“ኢትዮጵያ በአስጊ እና በአጓጊ ሁኔታዎች ተከብባለች!” ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በመቐለ መካሄድ ጀመረ

የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል

በጉባዔው መክፈቻ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበርና የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂ እና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ተገኝተዋል።

ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፥ ላለፉት ሁለት አመት ተኩል በተለያዩ አቅጣጫዎች ከባድ ትግል መደረጉን እና በአሁን ሰአት ኢትዮጵያ በአስጊ እና በአጓጊ ሁኔታዎች መከበቧን ተናግረዋል።

እንደ ሀገር የሚታዩ ተግዳሮቶችን መቅረፍ እንዲቻል ሴቶች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሊያደርጉ እንደሚገባ ነው ወይዘሮ ሙፈሪያት ያሳሰቡት።

ሴቶች ተፈጥሯዊ ባህሪያችን ለሰላም የቀረበ ነው ያሉት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ህዝብ እንደ ህዝብ ጥላቻ እንደሌለበትም ተናግረዋል።

መቼም ቢሆን ሴቶች ለሀገራዊ ሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ሀገሪቱ ከፊቷ የተደቀነባትን ተግዳሮቶች ማፅዳት እንደሚገባቸው ለጉባኤው ተሳታፊዎች አሳስበዋል።

ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ጉባኤ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶች ተሳታፊ ናቸው።

በዚህ ጉባዔ ድርጅቱ ለሴቶች የተሰጠውን ትኩረት አጠናክሮ የሚያስቀጥል አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የተደራጀ የሴቶች ተሳትፎ ለሀገራዊ ለውጡ የጎላ ፋይዳ እንዳለው በማሰብ ኢህአዴግ በሴቶች ዙሪያ እያደረገው ላለው እንቅስቃሴ ጉባኤው ተጨማሪ ጉልበት ይኖረዋል ተብሏል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ & አርትስ 07/ 04 /2011

One thought on ““ኢትዮጵያ በአስጊ እና በአጓጊ ሁኔታዎች ተከብባለች!” ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል

  1. ህወሃትን ባቀፈ ኢህአዴግ የሚባል ህብረት እየተመራች አገራችን አንድም ቀን በሰላም ታድራለች ብሎ መዘንጋት እንደሌለብን ትምህርት መውሰድ አለብን። ህወሃት እያንዳንዷን በቀንነት የሚቀርብ የማግባባት ጥረት እንዲሁም የሰላም ልመና የምትገነዘበው እኔ ከሌለሁ አገሪቱ ትፈርሳለች ያልኩት ገብቷቸዋል ብላ ነው። በዚህም ከይቅርታና መፀፀት ይልቅ የዘላለም ፍላጎቷ የሆነውን ዝርፊያዋን ለማስቀጠል ነው እቅድ የምትነድፈው። የለውጡን ኃይል መተቸት ወያኔን ስለሚያስደስት ምንም ማለት አልፈልግም። ሆኖም ትናንት ሲገሉን፣ ሲደፍሩን፣ ሲዘርፉን፣ ሲያሳድዱ ከነበሩ ጋር እየሳቁ መታየት ከነሱ ጋር እንዳያስደር እሰጋለሁ። ዛሬም አጥፍተናል ይቅር በሉን ከማለት ይልቅ እኛ ብቻ አይደለንም ወንጀል የሰራነው በሚል ጥፋተኞችን መከላከል ነው የመረጡት፤ ወንጀል ከሌሎች ጋር መፈፀም ህጋዊ ይመስል። ከዚህ ቀደም በአደጋ 30 ተማሪ የሞቱባት ደቡብ ኬርያ ሚንስትር ህዝብን በአግባቡ ስላልመራሁ ነው በሚል ይቅርታ ጠይቀው ከስልጣናቸው ለቀዋል። እኛ ጋር ግን ግብሰዶም ፈፅሞ የገደለ እየቀለደ ያስካካብናል። ሰዎቹ ስነልቦናችንን አውቀው ነው የሚቀልደብን። ኑ ሲሉን እንሄዳልን፣ ይህን ልበሺ ሲሉን እንለብሳል። በሆድ የሚገዙ ናቸው ብለው ሆዳም ሰብስበው እያበሉም ምርመራ የማይሻ 66 ቢሊዬን ዶላር ዘረፋን። ህዝብ በቃ ሲላቸው ተጨማሪ 100 ቢሉዬን እንድዘርፍ ካልፈቀዳችሁ በሚል የአምላክን ዘውድ ጭነው እርስ በርስ አባልቼ አጠፋችኋለው አሉን፤ አምላክ ተክተው በሰው ህይወት ለመወሰን። ሰሞኑን ከወደ መቀሌ የምናያቸው ስብሰባዎች የለውጡ የኋላ መሪዎች እኛ ነን እያሉ ከዚህ ቀደም ቃለ ምልልስ ይሰጡ የነበሩንም ደምቀው ቀጣይ አቅጣጫ ሲሰጡም አሰምቶናል። በከተማችን ያሉ ጭፍራዎቻቸውም ቀድሞ የለመዱትን ህዝብን እየሰደቡ ስጋ መቁረጥ እየተመለሱ ይመስላል። እኔ አገራችን አደጋ ላይ ነች ማለት የምጀምረው የለውጡ መሪነን የሚሉ ለበጎም ይሁን ለመጥፎ አላማ እነሱን ለብሶ እነሱን ሆኖ ከነሱ ጋር ሲታይ ነው። ለሴቷ ምንም ፋይዳ ያፈጠረ የሊግ ስብሰባ ቀረ አልቀር ለተሰብሳቡ አበል ባለፈ ለአገሩቱ ምንም ነው። ስጋታችን እውን አሁንም የኢትዮጵያ 5% ህዝብን የሚሸፍን ክልልን የምትወክለው የህወሃት የበላይነት ካልተከበረ አገሪቱ አደጋ ላይ ነች ነው እየተባለ ያለው?

    Like

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