“የስብሃት ማፊያ ቡድን” ክፍል 3፡ “የEFFORT” ትክክለኛ ባለቤት እና የህወሓት ዋና አለቃ ማን ነው?

እንደ ፖለቲካ ድርጅት ህወሓት ገና ከአመሰራረቱ ጀምሮ የተለየ ሃሳብና አመለካከትን የመታገስ ሆነ የመቀበል ልማድና ባህል የሌለው አክራሪ ድርጅት ነው። በዚህ ረገድ ከህወሓት መስራቾች አንዱ የሆነው የአለምሰገድ/ሀይሉ መንገሻን ጉዳይ እንደ ማሳያ መጥቀስ ይቻላል። በቀድሞ የሃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ጥበብ ትምህርቱን አቋርጦ የትጥቅ ትግሉን የጀመረው አለምሰገድ ሁል ግዜ ከድርጅቱ አመራሮች የተለየ ሃሳብ የማንጸባረቅ ልማድ ነበረው። በዚህ ምክንያት በ1976 ዓ.ም (እ.አ.አ.) በተካሄደው የመጀመሪያው የታጋዮች ጉባኤ ላይ በአመራርነት ሳይመረጥ ቀረ። የዩንቨርሲቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው የትጥቅ ትግል ከጀመሩት የህወሓት መስራቾች ውስጥ በአመራርነት ሳይመረጡ የቀሩት አለመስገድ መንገሻ እና አስፋሃ ሀጎስ ብቻ ናቸው። ከህወሓት አመራሮች እና አባላት የሚደርስበት ጫና እና ግፊት እያየለ በመሄዱ አቶ አለመስገድ መንገሻ ከአንድ አመት በኋላ ድርጅቱን ለቅቆ ተሰደደ። አቶ አስፋሃ ሀጎስ ደግሞ ከትማሊሌ ምስረታ በኋላ እ.አ.አ. በ1985 ዓ.ም ድርጅቱን ለቅቆ በስደት መኖር ጀመረ።

በመጀመሪያው የህወሓት ጉባኤ ላይ በአመራርነት የተመረጡትም ቢሆን ተመሳሳይ እጣ ነው የገጠማቸው። ቀድሞ የፖለቲካ ሳይንስ ተማሪ የነበረውና በመጀመሪያው የታጋዮች ጉባኤ ላይ ከተመረጠ በኋላ እ.አ.አ. ከ1976 – 1979 ዓ.ም የህወሓት ዋና ሊቀመንበር፣ እስከ 1986 ደግሞ የድርጅተቱ የወታደራዊ ኮሚቴ ሃላፊ ሆኖ ያገለገለው አረጋዊ በርህ (ዶ/ር) በትማሌሊ ምስረታ በኋላ በስብሃትና መለስ ቡድን ድርጅቱን ለቅቆ እንዲወጣ ተደርጓል። በተመሳሳይ እስከ ትማሌሊ ምስረታ ድረስ (1978 – 1985) የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር የነበረው አቶ ግደይ ዘራፂዮን በተመሳሳይ ምክንያትና መንገድ ድርጅቱን ለቅቆ እንዲወጣ ተደርጓል። ገሰሰው አየለ (ስሁል) እና ዘሩ ገሰሰ (አጋዚ) ትግሉ በተጀመረ የመጀመሪያ አመታት መገደላቸው ይታወሳል።

