የመንጋ ፍትሕ እና ጥላቻን የተሞላው “የውግዘት” ዘመቻ፦ የቡራዩ ጉዳይ

ከሁሉም በፊት የተፈጠረውን ግድያ እና ማፈናቀል አጥብቄ እቃወማለሁ! ይሄንን የሚፈፅም አካል የኢትዮጵያ ጠላት እንጅ ወዳጅ አይደለም።
አብዮታዊው (አብዮተኛው) ወጣት የፖለቲካ ጥቅም ፈላጊ ሰዎች ሰለባ እየሆኑ ይመስላል።

አፋኙን ሥርዓት ፊት ለፊት የገጠመው ወጣት በቀውጢው ሰዓት ከዛሬ በተሻለ ዲሲፕሊን ሰላማዊ ቅዋሜ ሲያካሄድ ነበር።

አሁን የሚታየው ሁኔታ ግልጽ ለማድረግ ያህል

የደቦ ፍርድ እና ብሔርን መሠረት ያደረገ ጥቃት፣ ግድያ፣ ዝርፊያ በተለያዩ ቦታዎች ይስተዋላል።

፩. በለውጥ ጊዜ የሚፈጠሩ ክፍተቶች የሕግ ማስከበሪያ አካላት ክፍተት፣ አልፎም ተርፎም በነዚህ አካላት ለረጅም ጊዜያት ተቋማዊ ተዓማኒነት ማጣት።

ይሄንን ቄሮ፣ ፋኖ፣ ዘርማ ብቻ ሳይሆን እኛ በዚሁ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያለን አንዛኞቻችን የምናሳየው ነገር ነው። ለምሳሌ፦ የእንጅነር ስመኘው በቀለን አሟሟት የፖሊስ ምርመራ ውጤት በፌዴራል ፖሊስ ሲቀርብ ምንል እንኳን ምንም መረጃ ባይኖረን አልተቀበልነውም…ምክንያቱም ፖሊስን ያለማመን ባህል አለን። የራሳችንን መላምት አስቀመጥን…አንዳንዶቻን ሥም እየጠራን። ይህ የመንጋ ፍርድ ነው። በነገራችን ላይ ወንጀልም ነበር…ያው ታለፍን።

ይሄ ማለት ተዓማኒ ናቸው ለማለት አይደለም…ከሁለት ቀናት በፊት እዚሁ አዲስ አበባ ላይ አንድ ዜጋ በፌዴራል ፖሊስ ተገድሏል።

ወጣቱም ጥቅሜ፣ ክብሬ፣ ማንነቴ ተነካ ብሎ ሲያምን በፖሊስ ወይም በሕግ ከመዳኘት ውጪ ልክ እኛ እንደምናረገው (በጅምላ ብሔርን እና ሙሉ የሕብረተሰብ ክፍል እንደምንፈርጀው) አካላዊ እርመጃ ይወስዳል። ይሄ ቄሮ ወይም ፋኖ በገሃድ ፈፀሙት እንጅ ሁላችንም ፍረጃውን ተያይዘንዋል።

፪. ይሄ አብዮታዊ (አብዮተኛ) ወጣት ኃላፊነት በማይሰማቸው እየተመሩ ነው። በማይገስፁኣቸው፣ በማይመክሩኣቸው ሰዎች እየተመሩ ጥፋት ሲያጠፉ ይታያል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በሚያሳዝን መልኩ የጥላቻ ዒላማ ተደርገው ፕሮፓጋንዳ እና ጥቃት እየተፈፀመናቸው ይገኛል። ስድብ፣ ማንቋሸሽ እና አንዳንዴም የአካላዊ ጥቃት ዒላማ ተደርገው እየተዘመተባቸው ውጣቶቹ ፅንፈኝነትን (extremism) DEVELOP እያደረጉ እየመጡ ነው። አክቲቪስት ይሁን፣ ምሁር ይሁን፣ ፖለቲከኛ ካድሬ ይሁን ወይም ዝም ብሎ ወረኛ የጥላቻ ዘሪ ይሁን ምኑም በማይታወቅ ወመኔ ልክ ወጣቱ ብሔርን ለይቶ እንደሚያጠቃ ይሄኛውም አደገኛ ስድ አድግ ብሔርን ለይቶ ይሳደባል፣ ይሳለቃል። ምንድር ነው አላማው? ምንድር ነው ልዩነቱ? ለኔ ምንም ነው።

በሌላ በኩል መንግሥት ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጪ እስኪሆኑ ድረስ አላስፈላጊ ግርግሮችን ማስተናገድ አልነበረበትም። ከዚህ በፊትም ተናግሬያለሁ። የድጋፍ ሰልፎች አላስፈላጊ አንደነበሩ የፖለቲካ ፓርቲ ሃገር ሲገባ እጅግ የተጋነነ የአቀባበ ሥነ ሥርዓት ማደረግ (መፍቀድ) አላስፈላጊ ነው። ምንድነው ጥቅሙ? ምንም!

የፀጥታ ችግሮች ሱከሰቱ ችላ የማለት ሁኔታ እንዳለም ይታዘባል።

የሚዲያ ነፃ አለመሆን አሁንም ትክክለኛውን መረጃ በጊዜ ያለማግኘት፣ በተቃራኒው የማንም ጥቅመኛ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ የሚነዛው ወሬ ላይ እንድንደገፍ ያስገድደናል።

እንደመፍትሔ የማስበው መንግሥት ሕግ ማስከበር፣ ሚዲያን ይበልጥ ነፃ ማድረግ፣ አላስፈላጊ ዝግጅቶችን እና ግርግሮችን ማስቆም።

ሌላው ወሳኝ ነገር ይሄ አብዮተኛ ወጣት ሕጋዊ ማዕቀፍ በተበጀለት መደራጀት እና ሥራ ሊፈጠርለት ይገባል።

በዚህ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ጥላቻን የምትሰብኩ ብታቆሙ ምለካም ነው። የተፈጠሩትን ችግሮች ለፕሮፓጋንዳ ባትጠቀሙ ጥሩ ነው። ዘመቻው ማንንም አይጠቅምም።

በተለይ በተለይ ሰዎች በገንዘብ ተደልለው ችግር እየፈጠሩ ባለበት ሁኔታ ፍረጃችንን በልክ ብናረገው አግባብ ነው።

አንዳንድ ወገኖች የተጎጁው ሕመም ሳይሆን ስለሱ በማውራት እና በመንዛት የሚያገኙት ርካሽ የፕሮፓጋንዳ ጥቅም ጥቅም ብቻ የሳባቸው ይመስላል። ጥፋተኛ ቡድን እና ግለሰብ በሕግ አግበብ መቀጣት እንዳለበት የማምነውን ያህል አጋጣሚውን ተጠቅመው ረጅም ጊዜ የቆየውን የጥላቻ ሰይፋቸውን የሚመዙትንም እቃወማለሁ። Collective character assasination helps no one in this nation. It is very clear that some groups have alreay been on the hate campaign for so long now, making the themselves the castodians of the Ethiopian sentiment when in reality they have a longstanding hate and mistrust towards the group they despise. This is by no means to justify the herroundous act of violence, rather to clarify between the victim and the hypocrite. We all have to campaign to address the basoc needs of the victims, and push the government to uphold the rule of law.

የተፈጠረውን ግዲያ፣ ዝርፊያ እና ማፈናቀል አጥቅብቄ እንደምቃወመው በድጋሜ ለመግለጭ እፈልጋለሁ!