በነገው ዕለት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ስልጣን እንደሚለቁ ተገለፀ!

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ነገ ሁለተኛ ልዩ ስብሰባቸውን ያካሂዳሉ።

ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመውም፥ ምክር ቤቶቹ በስብሰባቸው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የሚያቀርቡትን መልቀቂያ በመቀበል አዲስ ፕሬዚዳንት ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ መስከረም 27 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት ነበር አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስን በመተካት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙት።

ሶስተኛው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ነገ ለሚተካቸው አራተኛ የኢፌደሪ ፕሬዚዳንት በምክር ቤቶቹ ፊት ስልጣን ያስረክባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.