የህወሓቶች ገበና ሲጋለጥ፤ እንደ ወራሪ ጦር የዘረፉት መሬት፣ እንደ ጠላት የትም የበተኑት ገንዘብ! (አፈትልኮ የወጣ ሰነድ)

1) ህወሓቶች የተዘረፉት መሬት እየበተኑት ገንዘብ

የህወሓት ዘረፋና የመሬት ወረራ የተጀመረው ገና በትግል ላይ ሳለ ነው። በትግል ወቅት በቁጥጥሩ (ምርኮ) ስር የወደቁ ማናቸውንም ዓይነት ንብረትን የመውረስና ወደ ትግራይ ክልል ሰብስቦ የመውሰድ አባዜ ነበረው። ነገር ግን በዚህ መልኩ ተዘርፎ የሚወሰድ ሃብትና ንብረት ለህወሓቶች በቂ ወይም አጥጋቢ ሆኖ ባለመገኘቱ ከቁሳዊ ሃብት ይልቅ የከተማና ለም የሆኑ የእርሻ መሬቶችን መዝረፍ ጀመረ። የመሬትን ዘላቂ ጥቅምና አዋጭነት የተረዱት ህወሓቶች በ1984 መጀመያ አካባቢ በሰሜን ጎንደርና ወሎ ያሉ ለም የእርሻ መሬቶች ያሉበት ሁመራና ራያ በትግራይ ክልል ስር እንዲጠቃለል አደረጉ።

በመቀጠል በደርግ መንግስት ስር ይተዳደሩ የነበሩ የሜካናይዝድ የእርሻ መሬቶችን፣ ማሽኖችን፣ የባንክ ገንዘቦችን፣ በአጠቃላይ በወቅቱ በመንግስት ቁጥጥር የነበሩ ንብረቶችን “በኢንዳውመነት” ስም እንዲመዘገብ አደረጉ። በመቀጠል በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የሚገኙ የእርሻ መሬቶችን በኢንቨስትመንት ስም ተቆጣጠሩ። በዚህ መሰረት በጋምቤላንና አፋር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ፣ አብዛኛው የቤንሻንጉል-ጉሙዝ የእርሻ እና የከተማ መሬቶች፣ በደቡብ ኦሞ የመንግስት እርሻ ቦታዎች፣ የሆቴል እና የመኖሪያ ቦታዎች፣ በመተማና ጎጃም እርሻ ልማቶች፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ የሚገኙ ጥሩ የኢንቨስትምት እና የማዕድን ቦታዎችን ያለ ተቀናቃኝ በበላይነት ተቆጣጥረዋል።

በዚህ ተግባር የተሰማሩት ሰዎች የአንድ መንደር ተወላጅ የሆኑ የህወሓት አባላት ናቸው። እነዚህ መንደርተኞች በድብቅ መሬት እንዲወስዱ የተደረገው በወቅቱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር በነበሩት በአቶ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ ነው። አሁንም እየዘረፉና ሃብቱን እያሸሹ ያሉት እነዚህ ሰዎች ናቸው። ይህን ለማረጋገጥ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አማካኝነት ከዋናው መስሪያ ቤት እስከ ቅርንጫፍ የተሠጡ ብድሮችን፣ እንዲሁም በብድር ማስታመሚያና ማገገሚያ ክፍሎች ያሉት ፕሮጀክቶች የእነማን እንደሆኑ በመመርመር እውነታውን መገንዘብ ይቻላል፡፡

የህወሓቶችን የመሬት ወረራና ዘረፋ ለማሳየት የጋምቤላ ክልል ዓይነተኛ ማሳያ ነው። በኢንቨስትመንት ስም የክልሉን ነዋሪዎች በማፈናቀል የእርሻ መሬት የተሰጣቸው ሰዎች ዝርዝር ደግሞ የዛራፊዎቹን ማንነት ይጠቁማል። በመጀመሪያ ደረጃ እነዚህ ሰዎች በዝቅተኛ ክፍያ የወሰዱት የእርሻ መሬት በመስኖ ሊለማ የሚችል ነው። ሆኖም ግን የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶቹ “ከመስኖ ልማት” ይልቅ ያለ አግባብ ህጋዊ በማስመሰል “በዝናብ ማልማት” በሚል ተቀየረ። የወሰዱትን መሬት ለማልማት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ደግሞ በወቅቱ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕረዝዳንት በነበሩት በአቶ ኢሳይያስ ባህረ እንዲሰጣቸው ተደረገ።

