ፓለቲካችን በዛቻ እና ማስፈራሪያዎች እየተወጠረ ነው!

By Yared Hailemariam

ተራው የኛ ነው እያሉ ያሉት አክራሪ ልሂቃን እና የብሄር ድርጅቶች ሕዝብን፣ ሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶችን፣ መገናኛ ብዙሃንን፣ ጋዜጠኞችን እና መንግስትን ጭምር ከወዲሁ ማስፈራራት ጀምረዋል። የዛሬው የአምስቱ ድርጅቶች መግለጫ፣ ቀደም ብሎ አክራሪ ግለሰቦች ይሰጧቸው ከነበሩት ማስጠንቀቂያና ዛቻዎች የተለየ አይደለም። በዚህ አካሄድ የት ይደረስ ይሆን?

እኔን የሚያሳስበኝ በመግለጫው ላይ የተነሱት የመብት ይሁን የጥቅም ጥያቄዎች አይደሉም። እጅግ አሳሳቢው ነገር የዘረዘሩዋቸውን የጥቅም እና የመብት ጥያቄዎች ለማስጠበቅ እየሄዱበት ያለው መንገድ ነው። ያነሱት የአዲስ አበባ ባለቤትነት፣ የፌደራሊዝም እና ሌሎች የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና የፖለቲካ ጥቅሞችን ለማስፈጸም እንደ አንድ ተወዳዳሪ ፓርቲ በምርጫ ሂደት ውስጥ ተወዳድረን ስናሸንፍ እናስፈጽማልቸዋለን አይደለም እያሉ ያሉት። እንዲያ ቢሆንማ ምን ገዶን ቅር ይለናል። እዳው ለመራጩ ሕዝብ እና በምርጫው ለሚወዳደሩት ሌሎች ተፎካካሪ ድርጅቶች ይሆን ነበር።

እየተባለ ያለው ግን ወደድክም፤ ጠላህ፣ ወደፊት በሚካሄደው ምርጫ ተመረጥንም፣ አልተመረጥንም እነዚህ ጥቅሞቻችን እና መብቶቻችንን የኢትዮጵያን ሕዝብ አፍንጫውን ይዘንም ቢሆን እናስከብራለን ነው። ይህ አካሄድ ኢዲሞክራሲያዊ ከመሆኑም ባሻገር የወደፊቱን ምርጫ አስፈላጊነት ከወዲሁ ጥያቄ ውስጥ የከተተ እና እነሱ የፈለጉት ካልሆነም ወደ ኃይል እርምጃ እንደሚገቡ ያመላከተ ነው።

በአዲስ አበባ ውስጥ በኦሮሞ ትምህርት ቤቶች፣ ተቋማት እና ከክልሉ በመጡ ሰዎች ላይ የተደረገውን ሕገ ወጥ ነገር ማውገዝ ይገባል። እሱን እኛም እናወግዛለን። አጥፊዎቹም በሕግ አግባቢ ሊጠየቁ ይገባል። እደግመዋለሁ በሕግ አግባብ። ወታደራዊ ካምፕ ሰዎችን ማጎርን አይጨምርም። ነገር ግን ያንን ክስተት ሽፋን አድርጎ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ እየተሰነዘረ ያለው ዛቻ እና ማስፈራሪያ ግን ለከት እያጣ እየመጣ ነው። አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነች። በከተማው ውስጥ የመኖር እጣ ፈንታህ በእኛ እጅ ነው የሚመስል ማስጠንቀቂያ ሌላ የፖለቲካም ሆነ የጸጥት መዘዝ እንዳለው ልትረዱት ይገባል።

ለማንኛውም እያየን እና እየታዘብን ያለነው ነገር ይች አገር ወዴት እየሄደች ነው የሚል ጥያቄ እንድናነሳ ግድ ይለናል። እነ ዶ/ር አብይ እና ቲም ለማም የገቡበት ፈተና ቀላል አይመስልም። ሕዝብ ከጎናቸው ሊቆም ይገባል። እነሱም ተስፋ ለሰጡት እና ቃል ለገቡለት ሕዝብ በጽናት ከፊቱ እንዲቆሙ እግዚያብሔር ብርታቱን ይስጣቸው።

አቶ ያሬድ ሃይለማሪያም፥ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች
Advertisements

2 thoughts on “ፓለቲካችን በዛቻ እና ማስፈራሪያዎች እየተወጠረ ነው!

  1. This is so stupid and derogative article. Everyone have optimistic face and you are running to demolish this. Do not be a by product of the Meles regime. Think out of that framework. I heard what they said and there is good part and bad. But the way you are try to wrote is very derogative. there is always a challenge when destination is heaven so i take it as challenge nothing more. Ethiopian-ism n peace first.

    Like

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.