አርበኞች ግንቦት ሰባት ከመንግስት ጋር ስምምነት ላይ ደረሰ

የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በአሜሪካ ባደረጉት ሁለት ዙር ዝግ ውይይት ወደ ሀገር ቤት ተመልሰው በሰላማዊ መንገድ በፖለቲካ የሚሳተፉበት ሁኔታ ላይ መስማማታቸው ተሰማ።

አርብ ዕኩለ ለሊት አቅራቢያ በተጠናቀቀው ውይይት ላይ በኤርትራ ያሉ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮችን በተመለከት እንዲሁም ሀገሪቱ ወደ ፊት ወደ ዴሞክራሲ ሽግግር ለማድረግ በሚረዷት ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን በስብሰባው የተካፈሉ ምንጮች ነግረውናል። በቅርቡም ድርጅቱ በኢትዮጵያ በይፋ እንቅስቃሴ እንደሚጀምር ይጠበቃል።

በጉዳዩ ላይ ድርጅቱ ዝርዝር መግለጫ እንደሚያወጣ ይጠበቃል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ቀድሞ በሀገር ቤት በህቡዕ ይንቀሳቀሱ የነበሩ አባላቱን ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የማምጣትና የማደራጀት ዕቅድ እንዳለውም ከድርጅቱ የተገኘ መረጃ ያመለክታል። የድርጅቱ ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሐሙስ እለት ከሚኖሩበት እንግሊዝ ወደ አሜሪካ የመጡ ሲሆን በውይይቱ ላይ ተሳታፊ ነበሩ።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራዲዮ

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.