የህዝብና ሀገር ሃብት ያለ ዋስትና የተሰጣቸው የአንድ ሰፈር ልጆች የተቀራመቱትን የእርሻ መሬት ከማልማት ይልቅ በተወለዱበት መንደር ህንፃ ለመገንባት አዋሉት። በዚህ ምክንያት ከልማት ባንክ የወሰዱት ብድር ሙሉ በሙሉ በሚበል ደረጃ በማባከን ባንኩን ለኪሳራ ዳርገውታል። የወሰዱት መሬት ሩቡ እንኳን ቢለማ ለሀገርና መንግስት የሚያሰገኘው ገቢ ከፈተኛ ነው። በእርግጥ የተወሰኑ ሰዎች ከሃምሳና መቶ ሄክታር በማይበልጥ መሬት ላይ ለማምረት ሞክረዋል። ሆኖም ግን ከዚህ የሚያገኙት ገቢ የባንኩን ብድር ቀርቶ የመሬት ኪራዩን እንኳን ለመክፈል አይበቃም።

በዚህ ምክንያት አሁን ላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተመነጠረ ባዶ ሜዳ እና ያልተመነጠረ ጫቃ ይዞ ለመቅረት ተገድዷል። በጣም የሚያሳዝነው ነገር እነዚህ አካለት በዚሁ ባንክ የተጨማሪ ብድርና በጥቃቅን ለተደራጁ ተብሎ በመንግስት በተቀረጸው ፖሊሲ ስም በመቀየር ባንኩን እየዘረፉት ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ያለ ግብር (ከቀረጽ ነፃ) የገቡ ዘመናዊ ትራክተሮች፣ ማሽነሪዎች፣ ተሳቢዎች፣ መኪናዎች (ሪቮ፣ ሃይሉክስ፣ ኤፍ.ኤስ.አር… ወዘተ ) ዕቃዎቻቸው በመፍታት እየተሸጡ ሲሆን የተቀሩትን ደግሞ ወደ አልታወቀ ቦታ እየተወሰዱ ናቸው። ከፍተኛ መጠን ያለቸው የእርሻ መሳሪዎች ደግሞ ከነጭራሹ ሳይገዙ በተጭበረበረ ሰነድ የተገዙ በማስመሰል ያለ ዋስትና ከልማት ባንክ የወሰዱትን ብድር ለሌላ ጥቅም አውለውታል።

2) በጋምቤላ ክልል በሚገኙ በዝናብ የሚለሙ የእርሻ ፕሮጀክቶች ዙሪያ የተደረገ ጥናት ሪፖርት

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በጋምቤላ ክልል ፋይናንስ ያደረጋቸውን የእርሻ ፕሮጀክቶች በተሟላ መረጃ ላይ ተደግፎ ከገቡበት ችግሮች ለማውጣትና የተቋቋሙበትን ዓላማ ለማሳካት የመሬት ልማት፣ የህንፃና የካምፕ ግንባታ አፈጻጸማቸውን፣ የእርሻ መሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎች አያያዛቸውን፣ ስለቴክኖሎጂና ባለሙያ አጠቃቀማቸው፣ ስለምርትና ምርታማነታቸው፣ ስለብድር ክፍያቸው፣ ስለጋጠሟቸው ችግሮች በእያንዳንዱ ፕሮጀክት ደረጃ ጥልቅ ጥናት በማድረግ አስፈላጊው እርምጃ ሊወሰድ ይገባል። ይህን ታሳቢ በማድረግ በፕሮጀክቶች ችግር ዙሪያ ጥናት ለማድረግ የድርጊት መርሃ-ግብር (TOR) ተዘጋጅቶ ጥናት የሚያደርግ አንድ ቡድን ተቋቁሞ ነበር፡፡

