ሰበር ዜና: Mbirr እና የህወሓት ሽብር! ኢትዮጵያን የማተራመስ ዕቅድ – የ3 ወር አፈፃፀም ሪፖርት (ከMbirr ለትግራይ ክልላዊ መንግስት የተላከ ኢሜል)

ይህ ደብዳቤ የተላከው አቶ እንደሻው ከተባሉት የ“Mbirr IT Services PlC” ዋና ስራ አስኪያጅ ነው። መረጃው “endashaw@mossict.com” በሚል የኢሜል አድራሻ በቀጥታ ለትግራይ ክልላዊ መንግስት (tig.gov.@gmail.com) እና ለኢፈርት (EFERT@gmail.com) የተላከ ሲሆን በ getaches@gmail.com እና ermias@mossict.com የኢሜል አድራሻ ለሁለት ሰዎች ግልባጭ ተደርጓል። የመጀመሪያው የኢሜል አድራሻ የአቶ ጌታቸው አሰፋ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ምክንያቱም በደብዳቤው መጨረሻ ላይ ለአቶ ጌታቸው አሰፋ “ኮፒ” ወይም ግልባጭ መደረጉ ተጠቅሷል። ከእሱ በተጨማሪ ለአቶ አባይ ጸሀየ እና አቶ ስብሃት ነጋ ስም በግልባጭ እንደተደረገላቸው ተጠቅሷል፡፡

ይህ ደብዳቤ ሚስጥራዊ እንደሆነ ለማሳየት “highly classified” በሚል ተገልጿል። በእርግጥ የደብዳቤው ይዘት ተመሳሳይ ነገር ይጠቁማል። በጉዳዩ ላይ በተገለፀው መሰረት ደብዳቤው የተፃፈው ድርጅቱን “የሶስት ወር የስራ አፈጻጽም ግምገማ ለማሳወቅ” ነው። ሆኖም ግን ከዝርዝሩ መረዳት እንደሚቻለው Mbirr IT Services PlC የተባለው ድርጅት ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ከትግራይ ክልል መስተዳደር እና ኢፈርት የተቀበለውን ሰባት መቶ ሃምሳ ሺ ብር (750,000 ብር) በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ለሚገኙ ግለሰቦች በወኪሎቹ አማካኝነት ክፍያ መፈፀሙ ተገልጿል።

ከላይ በቀረበው የሰነድ ማስረጃ መሠረት በMbirr በኩል ክፍያ የተፈፀመው እነ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ አቶ አባይ ጸሀየ እና አቶ ስብሃት ነጋ በሰጡት ስምና አድራሻ እንደሆነ በደብዳቤው ተጠቁሟል። ከዚህ በተጨማሪ Mbirr IT Services PlC በሱዳን እና ጅቡቲ የነበሩት አካውንቶች አገልግሎት መስጠታቸውን እንዳቆሙ በመግለፅ በቀጣይ ግብጽ (ካይሮ) በሚገኘው የድርጅቱ አዲስ አካውንት በኩል ክፍያ እንዲፈፅሙ ጠይቋል። በመጨረሻም ድርጅቱ ተገቢውን ክፍያ እስከፈፀሙ ድረስ በአብሮነት ለመስራት ፍቃደኛ መሆኑን ገልጿል። በዚህ መሰረት፣

 1. Mbirr IT Services PlC ከትግራይ ክልላዊ መንግስት እና የኢፈርት ድርጅቶች የተቀበለውን ገንዘብ በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ለሚገኙ ሰዎች የሚከፍልበት ምክንያት ምንድነው?
 2. በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ ተከፋዮችን ስምና አድራሻ ለMbirr IT Services PlC የሚሰጡት አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ አቶ አባይ ጸሀየ እና አቶ ስብሃት ነጋ፣ እንዲሁም የክልሉ መንግስት እና ኢፈርት መሆናቸው ምን ያሳያል?
 3. የትግራይ ክልላዊ መንግስት እና የኢፈርት ድርጅቶች Mbirr IT Services PlC ለተባለው ድርጅት ጅቡቲ፣ ሱዳን እና ግብፅ በሚገኝ አካውንት ገንዘብ የሚያስገቡበት ምክንያት ምንድነው?
 4. Mbirr IT Services PlC በጅቡቲና ሱዳን ያሉት አካውንቶች ለምን አገልግሎታቸውን አቋረጡ? ኢዲሱ አካውንትስ ከሌሎች ሀገራት ይልቅ ግብፅ ውስጥ የተከፈተበት ምክንያት ምንድነው?

