የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር ዋለ!

አብዲ ሞሃመድ ኡመር ትናንት ከክልሉ ፕሬዚዳንትነታቸው መነሳታቸው ቢገለጽም የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪ ሆነው ይቀጥላሉ ተብሎ ነበር።

የቀድሞው የክልሉ ፕሬዝዳንት በመከላከያ ሠራዊት አባላት በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ከተደረጉ በኋላ ጅግጅጋ ከሚገኘው ቤተ መንግሥት እንደተወሰዱ ምንጮች ለቢቢሲ ሶማልኛ ገልጸዋል።

የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕረዜዳንት አብዲ ኢሌ

ከቅዳሜ አንስቶ በጂግጂጋ እና በክልሉ ሌሎች ከተሞች የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ የሃገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ወደ ክልሉ ገብቶ ሰላም እንዲያስከብር መታዘዙ የታወሳል።

አህመድ አብዲ ሞሃመድ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት በመተካት መሾማቸውም ይታወሳል።

አዲሱ የክልሉ ፕሬዚዳንት አህመድ አብዲ ሞሃመድ የሶማሌ ክልል ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ በመሆን አገልግለዋል።

አህመድ አብዲ ሞሃመድ ከቢቢሲ ሶማልኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ስልጣናቸውን አስረክበው በሰላም የስልጣን ሽግግር መካሄዱን ተናግረው ነበር።

አህመድ አብዲ ሞሃመድ ”አብዲ ሞሃመድ ሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ የክልሉ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዲስ መሪ መርጧል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ጂግጂጋ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እየኖሩ ይገኛሉ” ሲሉም ትናንት ተናግረው ነበር።

ምንጭ፦ BBC|አማርኛ

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.