ይህ ቡድኑ እንዲያጠና የታሰበው የፕሮጀክት ብዛት በጋምቤላ ክልል የሚገኙ በጅማና በጋምቤላ ዲስትሪክቶች የሚተዳደሩ 188 ፕሮጀክቶችን የሚያጠቃልል ሲሆን ከም/ፕሬዝዳንት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስንግ በተሰጠው መመረያ መሠረት የቡድኑ ትኩረትና ወሰን የተበላሸ ብድር ደረጃ ውስጥ የገቡትን ፕሮጀክቶች ብቻ መሆን እንዳለበት ተወስኗል። የጥናቱ ዓላማ በጋምቤላ ክልል በባንኩ ብድር የተቋቋሙ የእርሻ ፕሮጀክቶች የመሬት ልማት፣ የካምፕና ሌሎች ግንባታዎች፣ የእርሻ መሣሪያዎችና ተሽከርካሪዎች፣ የቴክኖልጂና የባለሙያ አጠቃቀም፣ የምርትና ምርታማነት፣ የብድር አጠቃቀምና የብድር ክፍያ አፈፃፀም በመገምገም ለባንኩ ውሳኔ አሰጣጥ የሚያግዝ ዝርዝር መረጃና ሪፖርት ማቅረብ ነው። ሙሉ ሪፖርቱን ይህን ሊንክ (Pdf) በመጫን ማወረድና ማንበብ ይቻላል፡፡

በዚህ መሰረት ቡድኑ ከግንቦት 21/2009 እስከ ሐምሌ 15/2009 ባለዉ ጊዜ ወስጥ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ በዝናብ የሚለሙ 113 የተበላሸ ብድር ደረጃ ውስጥ በገቡት ፕሮጀክች የመስክ መልከታ እና የልኬት ሥራ አከናውኗል። እነዚህ ፕሮጀክቶች ያጋጠሟቸዉን ፈርጀ ብዙ ችግሮች እና ሊወሰዱ የሚገቡ የመፍትሄ እርምጃዎችን በዝርዝር በመለየት “በጋምቤላ ክልል በሚገኙ በዝናብ የሚለሙ የእርሻ ፕሮጀክቶች ዙሪያ የተደረገ ጥናት” በሚል ርዕስ ሪፖርት አቅርቧል። በጋምቤላ የሚገኙ የእርሻ ፕሮጀክቶች ዝርዝር አፈፃፀምና የብድር አጠቃቀም ክንውን ከዕቅዱ ጋር እየተነፃጸረ ዝርዝር ሪፖርት በጽሁፍ፣ በምስልና በቪዲዮ በማስደገፍ ያቀረበ ሲሆን የሚከተሉትን ችግሮች በመለየት በዝርዝር አስቀምጧል፦

2.1) የብድር አከፋፈል

ከታች በሠንጠረዡና ቻርቱ እንደተቀመጠው ጥናቱ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ በጥናቱ የተካተቱ ፕሮጀክቶች ጠቅላላ የብድር መጠን (ወለዱን ጨምሮ) 1,680,981,859 ብር ሲሆን ከዚህ ዉስጥ መሰብሰብ የነበረበት የብድር መጠን 520,299,451 (ውዝፍ) ብር ቢሆንም የተሰበሰበዉ የብድር መጠን ግን 79,743,176 ብር (15%) ቢቻ መሆኑ ታዉቋል:: ይህ አሃዝ የሚያሳየዉ ብድሩ ግዜውን ጠብቆ በአግባቡ እየተሰበሰበ አለመሆኑና አጠቃላይ የብድር አስተዳደሩ (Loan Admnistration) ደካማ ሲሆን፤ ለዚህ እንደ ችግር ሊነሳ የሚችለዉ ብድሩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሌላ ዓለማ መዋሉ፤ የክትትል ማነስ፤ የበለሃብቱ ትኩረት ማነስና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ ችግር ለባንኩም ህልውና አሳሳቢ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

