አዲስ የተቋቋመው የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን አባላት፤ 9 ሚኒስትሮች፣ 8 የክልል ም/ ርዕስ ፕረዜዳንቶች፣ 2 ክንቲባዎች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ሰብሰባ የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን አባላት ሹመትን አፀደቀ። ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አቅራቢነት 20 የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን አባላት ሹመትን አፅድቋል። በዚህም መሰረት፦

 1. ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል- የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር
 2. አቶ አህመድ ሽዴ- የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር
 3. አቶ ኡመር ሀሰን- የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር
 4. ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ-የትራንስፖር ሚኒስቴር ሚኒስትር
 5. ዶክተር አሚር አማን- የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር
 6. ዶክተር ፍፁም አሰፋ-የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር
 7. አቶ ሽመልስ አብዲሳ-በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር
 8. አቶ ጃንጥራር አባይ- የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር
 9. ወይዘሮ ያለም ፀጋይ – የሴቶች ወጣቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር
 10. አቶ ተመስገን ቡርቃ-በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል በሚኒስትር ማዕረግ የጥናትና ፐብሊኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ
 11. ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም – የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ
 12. ዶክተር አብርሃም ተከስተ-የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
 13. አቶ ላቀ አያሌው-የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
 14. ወይዘሮ ጠይባ ሁሴን-የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
 15. አቶ አደም ፋራህ- የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
 16. አቶ ኦርዲን በድሪ-የሀረሬ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር
 17. አቶ ኤልያስ ሽኩር-የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
 18. አቶ አብደላ አህመድ ሙሀመድ-የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ
 19. አቶ አበራ ባዬታ-የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና
 20. አቶ ታንካይ ጆንክ-የጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የኮሚሽኑ አባላት ሆነዋል።

One thought on “አዲስ የተቋቋመው የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን አባላት፤ 9 ሚኒስትሮች፣ 8 የክልል ም/ ርዕስ ፕረዜዳንቶች፣ 2 ክንቲባዎች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