“የፀረ አብዮት እንቅስቃሴ” (COUNTER REVOLUTION) እና የዘር እልቂት አደጋ በኢትዮጵያ

እየተከሰተ ያለው ግጭት፣ ጥቃት እና መፈናቀል ” “የፀረ አብዮት እንቅስቃሴ (COUNTER REVOLUTION) ይመስላል። GENOCIDE እንዳያስከትል አፈራለሁ። 

የሀገራት ታሪክ ሥር ነቀል ለውጥ የፖለቲካ እና  ኢኮኖሚ ለውጦች ሲከሰቱ በግጭቶች መታጀቡ ያለ ነገር ነው። በተለይ ድግሞ ከAUTHORITARIAN ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ ለውጥ ውስጥ የኃይል አሰላለፍ ተስተካክሎ  የሕግ የበላይነት እስኪረጋገጥ፣ ተቋማት እስኪቋቋሙ እና ሕጎች እስኪሻሻሉ እንዲሁም ወይ በምርጫ ወይም በሌላ ሥልት የለውጡ መሪ ሥልጣኑን እስኪያደላድል የተለያዩ ኃይሎች በለውጡ ተቃራኒ መቆማቸው አይቀሬ ነው። ፍላጎታቸው አንዳንዴ ይሠምርና ግጭቶቹ ፍሬ አፍርተው መጠነኛ ጉዳት ከማስከተል እስከ ለውጡ ቅልበሳ የሚደርስ “ትግል” ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህ ነገር “Counter Revolution” ይባላል። 


ይህ ቃል አጠቃቀም ራሱ ብዙ ጉዳቶች ሲያስከትል በኛ ሀገር ታሪክም የምናውቀው ቢሆንም የተሻለ ቃል ስላላገኘሁ ከይቅርታ ጋር ልጠቀመው፥ተረዱልኝ። 


የፈረንሳይ አብዮት ፈንድቶ የካኅናትን እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥልጣን የሚደግፉ ፖሊሲዎች ተሽረው በሌላ ሲተኩ እንዲሁም ንጉሥ ሉዊሥ 16ኛ ሲገደሉ ቬንዴ በምታባል ግዛት የካቶሊክ ካኅናት፣ ባለሟሎቿ እና የንጉሣዊ ወታደሩ አባላት በአብዮቱ ላይ ሌላ አብዮት (Counter revolution) ጀመሩ። የፈረንሳይ ሪፐብሊክ የቬንዴ ሰዎች ወደ ውትድርና ገብተው አብዮቱን እንዲቀላቀሉ ቢጠይቅም የንጉሣዊ ሥርዓት ወዳጁ እና የካቶሊክ ካኅናቱ በአንድ ጎራ ከተሰዱዱ የቀድሞ ጠቅላይ አገዛዝ መሪዎች ጋር አዲሱን የፈረንሳይ አብዮት መሪዎች ጋር COUNTER REVOLUTION ጀመሩ።  በ1793 በአምስት ወራት ብቻ ከ30,000 በላይ የቬንዴ ነዋሪዎች በጅምላ ተጨፈጨፉ። ጭፍጨፋውም የፖለቲካ አመለካከትን፣ ኃይማኖትን፣ እድሜና ጾታን ሳይለይ የተፈጸመ ነው። የጄኖሳይድ አጥኚዎች አንዳንዶች የመጀመሪያ የዘመናዊ ታሪክ ጄኖሳይድ ነው ብለው ያምናሉ። (በአብዛኛው የመጀመሪያ የዘመናዊ ታሪክ ጄኖሳይድ የሚባለው በቱርክ በ1915 የተፈጸመው “አርሜኒያን ጄኖሳይድ” ነው 1.5 ሚሊዮን አርሜናዊያን በጅምላ የተጨፈጨፉበት)። 

COUNTER REVOLUTION ምንደነው? 
“A counter-revolutionary or otherwise known as a reactionary is anyone who opposes a revolution, particularly those who act after a revolution to try to overturn or reverse it, in full or in part. The adjective, “counter-revolutionary”, pertains to movements that would restore the state of affairs, or the principles, that prevailed during a prerevolutionary era”.

እንዴት ሊካሄድ ይችላል? 