ከሪፖርቱ የተወሰደ

2.2) የፕሮጀክት ክትትል ማነስ

በጋምቤላ ዲስትሪክት ያሉ ሠራተኞች በእነሱ ሥር የሚተዳደሩትን ፕሮጀክቶች በወረቀት ላይ ብቻ የሚያዉቁ መሆናቸዉና ፕሮጀክቶቹ ያሉበትን ቦታ በትክክል አለማወቃቸዉን ተገንዝበናል፡፡ በተለይ ክትትልን በተመለከተ ፕሮጀክቶቹ የሚገኙት በጋምቤላ ክልል ሲሆን በሌላ በኩል ብድሩ በጂማ ዲስትሪክት ተፈቅዶ በመለቀቁ ለፕሮጀክት ክትትል አስቸጋሪ አድርጓል፡፡ ይሁን እንጂ ፕሮጀክቶቹ ወደ ጋመቤላ ዲስትሪክት ከተላለፉ በኋላ በዲሰትሪክቱ በኩል አስፈላጊዉ ክትትል አለመደረጉን ተገንዝበናል፡፡ ከደንበኞች ያገኘነዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ዲስትሪክቱ ፕሮጀክቶችን የማይከታተልና የት እንዳሉም የማያዉቅ መሆኑንና አብዛኛዎቹ ፕሮጀክቶች የመስክ ምልከታ ከተደረገላቸዉ ከአንድ ዓመት በላይ ሆኗቸዋል፡፡ በተጨማሪም አንዳንድ ባለሃብቶች የእርሻ ሥራ ትቶ በመሄዳቸዉ የፕሮጀክቶቹ ሀብት (የእርሻ መሳሪያና ተከታዎቻቸዉ እንዲሁም የህንጻ ግንባታ) በክትትል ማነስ ምክንያት ለብልሽት እየተዳረጉ መሆኑ ከመስክ ምልከታ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ስለዚህ የክትትል ማነስ ለፕሮጀክቶቹ ውድቀት የአንበሳዉን ድርሻ ይይዛል፡፡

2.3) የፕሮጀክት አመራርና የሰው ኃይል ችግር

በቂ የሆነ የሰው ኃይል አለመመደብና ከቅርብ ሆኖ ፕሮጀክቶችን አለመከታተል፤ የእርሻ ሥራ በአግባቡ አለመምራት ለፕሮጀክቶቹ ውድቀት ወይም ውጤታማ አለመሆን እንደ ምክንያት ልወሰድ ይችላል፡፡ ከመስክ ምልከታ ለመገንዘብ እንደ ተቻለው ፕሮጀክቶቹ የባለሃብቱን ትኩረት ያላገኙ መሆናቸዉ፤ ብዙ ብር ፈሶባቸዉ የተገነቡት ህንጻዎች በጊዜ ባለመጠናቀቃቸዉ የተነሳ ለብልሽት አየተዳረጉ መሆኑ፤ በየቦታዉ የተጣለዉን የፕሮጀክቱን (የባንኩን) ንብረት አለመሰብሰብና በቂ ክትትል አለማድረግ የሚጠቀሱ የፕሮጀክት አመራር ችግሮች ናቸዉ፡፡

2.4) የፕሮጀክቶች ጥናት ችግር
በጋምቤላ ክልል በዝናብ የሚለሙ የእርሻ ፕሮጀክቶች እንዲያመርቱ ታሳቢ የተደረገዉ የሰብል ዓይነት ጥጥና ሰሊጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን ፕሮጀክቶቹ ያሉበት ድረስ በመሄድ ከመስክ ምልከታና ከቃለ መጠይቅ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለከተው ሁሉም ፕሮጀክቶች በጥናቱ የተጠቀሰውን የሰብል ዓይነት እያመረቱ አለመሆናቸዉ፣ ጥቂቶቹ በከፊል (በትንሽ ሄክታር ላይ) ብቻ በጥናቱ የተጠቀሰውን ሰብል እየዘሩ መሆናቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከባለሃብቶቹ እንደ ችግር የሚነሱ ምክንያቶች እርሻ እየተሠራ ያለው በሙከራ (trial and error) እንደደሆነና አፈሩ ለምን ዓይነት ሰብል እንደሚመች በአግባቡ ባለመጠናቱ ነዉ፡፡ በተጨማሪም የዝናብ ስርጭት ሁኔታም በትክክል የማይታወቅ መሆኑ፣ የትኛውን ሰብል በየትኛው ጊዜ መዘራት እንዳለበት አለማታወቁ የፕሮጀክት ጥናት ላይ ጥያቄ የሚፈጥር ነው፡፡