በዚህ መልኩ አቦይ ስብሃት ህወሓትን በሊቀመንበርነትና ምክትል ሊቀመንበርነት ሲመሩ የነበሩ የድርጅቱን መስራቾች በማባረር የሊቀመንበርነት ቦታውን የ28 ዓመት ወጣት ለነበረው መለስ ዜናዊ አስረከቡት። ከመስራቾቹ ውስጥ የቀሩት ለአቶ መለስ ዜናዊ ታዛዥ እና አገልጋይ የሆኑት አቶ ስዩም መስፍን እና አባይ ፀሓዬ ናቸው። ድርጅቱን ለቅቀው በወጡት መስራቾች ምትክ በአመራርነት የተሾሙት እና በድርጅቱ ውስጥ የሚቆዩት ለአቶ መለስ ዜናዊ ታዛዥና ተገዢ ከመሆን አንፃር ባሳዩት አፈፃፀም ነው። አቦይ ስብሃት ታዛዥና አጎብዳጅ በሆኑ ሰዎች ዙሪያቸውን ካጠሩ በኋላ እንደ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ አገላለፅ የህወሓት “Exchequer” ሆኑ። ይህ ማለት አቦይ ስብሃት የህወሓት ፋይናንስ ኃላፊ ሆኑ ማለት ግን አይደለም።

በእርግጥ የህወሓት ፋይናንስ ኃላፊ የነበረውን (አስፋሃ ሀጎስ?) ድርጅቱን እንዲለቅ ካደረጉ በኋላ ምትኩ ለመለስ ዜናዊ ታዛዥና ለእሳቸው ተገዢ የሆነ አመራር መድበዋል። ስለዚህ አቦይ ስብሃት የህወሓት ፋይናንስ ኃላፊ ሳይሆኑ የድርጅቱን የፋይናንስ ገቢና ወጪ በበላይነት ይቆጣጠራሉ። በሌላ በኩል የህወሓትን የፖለቲካ አቅጣጫና እንቅስቃሴ የሚመራውን የህወሓት ዋና እና ምክትል ሊቀመንበሮች በማስወገድ የሚፈልጉትን ግለሰብ እንዲሾም አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ እ.ኢ.አ በ1993 ዓ.ም ህወሓት ለሁለት ሲከፈል ለአቶ መለስ ዜናዊ ስልጣንና መመሪያ ተገዢ አልገዛም ያለውን ቡድን አከርካሪ በመምታት ረገድ ቁልፍ ሚና እንደነበራቸው ይታወቃል።

በዚህ መሰረት አቦይ ስብሃት ከህወሓት ሊቀመንበሩና ሌሎች አመራሮች ኃላ ተቀምጠው የድርጅቱን ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ የመዘወር ስልጣን እንዳላቸው መገንዘብ ይቻላል። ስለዚህ የድርጅቱን የፋይናንስ ገቢና ወጪ የሚቆጣጠሩ ወይም የፖለቲካ አደረጃጀትና እንቅስቃሴ የሚመሩ አይደሉም። ከዚያ ይልቅ ህወሓትን እንደ ትልቅ የቢዝነስ ኩባኒያ ብንወስደው፤ አቦይ ስብሃት የኩባንያው ባለቤት ሲሆኑ መለስ ዜናዊ ደግሞ ዋና ስራ አስኪያጅ (CEO) ነው። የተቀሩት የህወሓት አባላት እና አመራሮች በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የድርጅቱ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ናቸው።

የህዝብ እንደራሴ በነበረው አቶ ገሰሰው/ስሁል አየለ እና ሰባት (7) የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አማካኝነት የትግራይን ህዝብ እኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና የራስን እድል በራስ የመወሰን ዴሞክራሲያዊ መብትን ለማረጋገጥ የተመሰረተው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከመስራቾቹ ፍቃድና ይሁንታ ወደ ትማሌሊ ተቀየረ። በዚህ አማካኝነት ህወሓት ከተቋቋመለት ዓላማና ግብ ውጪ በአንድ ግለሰብ ፍላጎትና ቁጥጥር ስር ወደቀ። የደርግ መንግስት መውደቅን ተከትሎ ህወሓት ከትማሌሊ ወደ ¨EFFORT” ተቀየረ። እንደ አንድ ፖለቲካ ድርጅት የዜጎችን መብትና ፍትህ ከማስከበር ይልቅ የአቦይ ስብሃትን ገቢና ትርፍ ለማሳደግ የሚንቀሳቀስ የቢዝነስ ድርጅት ሆነ። በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የድርጅቱ አባላትና አመራሮች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ¨የEFFORT” ወኪልና ሠራተኞች ሆኑ። ከታች ባለው የቴሌቪዥን ቃለ-ምልልስ እንደተናገሩ ለአቦይ ስብሃት ¨EFFORT የማን ነው?” የሚለውን ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች የተማሩና የሚያስተውል አዕምሮ ያላቸው መሆኑን ይጠራጠራሉ።

