ትዝታ የኋሊት ፤ “ከጉዞ ማስታወሻ ወደ ዛላምበሳ” የተቀነጨበ

ማድነቄ አይድነቃችሁ፣ አለማድነቃችሁን ግን አደንቃለሁ!

(Why I had tears of smile over the Ethio-Eritrea resolution in Zalambesa)

እንደ ሄኖክ ያሬድ በጥበብ ከሽኜ ስለማላቀርብላችሁና በግርድፍ ቃላት ስለማስቸግራችሁ ይቅርታ ብል አልከፋም።

ወደ ገደለው ስገባ ዛላምበሳን የማውቃት በኢትዮ-ኤርትራ በነበረው የጦርነት ምስል አይደለም፤ ታጋዩ ወንድሜን ለማየት ሂጄም አይደለም፤ ብቻ ምን አለፋችሁ ዛላምበሳን የማውቃት ህዝቧንና እሷን ለማየት በመስከረም 15, 2009 ዓ.ም. ከአንድ የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ጓደኛየ  ጋር ባደረግነው ጉዞ ነበር፤ ጓደኛ ይዞ ጉዞ እንዲሉት።


ወደ ዛላምበሳ ከመግባታችን  በፊት በነበረው የፍተሻ ጣቢያ ስንፈተሽ የነበረው ስጋት ለመረዳት አልተቸገርንም። በዚህ ሁኔታ አልፈን ከተማው ስንገባ ልክ አንድ ትልቅ የፈረሰ ግንብ ከአስፋልቱ ወደ ግራ አየንና ሁለታችንም ባንድ ድምፅ “ምንድነው?” አልን። በኛ መምጣት ተስፋም ስጋትም ይነበብቸው የነበሩ የአከባቢው ነዋሪዎች ህንፃው የከተማዋ የድሮ  እንቅስቃሴ ሃወልት የሆነ የዱቄት ፋብሪካ የነበረ ግን በሰው ሰራሽ ጦርነት ፋብሪካው ራሱ ዱቄት ሁኖ የቀረ እንደሆነ ነገሩን።


ያሳዝናል ፩!

ከመኪና ወርደን ከወታደሮቻችን ጋር ተጫውተን ወደ ጨዋው ህዝብ አመራን። በነገራችን ላይ የሁለቱን ሃገራት የጦር ሠራዊት በ300 ሜትር ገድማ ርቀት ትይዩ እንደነበሩ ልብ ይሏል።መሬቱ አንድ ግን በሰው ሰራሽ የጦር ኬላ የታጠረ ፣ይህን እለፍ ይህን አትለፍ የምትባልበት፣በህዝቦቹ መካከል የጨርቅ ልዩነት ብቻ የምታስተውልበት  አንድነትን የገረሰሰ ሰው አመጣሽ ልዩነት ሁናቴ ነበር።መሬቱ ፣ሳሩ፣ተክሉ፣ሰው አንድ ግን በግድ የተለየ።

“Don’t tell how deep an ocean is until you step in unless you are a sonics “ይሉታል እንዲህ ነው…

ሁለት የሥጋ እህተማማቾች (ከግራ ወደ ቀኝ
ኤርትራዊት እና ኢትዮጵያዊት) በሁለቱ ሃገራት የጦር ሠራዊት አባላት በእርቅ ምክንያት ተገናኝተው ሲተቃቀፉ

ያሳዝናል ፪!


ፎቶ ለቅመን በአቅምቴ ያዳበርናት የመግባቢያ ክህሎት ተጠቅመን ፊታችን ወደህዝብ አቅንተን ከልጅነታቸውን በስጋት የሚኖሩ ልጆችና ጥቂት እናቶች ጋር በመሆን ወዳንዲት እናት ቤት ጎራ አልን። በባህላችን ለእንግዳ ያለን ቦታ ባውቅም የነሱን ያህል ግን አላየሁም፦ ለዛም ስጋትም ተስፋም ሰንቆ በመንታ ሃሳብ የተጠመዱ ሰዎች፤ ዛሬ ተተኮሰ ፣ነገ ሞትን ብሎ የሚኖሩት ሰዎች፣ እኛን ነጭ ልብስ በማድረጋችን የሚሰጣቸው እርዳታ እንዲሻሻል ተስፋ ያደረጉ ሰዎች ።

ጥሕሎ በልተን፣ ቡና ፉት ብለን፣ ጠጅ እየጠጣን ሐኪሞች መሆናችንን በመንገር ያሉበትን ሁኔታ እንድያጫውቱን ጠየቅኳቸው ።

ብዙ ዝርዝር ቢሆንም እንዲመች በዚህ አጠቃልለዋለሁ፦
እኛ እየኖርን የምንሞት መስሎን በእየእለቱ በጥርጣሬ ውስጥ እንድንኖር የተደረግን ሚስኪን ነን። እድለኛ የሆነ አንዳንዱ ሰው ልጆቹ ከጦርነት ተርፈው ሌላ የስደት ጦርነት አሸንፈው አረብ ሃገር ሂደው ከተሳካላቸው ይህን ትተው የተሻለ ኑሮ ወይም እዚህም ሁነው የሚረዱ አሉ። አብዛኛዎቻችን የምንኖረው ግን መንግሥት ለአንድ ሰው በወር 15ኪሎ በሚሰጣት ስንዴና ዘይት ነው። ሥራ መሥራት ሃብት ማፍራት ቀርቶ በጎረቤት ኮሽታ ስንሰማ ራሱ አሁን አለቀልን ብለን እዮሞትን እየዳንን ይኸው ከ15 አመት በላይ ሆነን” የሚል ሆድን የሚበላ ነበር።


ያሳዝናል ፫!

እኛም Khalil Gibran እንዳለው “I have nothing to give you except tears;will you be nourished on tears instead of milk?” ትዝ ብሎንና ምንም ልናግዛቸው ባለመቻላችን እያሰብን ተመለስን።


ዛሬ ቀኑ ተቀይሮ ያ ስጋትና ፍርሃት ወደ ደስታና ፍቅር በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አመራርና ኃላፊነት አንድ ሕዝብ በፍቅር ሲያለቅስ አየን። ያኔ ካለቀስነው እንባ የትናንቱ የደስታ እንባ (tears of smile) ይበዛልና አብይ አህመድን ማድነቄን እንዴት ይደንቃል? እንዴት የናንተን አለማድነቅ ግን አይደንቅም?

I know the French saying, “don’t say the day was good until the sun sets.“ይህ ግን የትናንቱን ደስታ ማንም አይቀንስም ይልቅኑ ሕዝቡ እንዲናገር መፍቀድ እንዳለብን ተምረናል።


ይህን ተከትሎ ዛሬ በዓዲግራት ከተማ ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ ስታዩ ያጣነው  ሰላም ብቻውን እንዳልነበር ማወቅ ይቻላል ።

ሕዝብና እውቀት የማይሻገረው ግንብ የለምና የጉድጓድን ጥልቀት በጉድጓድ ውስጥ ለሚኖረዉ ሕዝብ እናውቅልሃለን ባንለው መልዕክቴ ነው…ሰላሙን ዘላቂ ያድርገው ምኞቴ ነው።

በብዕር ሥሜ Pro Ethiopia ነኝ።

 ቸር ሰንብቱ!

One thought on “ትዝታ የኋሊት ፤ “ከጉዞ ማስታወሻ ወደ ዛላምበሳ” የተቀነጨበ

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