የመሆን እና አለመሆን ጥያቄ: የሀገር ወዳጅ ወይስ ጠላት? የህዝብ አሸባሪ ወይስ ደህንነት?

በሰው ልጅ ላይ የፈፀሙት ለመስማት የሚዘገንን ኢሰብዓዊ ድርጊት እየተዘረዘረ፣ የተዘፈቁበት በዓለም ታይቶም ሆነ ተሰምቶ የማይታወቅ የዘረፋና ሌብነት ተግባር እየተነገረ፣ በሀገርና ህዝብ ላይ ያደረሱት ለማመን የሚከብድ ክህደትና ውርደት እየተጠቀሰ፣… ከከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች እስከ የደህንነት ኃላፊዎች፣ ከጋዜጠኛ እስከ ቢሮ ሰራተኛ፣ ከወንድምና እህት እስከ የነፍስ አባት፣… በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በዚህ አሳፍሪ ወንጀል ተጠርጥረው በመታሰር ላይ ይገኛሉ።

አብዛኞቻችን በተጠቀሱት የወንጀል ተግባራት ስፋትና አስከፊነት በማሰብ ከመገረም በዘለለ “ለምን?” ብለን አንጠይቅም። የተጠቀሱትን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት በቅድሚያ ተጠርጣሪዎቹ ቀድሞ የነበራቸውን ስልጣንና ኃላፊነት ተጠቅመው በራሳቸው ሀገርና ህዝብ ላይ እንዲህ ያሉ አስከፊና ሰፋፊ ወንጀሎች የፈፀሙበትን ምክንያት መረዳት ያስፈልጋል። ይህን ማድረግ ካልተቻለ በስተቀር ችግሩን በዘላቂነት መቅረፍ አይቻልም።

በዚህ መሰረት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት በቅድሚያ በዜጎች ላይ የሚሰቀጥጥ ግፍና ስቃይ፣ በሀገር ላይ የሚያስደነግጥ ዘረፋና ክህደት የፈፀሙበትን መሰረታዊ ምክንያት በግልፅ መገንዘብ አለብን። ለዚህ ደግሞ በቅድሚያ “እንዲህ ያለ ግፍና በደል በሃሳብ ከመወጠን ጀምሮ ተግባራዊ እስከማድረግ ድረስ ያለውን ሂደት በበላይነት ሲመሩና ሲያስተባብሩ የነበሩ የፖለቲካ መሪዎች፣ የጦር ጄኔራሎች፣ የደህንነት ሰራተኞች እና የስርዓቱ ደጋፊ የሆኑ ልሂቃን ስለ ሀገሪቱና ህዝቡ ያላቸው አመለካከት ምንድነው?” የሚለው ጥያቄ ሊመለስ ይገባል።

በመሰረቱ የሀገር ባለቤትነት እና የህዝብ ወገንተኝነት ስሜት ያላቸው ሰዎች ከላይ በተጠቀሱት ዓይነት የወንጀል ተግባራት ውስጥ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አይሳተፉም። በሀገሩ ላይ የባለቤትነት ስሜት ያለው ሰው የዜግነት ግዴታውን በዚህ ልክ መዘንጋት አይቻለውም። ቅንጣት ያህል ሰብዓዊነት ያለው ሰው ደግሞ በሀገሩ ልጆች ላይ እንዲህ ያለ ግፍና በደል አይፈፅምም። ወይም ደግሞ እንዲህ ያለ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የሚፈፀሙበት ሰው ሰብዓዊ ፍጡር መሆኑን አምነው አልተቀበሉም።

በመሆኑም እንዲህ ያሉ አሰቃቂ ተግባራት በሰው ልጅ ላይ የፈፀሙት፤ ወይ በራሳቸው ሰብዓዊ ፍጡር አይደሉም ወይም ደግሞ ድርጊቱን የፈፀሙባቸው ሰዎች ሰብዓዊ ፍጡር መሆናቸውን በተግባር አልተቀበሉም። ምክንያቱም ሰብዓዊ ርህራሄ ያለው ሰው በሀገሩ ልጆች ላይ እንዲህ ያለ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ሊፈፅም አይችልም። ይህን አስቃቂ ድርጊት በሰው ልጅ ላይ ከፈፀሙት ደግሞ እነሱ በራሳቸው ኢ-ሰብዓዊ ፍጡራን ናቸው። ነገሩ የመሆን ወይም ያለመሆን ጉዳይ ነው። ሰው ሆኖ እንደ አውሬ፣ አውሬ ሆኖ እንደ ሰው ማሰብና መንቀሳቀስ አይቻልም።

የሀገሪቱን ሰላምና ሉዓላዊነት እንዲያስከብር ከህዝብና መንግስት ስልጣን እና ኃላፊነት የተጣለበት ሜጀር ጄኔራል በህገ-ወጥ መንገድ ጦር መሳሪያ ገዝቶ የኢትዮጵያን ጦር ሰራዊት ለሚወጉ ታጣቂ ቡድኖች የሚሸጥ ከሆነ በሀገሪቱ፣ ህዝቡ፣ መንግስት ሆነ ሰራዊቱ ላይ የባለቤትነት ወይም የእኔነት ስሜት በጭራሽ አለው ሊባል አይችልም። በተመሳሳይ የህዝብን ሰላምና ደህንነት የማስከበር ስልጣንና ኃላፊነት የተጣለበት የሀገሪቱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኃላፊ ዜጎችና የመንግስት ኃላፊዎች በተሰበሰቡበት አደባባይ ቦንብ አጥምዶ በማፈንዳት የሞትና አካል ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ ደም የጠማው አሸባሪ እንጂ የሰላምና ደህንነት አስከባሪ ሊሆን አይችልም።

በዚህ መሰረት ሰሞኑን የምንሰማቸውን የወንጀል ተግባራት በሀገርና ህዝብ ላይ የፈፀሙት የጦር፣ የደህንነት እና የፖለቲካ ኃላፊዎች የሌላ ሀገር ዜግነት ያላቸው ወይም በሽብር ተግባር የተሰማሩ ወንጀለኞች ናቸው። የጠላትን ጦር የሚያስታጥቅ የጦር ጄኔራል እና የሀገሪቱን ህዝብ የሚያሸብር የደህንነት ኃላፊ ፍፅሞ ሊኖር አይችልም። በአንድ ግዜ የሀገር ጠላት እና ወዳጅ፣ የህዝብ አሸባሪ ወይም ሰላም አስከባሪ መሆን አይቻልም። በድጋሜ ጉዳዩ የመሆን ወይም ያለመሆን ጉዳይ ነው፤ ጠላት ወይም ወዳጅ፣ ፀረ-ህዝብ ወይም የህዝብ…

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.