አቦይ ስብሃት በቃለ-ምልልሱ እንደገለጹት ¨በEFFORT” ስር ያሉት ድርጅቶች በኢትዮጵያ የንግድ ህግ መሰረት የተመዘገቡ የኢንዶውመንት ድርጅቶች ናቸው። የድርጅቶቹን መነሻ ካፒታል ህወሓቶች ከውጪ ያመለጡት ሃብት ነው። በመሆኑም ሲፈልጉ ታንዛኒያ ወይም ሌላ የውጪ ሀገር ማድረግ ሲችሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ መወሰናቸውን ጠቅሰዋል። የህወሓት “Exchequer” እንደመሆናቸው መጠን የEFFORTን መነሻ ካፒታል ከየት እንዳመጡት በግልፅ የሚያውቁት አቦይ ስብሃት ብቻ ናቸው። በህወሓት አማካኝነት በሰበሰቡት ገንዘብ በተቋቋሙት የኢንዶውመንት ድርጅቶች ላይ ህወሓት ምንም ዓይነት ድርሻ ሆነ ባለቤትነት እንደሌለው በመጥቀስ፣ በEFFORT ላይ ባለቤትነት ሊኖረው የሚችለው የትግራይ ህዝብ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ባለፈው አመት የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የEFFORT ድርጅቶችን በአክሲዮን መልክ ወደ ህዝብ ስለማስተላለፍ መወያየት ሲጀምር አቦይ ስብሃት ድርጅቱ የግል አንጡሯ ሃብታቸው እንደሆነ፣ በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በራሳቸው እና በቤተሰቦቻቸው ስም ተመዝግቦ እንደሚገኝ እና ይህን ሃብት ለትግራይ ህዝብ አዘዋውር ብሎ ማንም ሊጠይቃቸው እንደማይችል ተናግረው ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ይታወሳል። በመጀመሪያ የEFFORT ድርጅቶች መነሻ ካፒታል የተገኘው በአቦይ ስብሃት አማካኝነት ነው። ሁለተኛ በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚገመት የEFFORT ሃብት በአቦይ ስብሃት ስም ተመዝግቦና ገቢውም በእሳቸው የባንክ ሂሳብ ገቢ መደረጉን በራሳቸው ተናግረዋል። በዚህ መሰረት “የEFFORT” ዋና ባለቤት የትግራይ ህዝብ፣ ህወሓት ወይም ሌላ አካል ሳይሆን አቦይ ስብሃት ነጋ ናቸው።

ቀደም ሲል ለመግለፅ እንደተሞከረው ከትማሌሊ ምስረታ በኋላ ህወሓት በአቦይ ስብሃት ፍላጎትና ፈቃድ የሚመራ ድርጅት ሆኗል። ከህወሓት ሊቀመንበር ጀምሮ ያሉትን አመራሮች ለእሳቸው ጥቅምና ፍላጎት ተገዢና አገልጋይ እንዲሆኑ በማድረግ ድርጅቱን የግላቸው አድርገውታል። ስለዚህ አቦይ ስብሃት የህወሓት አባልና አመራር ብቻ አይደሉም። ከዚያ ይልቅ ህወሓት አቦይ ስብሃት የዘረጉት ድርጅታዊ መዋቅርና የሰው ኃይል አደረጃጀት ነው። ይህን ካደረጉ በኋላ፤ በአስከፊ ድርቅ ምክንያት ለተራበው የትግራይ ህዝብ ከውጪ የተለገሰ የእርዳታ ገንዘብ፣በአክሱም ከተማ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተዘረፈ ገንዘብ፣ ከደርግ ሰራዊትና የመንግስት ድርጅቶች የተዘረፈ ሃብትና ንብረት፣ እንዲሁም ምንጩ በግልፅ ያልታወቀ ገንዘብን በማሰባሰብ “EFFORT” የተሰኘ ትልቅ የንግድ ኩባኒያ አቋቁመዋል። ስለዚህ አቦይ ስብሃት የEFFORT ባለቤት እና የህወሓት አለቃ ናቸው። በአጠቃላይ EFFORT እና ህወሃት አንድ ላይ “የስብሃት ማፊያ ቡድን” ሊባል ይችላል።