የMbirr ዋና ሥራ አስኪያጅ የፃፈውን ደብዳቤ መሠረት በማድረግ የሚከተሉትን ነጥቦች ማስቀመጥ ይቻላል። በመጀመሪያ ደረጃ Mbirr IT Services PlC የተባለው ድርጅት ከትግራይ ክልላዊ መንግስት እና የኢፈርት ድርጅቶች ገንዘብ እየተቀበለ በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ገንዘብ የሚያከፋፍልበት አግባብ የለም። ምክንያቱም የክልሉ መንግስት ሆነ የኢፈርት ድርጅቶች ግልፅነት በጎደለው መልኩ ከኢትዮጵያ መንግስት ዕውቅና ክትትል ውጪ የገንዘብ ዝውውር የሚፈፅምበት አግባብ የለም። በመሆኑም የትግራይ ክልላዊ መንግስት እና የኢፈርት ድርጅቶች በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር መሰማራታቸውን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚያ በተጨማሪ የተከፋዮቹን ስምና አድራሻ ለMbirr IT Services PlC የሚሰጡት አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ አቶ አባይ ጸሀየ እና አቶ ስብሃት ነጋ መሆናቸው፤ ክፍያው የሚፈፀመው በሀገር ውስጥ ለሚገኙ ግለሰቦች ሆኖ ገንዘቡ ግን ገቢ የሚደረገው ሱዳን እና ጅቡቲ በሚገኙ የMbirr IT Services PlC አካውንቶች መሆኑ፤ እንዲሁም የጅቡቲና ሱዳን አካውንቶች ሲዘጉ ከሌሎች ሀገራት ይልቅ በግብፅ ካይሮ አዲስ አካውንት መክፈቱ በህገወጥ መንገድ የሚዘዋወረው ገንዘብ የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት ለማናጋት የሚውል እንደሆነ ይጠቁማል። በዚህ መሠረት በፀረ-ለውጥ አቋማቸው የሚታወቁት አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ አቶ አባይ ጸሀየ እና አቶ ስብሃት ነጋ በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት በMbirr IT Services PlC አማካኝነት የገንዘብ ክፍያ እንደሚፈፅሙ መገንዘብ ይቻላል። በደብዳቤው ላይ እንደተገለፀው ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ 750ሺህ ብር የተከፈለ ሲሆን ገንዘቡ ምንጭ ደግሞ የትግራይ ክልላዊ መንግስት እና የኢፈርት ድርጅቶች ናቸው።

ከላይ በተገለፀው መሠረት የህወሓት መስራቾች የሆኑት አቶ አባይ ጸሀየ እና አቶ ስብሃት ነጋ፣ እንዲሁም የድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው አሰፋ በተለያዩ የኢትዮጵያ አከባቢዎች ሁከትና ብጥብጥ የሚያስነሱ ሰዎችን እንደሚመለምሉ፣ ስምና አድራሻቸውን ለMbirr IT Services PlC በመላክ የገንዝብ ክፍያ እንዲፈፀም ትዕዛዝና መመሪያ ይሰጣሉ፡፡ ሌላው ከትግራይ ክልላዊ መንግስት እና የኢፈርት ድርጅቶች የተገኘው ገንዘብ ለMbirr የሚሰጠው ጅቡቲ እና ሱዳን ባሉት አካውንቶች በኩል ነው፡፡ ይህ የሆነበት መሰረታዊ ምክንያት በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረገው የገንዘብ ዝውውር ከኢትዮጵያ መንግስት ለመሰወር ነው። ከቅርብ ግዜ ወዲህ የዶ/ር አብይ አመራር ከጅቡቲ እና ሱዳን መንግስት ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እያጠናከረ መምጣቱን ተከትሎ Mbirr IT Services PlC በሁለቱ ሀገራት ያለው አካውንት እንዲዘጋ መገደዱን መገመት ይቻላል፡፡ ይህን ተከትሎ በግብፅ ካይሮ አዲስ አካውንት በመክፈት አገልግሎቱን ለመስጠት መወሰኑን አስታውቋል። በዚህ መሠረት አስፈላጊውን ክፍያ እስከተፈፀመ ድረስ በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት ተግባር ለተሰማሩ ሰዎች ክፍያ መፈፀሙን እንደሚቀጥል የMbirr ዋና ሥራ አስኪያጅ ከትግራይ ክልላዊ መንግስት እና ለኢፈርት በላከው ደብዳቤ አረጋግጧል።

7 thoughts on “ሰበር ዜና: Mbirr እና የህወሓት ሽብር! ኢትዮጵያን የማተራመስ ዕቅድ – የ3 ወር አፈፃፀም ሪፖርት (ከMbirr ለትግራይ ክልላዊ መንግስት የተላከ ኢሜል)

 1. how come effort and Tigray government uses Gmail account as an institution? I mean I thought you are smart enough to understand such petty stuff.

  Like

 2. The fake news article posted on Ethio Think Tank was categorically untrue, and resulted from the impersonation of one of our employee’s email accounts. We have demanded that they retract the article immediately. We request that all news media refrain from publishing this fake news article.

  Like

 3. Seyoum Teshome የጀግና ስራ ነው። በቻይኖች የሚመሩ በርካታ ኩባንያዎችን ሚስጥርም በቅርቡ በሰበር ዜና እጠብቃለሁ

  Like

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