ኢትዮጵያዊነት የሁሉም ድምር ውጤት ነው‼️

ስማ ስማ… ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነበር?ሀገር ነው? ቋንቋ ነው? ብሔር ነው? ባህል ነው? መሬት ነው? ዳር ድንበር ነው? ሜዳና ተራራ ነው? ሰው ነው? ህገመንግስት ነው?… ኢትዮጵያዊነት አንዳቸውም አይደለም። ከዚያ ይልቅ ከላይ የተጠቀሱት በሙሉ የኢትዮጵያዊነት አካል ናቸው። ኢትዮጵያዊነት የሁሉም ድምር ድምር ውጤት ነው።

ኢትዮጵያዊነት

አዎ ኢትዮጵያዊነት እንደ ራስ መሆን፥ ራስን መምሰል ነው። ይሄ ሰውኛ ባህሪ ነው። ኢትዮጵያዊነት ከዚህ ተፈጥሯዊ ባህሪ ጋር የተቆራኘ ነው። ሁሉም ሰው በተፈጥሮ በእኩል ዓይን መታየት ይፈልጋል። እንደ ወያኔ የድኩማኖች ስብስብ ካልሆነ በስተቀር የሰው ልጅ የራሱን የበላይነት በሌሎች ላይ ለመጫን አይሞክርም። ምክንያቱም ማንም ሰው በበታችነት እየተበደለ መኖር አይሻም። የበታችነትን ተቀብሎ መኖር የሚሻ ከሌለ የበላይነትን አምኖ የሚቀበል አይኖርም። ሌሎቹን በመጫን በሌሎች ጉዳት የራሱን ጥቅም ለማስከበር የሚሻ ሰው የዘረኝነት ፈንገስ የያዘው ነው።

በነገራችን ላይ የበላይነት ስሜት መንስዔው የበታችነት ስሜት ነው። የበታችነት ስሜት ያለበት ብቻ ነው በሌሎች አናት ላይ ዘሎ ፊጥጥጥ ማለት የሚሻው። ከዚያ በስተቀር ከሌሎች ጋር በአብሮነት ተከባብሮ መኖር የሰለጠነ ማህበረሰብ መገለጫ ነው። ይህን በአብሮነት የሚኖር ማህበረሰብ በባህል፣ ሃይማኖት፣ ጎሳ፣ ቋንቋ፣… እየከፋፈልክ እርስ በእርስ የምታጋጭ እና የምታናጭ ከሆነ አንተ ወያኔ ነህ። ወያኔነት በበታችነት እና የበላይነት ስሜት የሚያናውዝ የአስተሳሰብ በሽታ ነው።

ኢትዮጵያዊነት ማለት ደግሞ ከሁለቱ አሉታዊ አመለካከቶች በፀዳ መልኩ በእኩልነት ላይ የተመሠረተ አብሮነት ነው። ኢትዮጵያዊያን በአብሮነት የሚኖሩት የጋራ ሀገር ስላላቸው ብቻ አይደለም። ሀገሪቱ ራሷ የተመሠረተችው የተሳሰረ ህልውና ባላቸው ማህብረሰቦች ነው። ከእነዚህ ውስጥ አንዱን ማህብረሰብ ስትጨቁን ህመምና ጉዳቱ ሁሉም ማህብረሰቦች ጋር ይደርሳል።

ወያኔ “ከአማራ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ” ሲል ከሁሉም ቀድሞ “ከእኛም ጋር የምታወራርዱት ሂሳብ አላችሁ” ያላቸው ሱማሌው ሙስጠፌ ነው። በወያኔዎች ዘንድ አማራ እና ሱማሌ ምዕራብ እና ምስራቅ ተቃራኒ ፅንፍ ላይ የሚገኙ ማህብረሰቦች ናቸው። “እርስ በእርስ ቢተዋወቁ እንኳን አይተባበሩም” ብለው ያሰባሉ። ለእነዚህ ድኩማኖች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ማህብረሰቦች በሙሉ የስሜት ህዋሳቸው የተሳሰረ መሆኑ አይገባቸውም። ምክንያቱም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የተመሰረተችው የተሳሰረ ህልውና ባላቸው ማህብረሰቦች ነው ስንላቸው አይሰሙም። “የተሳሰረ ህልውና” ያላቸው ሲባል የእያንዳንዱ ማህብረሰብ መኖር እና አለመኖር ከሌሎች ሰላምና ደህንነት ጋር የተቆራኘ እንደ ማለት ነው።

“አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል” እንደሚባለው አማራ ሲመታ ሱማሌ ያመዋል። በአፋር ላይ የተሰበቀውን ጦር ኦሮሞ ይመክታል። በአጠቃላይ አንዱ ሲመታ ሌላኛው ያቆስላል። ሁሉንም አንድ ላይ አቅፋ የያዘችው ደግሞ ወይዘሪት ኢትዮጵያ ትባላለች። እሷ ላይ የተቃጣ ጥቃት እያንዳንዱ እና ሁሉም ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ይሆናል። በመሆኑም “ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ” ሆነ “አማራን አጠቃለሁ” ብለህ ስትነሳ እያንዳንዱን እና ሁሉንም ነው ያጠቃኸው። ምን ያደርጋል ታዲያ ስህተትህ የሚገባህ ዘግይቶ ነው። ስህተትህ ማጥቃትህ ብቻ አይደለም። አንዱን በማጥቃት ሁሉም ተባብሮ እንዲያጠቃህ መንገድ መክፈትህ ነው። ያልገባው ካለ ህወሓቶችን ይጠይቃቸው‼️

2 thoughts on “ኢትዮጵያዊነት የሁሉም ድምር ውጤት ነው‼️

  1. “ኢትዮጵያዊነት የሁሉም ድምር ድምር ውጤት ነው።” እስቲ እንዲ ንገርልኝ እነሱ እስኪበስሉ እኛ እኮ አረርን ከዚህ በኃላ ግን ለማረር ጊዜ የለንም ለመምረር ካሎነ በቀር። #በቃን

    Like

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.