2.5) የገቢያ ትስስርና የአቅርቦት ችግር

አንዳንድ ባለሃብቶች እንደገለጹት ምርታቸው ትንሽ ቢሆነም ገበያ ባለመኖሩ የተመረተውን ምርት መሸጥ አለመቻላቸውን እንደ ችግር አንስተዋል፡፡ ለዚህ እንደ ችግር የሚጠቀሰው የምርት የጥራት ጉድለት፤ እየተመረተ ያለው ምርት ጥራቱ በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑ የተነሳ በገበያ ተቀባይነት ማጣቱን በተለይም የጥጥ ማዳመጫ በክልሉ ባለ መኖሩ ለብዙ አለ አስፈላጊ ወጪ እየተዳረጉ መሆናቸውን ጨምሮ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በአከባቢው የምርጥ ዘር አቅርቦት ችግር መኖሩና እየቀረበላቸው ያለውም ዘር ቢሆን በጣም ረጅም አመት ያስቆጠረ መሆኑን ተገልጸዋል፡፡

2.6) የአመለካከት ችግር

አብዛኛዉ የፕሮጀክት ወጪ የሚሸፈነዉ በባንኩ ብድር በመሆኑ በባንኩ ብር የተገዙትን የእርሻ ትራክተሮችንና መኪናዎች፤ የተገነቡትን ግንባታዎች እንደራሳቸዉ ንብረት አድረጎ መያዝና ከብልሽት መጠበቅ ላይ ትልቅ ክፍተት መኖሩና ይህም ከአመለካከት ችግር የመነጨ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ በተጨማሪም የተሰጠዉን ብድር በአግባቡ ሳይጠቀሙ አሁንም ከባንኩ ተጨማሪ ብድር የመፈለግ አዝማሚያ ማሳየትና ይህ ካልሆነ ብድሩን ለመክፈል ፍቃደኛ አለመሆን ከባለሀብቱ የሚንጸባረቁ የአመለካከት ችግሮች ናቸዉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በባንኩ ሠራተኞችም በኩል የሚንጸባረቀዉ አመለካከት ባንኩን ከመወገን ይልቅ የደንበኞችን ድክመት በመሸፈን የተሳሳተ ሪፖርት የማቅረብ አዝማሚያ ማሳየት፡