ግልፅ ተቃውሞ፣ ሽምቅ ውጊያ፣ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ የዲፕሎማሲ እርዳታን መግታት፣ ተከታታይ የሥውር እጅ ሁከት እና ብጥብጥ ማቀድ፣ ማሰልጠን፣ በገንዘብ እና በቁሳቁስ መደገፍ፣ ግጭት ሊፈጠሩባቸው የሚችሉ ቦታዎች ላይ በጎሳ፣ በኃይማኖት፣ በመደብ እና በሀብት (መሬት፣ ፋብሪካ፣ ከብት፣ ጊጦሽ) ግጭት መፍጠር…የጸጥታ እና የደኅንነት መዋቅሮች ውስጥ፣ በመሥሪያ ቤቶች የራሳቸው አላማ የሚያስፈፅሙባቸውን ተልዕኮ ያላቸው ሰዎች መረብ መፍጠር፣ ከዓላማው ጋር ሊስማማ የሚችሉ አካላት ጋር መወዳጀት እና የተፈጠረውን “አብዮት” መቀልበስ ይገኙበታል። 

ሌላው ወሳኝ ሥራ “የአብዮት ኃይሉን የሚመስሉ ፀረ አብዮተኞችን” መፍጠር ነው። በተለያዩ ጊዜያት ተሞክሮ የታወቀ ሥልት ነው። ይሄም የአብዮተኛውን ኃይል ማዳከም እና በአብዮተኛው ኃይል ላይ የሕዝቡ እምነት እንዲጠፋ ማድረግ ነው። ለምሳሌ ፖሊስ ውስጥ፣ አብዮቱን በሚደግፉ ወጣቶች ውስጥ፣ በወታደሩ ውስጥ፣ በደኅንነት ሰዎች ውስጥ የአብዮቱን ሥራ የሚያደናቅፉ፣ ያልተገባቸው ነገር ውስጥ የሚገቡ የራሳቸውን ዓላማ የሚያፈፅሙ “የአብዮተኛ ውስጥ ፀረ አብዮተኛ” ኃይል በመፍጠር ግርግር እና ግጭት፣ ግዲያዎችን መፈፀም። 

 I am certain in assuming that there is a counter revolution in nature trying to hamper the change. This is also another factor. የጥቁሮች መብት ሙገታ ጊዜ ከነ ማርቲን ሉተት ጋር ከሚሰለፉ ጥቆሮች ውስጥ ለFBI የሚሠሩ የጥቁሮችን ሥም የሚያጎድፍ እና የመብት ጥያቄያቸው ተቀባይነት እንዳያገኝ በጥቁሮች ሥም ወንጀል የሚሠሩ የጥቁር አሜሪካዊያን ሰዎች ነበሩ። በኛ ሃገርም ይኖር ይሆናል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሥልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ 

በተለያዩ ሥሞች ብሔርና ኃይማኖትን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች፣ ጥቃቶች፣ ግዲያዎች እና መፈናቅሎች ተፈጥረዋል። የሽብር ጥቃት የሚመስሉ፣ እንደ ቤትን ቀለም መቀባት፣ ሽብር የሚነዙ በራሪ ወረቀቶችን መበተን ሥራዎች እየተሠሩ ነው። 

በአሶሳ፣ በሀዋሳ፣ በጌዲኦ፣ በቡራዩ፣ በጅግጅጋ፣ ሰሞኑን በምሥራቅ ወለጋ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ  ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች፣ በጋምቤላ የተለያዩ ግጭቶች፣ ጥቃቶች፣ ግዲያዎች እና መፈናቅሎች ተከስቶ የብዙ ሰው ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ጠፍቷል። ቁጥራቸው የበዙ ተፈናቃዮች አሉ። 

መምግሥት ሲገልፃቸው

“ለውጡን የማይፈልጉ”

“ጥቅማቸው የተነካባቸው”

” ‘በእንትን’ሥም የተደራጁ ኃይሎች”

“ገንዘብ መድበው የሚንቀሳቀሱ አካላት”

“ገንዘብ የተከፈላቸው፣ ሥልጠና የወሰዱ፣ በሌላ አካል የተላኩ”…ወዘ ተረፈ እያለ  የድርጊቶቹም ፈፃሚዎች ይገልፃቸዋል። 

እኔ እንደሚገባኝ መንግሥት “ገንዘብ መድቦ”፣ “አደራጅቶ”፣ “ሥልጠና እየሠጠ” እልቂትን የሚፈፅመውን ከደረሰበት ማንም ይሁን ለምን እርምጃ አይወስድም? 

