ሰበር ዜና: “የፌዴራሊስት ግንባር” መስራቾች ስም ዝርዝር አፈትልኮ ወጣ!

የህወሓት አመራሮች “ኢትዮጵያን እናድን በሚል ፌዴራሊስት ሃይሎችን” ከህዳር 23/2012 ዓ.ም ጀምሮ ስብሰባ መጥራታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። በዚህም በስብሰባው ከ15 አገር አቀፍ እና 30 ክልላዊ ድርጅቶች የተውጣጡ ከ190 በላይ አመራሮች እና ሽማግሌዎች እንዲሳተፉ የህወኃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት አመራሮች ጥሪ በማድረግ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የተገኘው መረጃ ያመላክታል። በዚህም በስብሰባው፦

  • የጉሙዝ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ አመራሮች የሆኑት ግራኝ ጉደታ (ሊቀመንበር)፣ ዶ/ር መኮነን ጎለሳ ባጄትስ፣ ደርጉ ፈረንጅ ባማይ፣ ወቅቶላ ኩኩ ደዴ፣ ረመዳን ሱሌይማን አብዱ፣ ጉደታ ቦሩ ሸንጎራ እንዲሁም ከሽማግሌዎች ጎበና አሻካ ጃሞ እና ራጁ አብዱ ቱኔ፤ ከምሁራን ወልተጂ ቦጋሎ ባንጄራ እና ቦጂ ፈይሳ ቴቶ እንደሚሳተፉ፤
  • የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ቤህነን) አመራሮች የሆኑት አብዱረሂም ሃሰን አልበድሪ፣ ሀሊል ሙርሲል ጁማእ፣ አቡድ አህመድ መሃመድ፣ አዜን ያሲን ሆጄሊ፣ አብዱሰላም ሸንገል አልሃሰን እንዲሁም ዘሩቅ ሃምዳን አብደላ እና መደዊ አብዱረሂም አቡሃዚሞ የተባሉ ሽማግሌዎች እንደሚሳተፉ፤
  • የሲዳማ ነፃነት ንቅናቄ አመራሮች የሆኑት ዶ/ር ሚልዮን ቱማቶ፣ ይልማ ቻሞላ ጉጃ፣ ዋለልኝ ዋቀዮ ጋራሞ፣ ጊዴሳ ቡናቶ ዲዴዋ፣ በላይነህ ይንኩራ ዩማ፣ መንግስቱ ግራሼ ነጌሶ እና ዶ/ር አየለ አሊቶ እንዲሁም የሲዳማ ሃዲቾ የተባለ ድርጅት አመራር የሆኑት ፀጋዮ ፉኤ ኦኮቶ፣ ታሪኩ ዳዋሳ ዶኖሳ፣ ነጌሶ ሮባ እንሚሳተፉ፤
  • ከጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋህነን) ፓተር አማን ቸቢይ፣ ባሬ አጊድ ኡጅዋቶ፣ ኡቡንግ ኡሙድ ኙግዋ እና ዘሪሁን በየነ ወየሳ የተባሉ አመራሮች እንደሚካፈሉ፤
  • ከሶማሌ ክልል ያልተገለጸ ድርጅት አመራር የሆኑት ሃሰን ነገዮ ቱካሌ፣ መሃመድ አህመድ አደን፣ ዓብዲ አህመድ መሃመድ፣ ሃጂ ማሀመድ አው ሙሳ፣ ሳረ አለመር እንደውን፣ አሽረፍ ኡመድ ሙመድ፣ ፈይዛ ሃሺም መሃመድ፣ መሃመድ አህመድ ኢብራሂም እና ሳዮ ቦና ዓብዱላሂ እንዲሁም የሀገር ሽማግሎች፣ ወጣቶች እና ተዋቂ ግለሰቦች እንደሚሳተፉ፤
  • ከአፋር ክልል የአርዱፍ ፓርቲ አመራር የሆኑት መሀማድ ሃጂ ዓሊ፣ መሃመድ ሰዒድ ዓብደላ እና ሁሴን ሃሰን፤ የአፋር ህዝብ ፓርቲ (APP) አመራር የሆነው ሁሴን ደቶና እንዲሁም የአፋር ፍትህ እና እኩልነት ፓርቲ አመራር መሃመድ ዳውድ እንደሚሳተፉ፤
  • በስም ያልተገለጸ የፖለቲካ ድርጅት አመራር እንደሆኑ የተገለጹ ተሰማ ሁንዱማ ጎርፎ፣ ሰኚ ታደሰ ዴፋ፣ ዋገሪ አስፋው ዋቅጂራ፣ ሳኒ መጋላ ዳዲ እና ጎበና ቱሉ ቂጣታ የተባሉ አመራሮች እንደሚሳተፉ፤
  • ከትግራይ የባይቶና ፓርቲ አመራሮች እና ሳልሳይ ወያኔ የተባለ ድርጅት አመራር የሆኑት ዓብለሎም ገ/ሚካኤል፣ ሃይሉ ጎደፋይ ስዩም፣ ፀጋዝአብ ሽሻይ ገብረመድህን እና ሃይሉ ከበደ በስብሰባው እንደሚሳተፉ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
  • በሌላ በኩል ለስብሰባው ተሳታፊዎች በሚሰጥ አባል እና የጉዞ ወጪ በተመለከተ በህወኃት ጽ/ቤት አመራሮች መከካል ልዩነት እንዳለ የተገለፀ ሲሆን በዚህም አማኑኤል አሰፋ የተባለ አመራር በየቁኑ 500 ብር ታሳቢ በማድረግ የ15 ቀን እንዲከፈላቸው የሚል አቋም ያለው ሲሆን ኪሮስ ካሳሁን እና አለም ገ/ዋህድ የትራንስፖርት ብቻ ይከፈላቸው የሚል አቋም እንዳላቸው የተገኘው መረጃ ያሳያል። ከዚህ በፊትም የህወሓት አመራሮች “ኢትዮጵያን እናድን በሚል ፌዴራሊስት ሃይሎች የሚሏቸውን” ወጪያቸውን በመሸፈን መቀለ በመጥራት ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን አሁን የተጠራው ስብሰባ በፊት ከተደረገው ሰፊ ተሳታፊ የሚገኝበት እንደሆነ ተገልጿል።