2.7) የቤተሰብ ፕሮጀክቶች ችግር

ቡድኑ ከመስክ ምልከታ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ችግር ከታየባቸው ፕሮጀክቶች መካከል የቤተሰብ ፕሮጀክቶች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እንደ ምሳሌ ገ/ሂወት ተስፋዬ ፤ሑሪያ ይክኖ ፤ ሊዲያ ገ/ሂወት (ባል ፤ሚስት እና ልጅ)፤ አክሱማዊት ይክኖ(የሚስት እህት)፤ ዮሐንስ መረሳ (የአክሱማዊት ይክኖ ባል) አንድ ቤተሰብ ሲሆኑ አምስቱም ፕሮጀክቶች በባንኩ ፋይናነስ የተደረጉ ሆኖ አራቱ (ገ/ሂወት ተስፋዬ፤ ሑሪያ ይክኖ፤አክሱማዊት ይክኖ እና ዮሐንስ መረሳ) አፈጻጸማቸው በጣም ዝቅተኛ መሆናቸውን ከባለሙያ ሪፖርትና ከመስክ ምልከታ ለመረዳት ችለናል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ሌላ የቤተሰብ ፕሮጀክት (ፋንታሁን ቢያድግልኝ፤ ነጋ ቢያድግልኝ፤ ዕርጥቤ ቢያድግልኝ) የአንድ ቤተሰብ ናቸው፡፡ የነዚህ ባለሃብቶች የእርሻ እንቅስቃሴ ጥሩ ቢሆንም ሁሉም የባንኩን ብድር እየከፈሉ አይደለም፡፡ እንዲሁም ሙሉብርሃን ደሳለኝ እና ሙሉ ብርሃን አግሮ ቢዝነስ ሁለቱም የአንድ ቤተስብ ፕሮጀክት ሲሆኑ በፕሮጀክቱ ላይ ያለው እንቅስቃሴ በጣም ደካማ መሆኑ ከመስክ ምልከታ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በተጨማሪም ንጉስ ሲሳይ እና ዩብሮ ኢንጂነሪንግ ሁለቱም ፕሮጀክቶች የአንድ ባለሃብት ሲሆኑ እንቅስቃሴያቸውን በተመለከተ በተለይ ዩብሮ ኢንጂነሪንግ በፕሮጀክቱ ቦታ ምንም ዓይነት የሰው ኃይልም ሆነ የእርሻ ማሽነሪዎች አለመኖራቸው ከመስክ ምልከታ ለመረዳት ትችሏል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት እንደ ምሳሌ የሚነሱ ሲሆን የዘመድ (የቤተሰብ)ፕሮጀክቶች ከዚህ በላይ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

2.8) የብድር መያዣ ደካማ መሆን

በባንኩ ፖሊሲ በግልጽ እንደተቀመጠው ፕሮጀክቱን ጨምሮ የፕሮጀክቱ ማንኛውም ቋሚ ንብረት ለብድሩ እንደ መያዣ የሚቆጠር መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በጋምቤላ ክልል ያሉ በባንኩ ፋይናንስ የተደረጉ ፕሮጀክቶች የብዙ መኪናና የእርሻ ትራክተር ሊብሬ በባንኩ ሥም ባለመመዝገቡ፤ እንዲሁም የመድን ዋስትና ሽፋን ያልተገባለቸዉ ባርካታ ፕሮጀክቶች መኖራቸዉ፤ በተጨማሪም ብዙ መኪናና የእርሻ ትራክተሮች በቦታ ባለመገኘታቸዉና የይዞታ ማረጋገጫ በፋይል ውስጥ ባለመገኘቱ ምክንያት መገዛታቸዉም የማይታወቅ በመሆኑና፤ በቦታ ያሉትም በጥንቃቄ ባለመያዛቸዉ ፤ግንባታዎች ባለመጠናቀቃቸዉና በመፍረሳቸዉ ፤የመሬት ልማቱ ከወጣዉ ወጪ ጋር የማይመጣጠን በመሆኑ የብድር መያዣቸው ደካማ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በተለይ የዲማ ሮዝ የተቀናጀ እርሻ ልማት የይዞታ ማረጋገጫ በፋይል ውስጥ አለመገኘቱ እንደ ትልቅ ክፍተት ተለይቷል፡፡

2.9) የደንበኛህን ዕወቅ ጥናት ችግር (KYC-know your customer)

በጋምቤላ ክልል ያሉ በባንኩ የብድር ድጋፍ የተደረገላቸዉ ፕሮጀክቶች ከመጀመሪያ የደንበኛህን ዕወቅ ጥናት ችግር እንዳለባቸዉ በዲስትሪክቱ ያሉ የተበላሸ ብድር ደረጃ ዉስጥ የገቡ ከ100 በላይ የሚሆኑ ፕሮጀክቶች ምስክሮቸ ናቸዉ፡፡ የደንበኞች ባህሪይና ሌሎች ተዛማች ጉዳዮች በጥንቃቄ ባለመጠናቱ ምክንያት ባለሃብቱ ከልማቱ ሳይሆን ከብድሩ ሂደት (የባንኩን ክፍተት) የመጠቀም አዝማሚያ አሳይቷል፡፡ ባንኩ የደንበኛህን ዕወቅ ጥናት ተጠቅሞ እንደዚህ ዓይነቶቹን ደንበኞች መለየትና አስፈላጊዉን እርምጃ መዉሰድ ሲችል ይህን በለማድረጉ አሁን የሚታየዉ ችግር ሊከሰት ችሏል፡፡ ቡድኑ የብድር ፋይሉን ለማየት በቂ ጊዜ ባይኖረዉም የደንበኞች መዋጮ በትክክል ተዋጥቶ በሥራ ላይ ዉሏል የሚል ግምት የለዉም፡፡

2.10) ፕሮጀክቶችን ጥሎ መጥፋት

በመስክ ምልከታ ወቅት እንደተመለከትነዉ 16 ባለሀብቶቸ ፕሮጀክቶችን ጥሎ የጠፉ ሲሆን ፤ እነዚህም ሑሪያ ይኩኖ አሰፋ፤ ሜሪ አግሮ ቢዝነስ፤ ኬቲ መካናይዝድ እርሻ ኃ/የተ/የግ/ማ፤ ለገሰ አግሮ ኢንዱስትሪ፤ ሚካኤል ሲሳይ፤ ተሻለ ኮለሌ፤ ሃሸንጌ አግሮ ቢዝነስ፤ ተክሉ ማሞ፤ ኦፓኛ ባ-ኣቦድ ኣግሮ ኢንዳስትሪ፤ ደመርከስ አግሮ እንዱስትሪ፤ ሚሊዮን ካሳሁን፤ አልዌሮ አግሮ ቢዝነስ፤ ገ/ሂወት ተስፋዬ፤ ሙሉብርሃን ደሳለኝ፤ ንጉስ ሲሳይ እና ሙሉብርሃን አግሮ ቢዝነስ ናቸዉ፡፡ የእነዚህ ፐሮጀክቶች የእርሻ ትራክተሮችና ተከታዎቻቸዉ ባለቤት እንዳሌላቸዉ በየቦታዉ የተጣሉ በመሆናቸዉ የጂማና የጋምቤላ ዲስትሪክቶች ተጠያቂዎች ናቸዉ፡፡

2.11) የብድር አጠቃቀም ችግር (ብድሩን ለተባለለት አላማ አለማዋል)

የብድር አጠቃቀም በተመለከተ የሚከተሉት ብድሩ ለተባለለት አላማ አለመዋሉን አመልካች ሁኔታዎች ናቸዉ፡-

 • ሁሉም ፕሮጀክቶች በጥናቱ የተቀመጠዉን የሰብል ዓይነት አለማምረታቸዉ፤
 • በደንበኛው መዋጮም ይሁን በባንኩ ብድር የተገዙት መኪናዎችና ትራክተሮች ለፕሮጀክቱ አገልግሎት ብቻ አለመዋላቸውና በቦታዉ አለመገኘታቸዉ፤
 • ጥቂት ፕሮጀክቶች 50% የግንባታ ብር የተለቀቀላቸው ቢሆንም አስከ አሁን ያልጀመሩ መሆናቸዉ፤ በጥናቱ ታሳቢ የተደረገዉ የሰዉ ኃይል አለመቀጠሩ፤ እና
 • አስከ አሁን ባለ ጊዜ ውስጥ የመሬት ልማት ሙሉ በሙሉ መጠናቀቅ ሲገባው ያልተጠናቀቀ በመሆኑ፡፡

2.12) የፖሊሲ ጥሰት

ከሰተ ባህታ የሚባል ባለሃብት (በላሬ ወረዳ የሚገኝ) ከግማሽ በላይ የሚሆነዉ መሬቱ ውሃ የሚተኛበት ሆኖ በባንኩ የብድር ድጋፍ የተደረገለት በመሆኑ የብድር አሰጣጡ ላይ ችግር መኖሩንና ውሃ የሚተኛበትን መሬት በዝናብ እንዲለማ ብድሩን ያቀረበ፤ ያጠና፤ እንዲሁም ያጸደቀዉ አካል ተጠያቂ መሆን አለበት፡፡ ከላይ የተገለጸዉ እንደ ምሳሌ የሚነሳ ሲሆን ዉሃ የሚተኛባቸዉ ፕሮጀክቶች ከዚህ በላይ ናቸዉ፡፡

