከአበባ ተነስቶ በመቀሌ፣ በአድዋ፣ በራማ፣ በመረብ አድርጎ ወደ አስመራ የሚያቀናው 1005 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲሆን፥ ከአዲስ አበባ አድዋ ያለው መንገድ በአስፓልት ደረጃ ተሰርቷል፤ ቀሪው ከአድዋ እስከ መረብ ያለው በ2012 ይጠናቀቃል ብለዋል፡
ሦስተኛው ከአዲስ አበባ ተነስቶ ጎንደር ሁመራ የሚዘልቀው 991 ኪሎሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን፥ ሙሉ ለሙሉ በአስፓል የተሸፈነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አራተኛው መዳረሻ ደግሞ መነሻውን አዲስ አበባ በማድረግ በአዋሽ አርባ እና በዴቼቶ አቅንቶ በቡሬ በኩል አሰብ የሚደርስ ነው፤ ይህ መስመር 876 ኪሎሜትር ርዝመት ይሸፍናል፡፡

በአራተኛው መስመር ከአዲስ አበባ ተነስቶ እስከ ዴቼቱ ያለው 659 ኪሎሜትር ሙሉ አገልግሎት መስጠት ይችላል፤ አሁንም ቢሆን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ያሉ ሲሆን፥ ከዚያ በኃላ ያለው መስመር ትንሽ የማስተካከል ስራዎችን የሚጠይቁ ናቸው ብለዋል፡፡

የአራቱን አቅጣጫዎች የመንገድ ደህንነት ለመፈተሸ አስፈላጊውን መረጃ ለመሰብሰብ የባለስልጣኑ ሰራተኞች ምልከታ ማድረጋቸውን አንስተው ከአራቱ መካከል የሦስቱ ይዞታ ተሸከርካሪን ማስተናገድ የሚችሉ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይ አዋጭነታቸው እየታየ ሌሎች አማራጭ መንገዶች ሊከፈቱ እንደሚችሉም አቶ ሳምሶን ወንድሙ ገልጸዋል፡፡


Source: FBC

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.