ኢንተርፖል: “ወንጀል ፈፅመው በውጪ ሀገር የተደበቁ ተጠርጣሪዎችን እጃቸውን አንጠልጥዬ ለኢትዮጵያ መንግስት አስረክባለሁ!”

በኢትዮጵያ ወንጀል ሰርተው በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የትም ሆነ የት መሸሸጊያ ያላቸውን እጃቸውንም አንጠልጥዬ ለኢትዮጵያ መንግስት አስረክባለሁ ሲል አለም አቀፍ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል ማስተማመኛ ሰጠ፡፡

ትናንትና አዲስ አበባ የመጡት የኢንተርፖል ዋና ሀላፊ ዶ/ር ጀርጋን ስቶክ ከፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ነው ወሬው የተሰማው፡፡

ከንግግሩ በኋላ መግለጫ የሰጡት ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው በኢትዮጵያ ወንጀል ሰርተው በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያንን ኢንተርፖል ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደሚሰጥ ማስተማመኛ ሰጥቷል ብለዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራሉ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙና ሀገር የዘረፉ ሰዎች ግማሾቹ በሀገር ውስጥ ግማሾቹ ደግሞ ባህር አቋርጠው በውጭ አገር እንደሚኖሩ ታውቋል ብለዋል፡፡

ይህንን ወንጀል ፈፃሚዎቹ የትም ይደበቁ የትም ይኑሩ ኢንተርፖል እጃቸውን አንጠልጥሎ ለኢትዮጵያ መንግስት እንደሚያስረክብ ሀላፊው አረጋግጠውልናል ሲሉ መናገራቸውን ከመንግስታዊ የወሬ ምንጮች ሰምተናል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሰሞኑ ባስተላለፉት መልዕክት በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች ማንም ይሁን ማን ከየትኛውም ብሔር ገብተው ይደበቁ፣ የትኛውም ወገን ይጩህላቸው በወንጀል እስከተጠረጠሩ ድረስ ካሉበት አድነን ለህግ እናቀርባቸዋልን ማለታቸው ይታወሳል፡፡

(ንጋቱ ሙሉ)

ምንጭ፦ ሸገር

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.