8 thoughts on ““የስብሃት ማፊያ ቡድን” ክፍል 3፡ “የEFFORT” ትክክለኛ ባለቤት እና የህወሓት ዋና አለቃ ማን ነው?

  1. እጅግ እውነትን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ጽሀፍ ነው። በ1967 ዓ.ም ለህዝባችን ፍትህና እኩልነትን ማረጋገጥ የምንችለው ለነፃነት ስንታገል በሚል ነፃ አገር ለመመስረት ነበር ሁሉም ወደ ደደቡት ያቀነቱ። ሆኖም በኃላ የመጡ ብልጥ ነን ባዮች የድርጅቷን ግብ ከነፃነት ወደ ኢትዬጵያን ወሮ መዝረፍ ቀይረው ሌሎቹን አሰናበቱ። የዝርፊያው እቅድ ባለቤት መለስን ስብሃት መሆናቸውን መረዳት ይቻላል። ለሁለቱ ብቻ ሚስጥር ለሆነው እቅድ የማይመቹትን በግዜ ሸኙ። ወላዋዮችን ያለዋቸውን የሚያስተጋቡ ፑፓት መሆናቸውን ስለተረዱ ይዘዋቸው ቀጠሉ። የተወገደትም የቀጠሉትም አንዳንዶቹ ወደ ዝርፊያ ቡድን መቀየራቸው ስላልገባቸው ሲሆኑ፣ ከፊሉ 81% የአገሪቱን ህዝብ የሚወከልቱ 3ቱ እህት ተብዬ ፓርቲዎች ያን ያህል ጅል ሆነው አገራቸውን ያዘርፋሉ ብሎ ካለመጠበቅም ይመስላል። በዘራፊ ቡድንና ተቋም ውስጥ እርግጥ ነው በጅሮንድ ወይም አቅቤ ነዋይ የአፄነት ሚና ይረዋል። ምክንያቱ የሚዘተፈው ነገር መጨረሻ ውጤት ገንዘብ ነውና። የወተት ልማት የሚያከናውን ትልቁ የሰው ሃብቱ ከላሞቹ ጋር ግንኙነት ያለው ነው። የግንባታ ተቋም ኢንጁነር፣ ሆስፒታል ዶክተር፣ ፋብሪካ ምርት ክፍል ያሉ ኃላፊዎች አፄ ናቸው። ለሌባና ዘራፊ ቡድን ደግሞ ገንዘቡ ዘራፊና ፋይናንስ አስተዳዳሪ ነው አፄው። ተዘርፎ ካልመጣ ወታደሩ ምን በልቶ ሊዋጋለት ከፋይናንሱ ሰው በላይ ቦታ ይሰጠዋል? የሚዘተፍ የሌለውን ገበሬ የሚቀሰቅሱትስ ቢሆኑ ለሌባ ቡድን ከአቃቤ ነዋይ ይልቅ ምንም ሊፈይዱስ ይከበራሉ። ስለዚህ ሁለቱ ሰዎች ብቻ አውቀው ወደ ወራሪ ዘራፊትነት የቀየሩት የህወሃት ግብ ነው የበጅሮንድ ስብሃት ስምና ስልጣን ያገዘፈው። የሌባ ግብ ፋይናንስ ስለሆነ። የዘራፊ ቡድን መሪም የዘረፈውን የሚሰበስብለት ከካደው ባዶ መሆኑን ስለሚያውቅ ከሱ በላይ የገንዘብ ቋቱን ያከብራል። ይህ በብዙ ዘራፊ ኩባንያዎች የሚታይ እውነት ነው። የሰርቁትን ንብረት ያስቀመጡበት ሰው ክዷቸው የፈረሱ ብዙ አሉ። መለስ ደግሞ በዚህ የሚሸወድ ስላልነበር አቃቤ ነዋዩና የኢንቨስትመንት ማናጀሩን ከሱ በላይ አፄ በማድርጉ ሳይወድቅ የቆየው። አቃቤ ነዋይ ካኮረፈ የሚጣውን ስብሃት ለነደፂ ነግሯቸው ይሄው ህልም ነገር ወደ ጦር ግንባር ሲል አብረው ማለት ጀምረዋል። የጵጵስና ቆብ ድፋ ሲለውም ደፍቷል፤ አቃቤ ነዋይ ነውና። የሌባ ቡድን ምናልባት ነገ ቢነቃብኝ ብሎ ስለሚሰጋ ከነገም ይሰርቃል። ህወሃትም ለዚህ ነው አገሪ ከነገ ሃብት የምትከፍለው እዳ ጭኖባት የነገ ዝርፊያ ውን ዛሬ የጨረሰው። ዘራፊ አላማውን የሚያደናቅፍ ከገጠመው ይገድላል፣ ያሳድዳል፣ ያሰቃያል፣ ይደፍራል። ለዚህም ነው ህወሃት ለዝርፊያ የምትጠቀምበትን መንግስትነት ያሳጡኛል የምትላቸው ሰብአዊ መብታቸውን ገፋ ዝም ስታስብል የነበረው። ዘራፊ ተጠርጣሪ ስለሆነ ማንንም አያምንም። ለዚህም ነበር ህወሃትም ለዝርፊያዋ ስትል ከራሷ አልፋ እንደ ሸርሙጣ 3ቱ እህቶቿ ቤት ገብታ መስታወት ታይ የነበረው፤ ስለማታምናቸው። ባለፉት 27ት አመታት በአገራችን የነበረው ፓለቲካ ሳይሆን ዝርፊያ እንደነበር ማረጋገጫው ከፓለቲካ ስልጣን ውጭ የነበረው አፄ ስብሐት ትናንት ብቻ ሳይሆን አሁንም ጭምር የሱ ክንፍ በለውጡ ቲም ውስጥም የሚታየው። ለዘረፋ በሚወረር አገር ወዳጅ ሊሆን የሚችለው የትም ሃገር ዜጋ ይሆኑ ተባባሪ ሌባ ነው። እነ ቻይና እና ህንድ ከኢትዮጵያዊን በላይ በህወሃት አዛራፉ ስለሆኑ ነው። ህወሃት ሽንፈት 27ት አመታት ወራሪ ዘርፊ ቡድን እንደነበረች 1 ሚልዮን መረጃዎች ነበሩ። አሁንስ ኢትዮጵያን መዝረፍ በቃ ብለን መንግስትነቷን ልንከለክላት ግድ የሚልበት ወቅት ላይ ነንና የመረጣትን ህዝብ እንጂ ፌደራል ላይ ነንና ከላይ እስከ ታች ከሲዳማ የበለጠ ሚና ሊኖራት አይገባም። ለዝርፊያ የተማረ ሽልማት ስለማይሆን በየትኛውም የፌደራል ተቋም ትምህርት ልዩ መጠቀሚያዋ እንዳይሆን እንጠንቀቅ። ትምህርቱም የተገኘው በሌብነት ሌሎቹን ቀምታ ስለሆነ። ይቅርታ ትናንት የነበረውን ሸራርፎ ለምስቀጠል ከሆነ አዋጁን በግዜ ልንቃወም ይገባል። አገር ወሮ ለዘረፈስ እንዴት ይቅርታ አድርጌልሃለሁ ይባላል። ሌብነት እኮ ሱስ ነው።

    Like

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