የዛሬው ውይይት ግማሽ ሙሉ፤

በያሬድ ሃይለማርያም

ዛሬ የሕገ መንግሥት ትርጓሜ አስፈላነት ላይ የተካሄደውን የምሁሮች ውይይት በአንክሮ ተከታትየዋለሁ። እጅግ አስተማሪ ከመሆኑም ባሻገር በአገር ደረጃ ለእንዲህ ያሉ ውይይቶች የሚያመቹ መድረኮች መፈጠራቸውም ጥሩ ጅምር ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ይሁንና የውይይቱ ጠቀላላ ይዘት ሲታይ ከጀርባ የተሰራ ድርጅታዊ ስራ ውጤትም ይመስላል። ዛሬም ከድርጅታዊ ሽረባ ገና ነጻ እንዳልወጣንም ያሳያል።

ዋናው ጭብጥ እና ሙያዊ ምክር የተጠየቀበት ጉዳይ የሕገ መንግስት ትርጓሜ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም የሚለው ሆኖሳለ በውይይቱ ላይ ሲወቀጥ የዋለው ፍሬ ነገር ግን የአንዱ ወገን ብቻ ነው። የገዢው ፖርቲ ቀድሞ አቋም የያዘበት የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋል የሚለው ሃሳብ ብቻ ነው። ይህን ውይይት ሙሉ ሊያደርገው ይችል የነበረው ሁለቱንም፤ ትርጉም ያስፈልጋል እና ትርጉም አያስፈልግም የሚል አቋም የሚያንጸባርቁ ባለሙያዎች እኩል እድል ተሰጥቷቸው እንዲሟገቱ እና ሃሳባቸውን በዝርዝር እንዲያስረዱ የሚያስችል ቢሆን ነበር። አሁን ግን የሚመስለው ስለ ሕገ መንግስት ትርጓሜ ገዢው ፖርቲ ያቀረበውን የመፍትሄ ሃሳብ ምን ያህል የሕግ ምሁራኖች ድጋፍ እንዳለው ማሳያ እና ያንን አቋም በመደገፍ የቀረበ የሕግ ማብራሪያ ነው የሚመስለው።

መድረኩ የምክክር እስከሆነ ድረስ በግራና በቀኝ ያሉ ሃሳቦች ተፍታተው ቢቀርቡበት ከአስተማሪነቱም አልፍ ዲሞክራሲያዊና ነጻ የውይይት ባህልን ለማዳበር ያለውንም ቁርጠኝነት ያሳይ ነበር። ሃሳባቸው ልክም ይሁን፤ አይሁን በተለያዩ መድረኮች የሕገ መንግስት ትርጓሚ አያስፈልግም የሚል ጠንካራ የመከራከሪያ ሃሳብ ሲያቀርቡ የቆዬ የሕግ ምሁራኖች መኖራቸውን ልብ ይለዋል። ገሚሶቹም ጥሪውን ተቀብለው ምክረ ሃሳባቸውን በጽሑፍ አስገብተዋል። በቀጣዬቹ ውይይቶች ለእነኚህ ምሁራን ተመሳሳይ እድል ይሰጣል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ውይይቱ ግን ያስፈልገናልና መድረኩ ሊለመድ ይገባል።

One thought on “የዛሬው ውይይት ግማሽ ሙሉ፤

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.