2.13) የሠራተኞች ችግር

 • በዲስትሪክቱ (ጋምቤላ) ዙሪያ የታዩ ችግሮች

ከደንበኞች ጋር ተስማምቶ የመስራት ብቃት ማነስ፤ በደንበኞች መካከል አድሎ ማድረግ፤ የተበላሹ እና ፕሮጀክቱን ጥሎ በጠፉት ላይ እርምጃ ያለመውሰድ፤ በዲስትሪክቱ ሥር ያሉትን ሠራተኞችን የማስፈራራት፤ በስሩ ላሉት የቅርንጫፍና የቡድን ሥራ አስከያጆች የተቋቋመው ቡድን ወደ ሥፍራው ከሄደ በኋላ ከዲስትሪክቱ ሥራ አስከያጅ እውቅና ውጪ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ የማስፈራሪያ ድብዳቤ መጻፉን ተገንዝበናል፡፡

 • በሠራተኞች (ጋምቤላ) ዙሪያ የታዩ ችግሮች

ኮንታክት ኦፊሰሮች ፕሮጀክቶች ያሉበትን ቦታ አለማወቅ እና ፕሮጀክቶቹ ወዳሉበት ሥፍራ በመሄድ ያሉበትን ደረጃ በማወቅ ትክክለኛዉን መረጃ በማቅረብ የተሰጣቸዉን ኃላፊነት በብቃት እየተወጡ አይደለም፡፡

ከፋይል ያገኘነው የእርሻ ማሽነሪ ግምት መረጃ (ሑሪያ ይኩኖ አሰፋ) እንደሚያሳየው ትራክተሩ እና ተከታዮቻቸው በቦታ እንደሚገኙና የግምታቸውን ውጤት ብር 1.7 ሚሊየን የተገመተ መሆኑን የተገነዘብን ቢሆንም ወደ መስክ በሄድንበት ወቅት የተመለከትነው በቦታ ምንም ዓይነት ትራክር አለመኖሩን አረጋግጠናል፡፡ ይህን የግምት ሥራ የሠራው መሃንድስ በቡድኑ ተከቷል፡፡

3 thoughts on “የህወሓቶች ገበና ሲጋለጥ፤ እንደ ወራሪ ጦር የዘረፉት መሬት፣ እንደ ጠላት የትም የበተኑት ገንዘብ! (አፈትልኮ የወጣ ሰነድ)

 1. ahunem bihone yagambeila district sera askiyaje yanberute wda woliyta soddo district tkayerawe sratgawene bmasfraratena bmaskayte bherne tgne bmaderge ybzhuanune projectoche bmgudate laye yegalu btchemarime hone belwe wd altenkabtena wdaltzerfabte akababi bmazwawer lraschwe tekem belwe bsafiwe tyayezwetale mnegestem asflagiwene biyaderge ytashal amarche nawe

  Like

 2. በአሀሁነኑ ሰአተት ወለላየይተታ ሰሶደዶነን ለመማተረራመሰስ የይረደዳቸወው ዘነንደድ ከተበባበባረሪየዮቸቹ ገጋረር የወለላየይተታ ሰሶደዶ ደዲሰስተትረሪከክተት ሰስረራ አሰስከኪየያጀጅ አደድረርገወውተታለል የ ገጋበቤለላ ደዲሰስተትረሪከክተት ሰስረራ አሰስከኪየያጀጅነን ሰስለዘዚሀህ መነንገግሰተት አእነና ሀህዘዝበብ አሰስፈለላገጊወውነን ጠጥነንቀቀቄቀቄ አእደዲወዎሰስደድ

  Like

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