የዜጎች ደኅንነት በየቦታው በሥጋት ብቻ ሳይሆን በጭካኔ ሞት እና መፈናቀል እየታመሰ ይገኛል። 

ወይስ ኃይል የለውም? ወይስ የመንግሥት መዋቅር በዚህ “ፀረ አብዮያተኛ” ቡድን INFILTRATE ተደርጓል? 


አሁን ያለው ሁኔታ በፍጹም እረፍት የሚሰጥ አይደለም። የዚህችን ሃገር የለውጥ ተስፋ በእጅጉ የሚያጨልም፣ ለማንም ጥቅም ሊውል የማይችል እና ምናልባትም ኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት ያጣችውን የለውጥ ጉዞ የምታስቀጥልበትን እድል ለሌላ ረጅም ጊዜ የሚያጨነግፍ ሁኔታ ነው ያለው። 

COUNTER REVOLUTION በኛም ሀገር በሌሎች ሀገሮች ታሪክም ትልቅ እልቂት እና ታሪካዊ ኪሳራዎችን ያስከተለ አደገኛ ነገር ነው። 

እዚህ ጋር እንድትረዱኝ የምፈልገው ነገር ቢኖር COUNTER REVOLUTION ሥልጣን ከለቀቀ ወገን ብቻ ይመጣል የሚል ግምት እንደሌለኝ እና ይልቁንም አጋጣሚውን ተጠቅሞ የራሱን የአጭር ይሁን የረጅም ጊዜ ፖለቲካዊ ፍላጎት ለማሳካት ለውጥን ወይም ደግሞ የለውጥ ጊዜ POWER AND ORDER VACUUM የሚጠቀም አካልም ሊኖር እንደሚችል አስባለሁ። በግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ምክንያት የሚከሰተውን ሁኔታ እንደ “አመራር ክፍተት’ ወይም “ብቃት ማነስ” እንደ ምክንያት በመጠቀም ” POWER DEAL” (FROM OTHER PARTY) OR UNSEAT THE LEADER (FROM WITHIN THE PARTY) ስልቶችን ሊፈጥሩ ይችላሉ። 


አንድ ግልፅ መሆን ያለበት ነገር ግን አለ። ኢትዮጵያ በምርጫ የተመረጠ መሪ እስኪኖራት ድረስ የአብይ አህመድ መንግሥት ያላት የመጨረሻው የለውጥ ተስፋ ነው። ይሄንን ካጣን ሌላ ሩብ ምዕተ ዓመት ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል። 

እኛ ዜጎች በዚህች ሀገር ያዘንነውን እና ተስፋ የቆረጥነውን ያክል፣ እኛ ለቡድናዊ ጥቅም የሀገር ጥቅምን አሽቀንጥረን የምንጥለውን ያክል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢረዱ ምን ይሰማቸው ይሆን? አብይስ በኢትዮጵያ ተስፋ መቁረጥ ይችል ይሆን? ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ አልፈልግም። የአብይ “የኛን” የሚመስል ቡድናዊ ጥቅም አለ ግን? 

ይሄንን ለጊዜው ልተወው

ስለዚህ ሁሉንም ነገር በቡድን ዓይን ብቻ ከማየት ለጋራ ጥቅምም ቢሆን አብረን እንደንተርፍ በአንድነት ከመንግሥት ጎን እንቁም።


መንግሥትም በ”እንትና” ሥም የተደራጁ…ገንዘብ መድበው ገለመሌ ትቶ የዜጎችን ደኅንነት እና የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ግዴታው ነው። ከአንድ ሀዘን ወደ ሌላ ሀዘን በየቀኑ እየተነሳን ማልቀስ ይብቃን።

ለአስተያይትዎ በ ኢሜይል servezking@gmail.com

ወይም በፌስቡክ ገፄ  Mengistu D. Assefa ሊጠቀሙ ይችላሉ

2 thoughts on ““የፀረ አብዮት እንቅስቃሴ” (COUNTER REVOLUTION) እና የዘር እልቂት አደጋ በኢትዮጵያ

  1. I share your idea and this is/will going to happen!so we have to generat ppl.awarness and could stand by Dr.Abiy’s side for better idea and benifits increase the majorities choice come to a democratic ellection to the constitution! I think this is what we got durring trasitional period until we elected the drilling party/ government.tnx for sharing your idea.
    sincerely. 💚💛❤

    Like

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