ህወሓት እና ናዚ ምን አገናኛቸው?

ይህ ምስል በቆቦ ከተማ ከሚገኝ አንድ ሆቴል መኝታ ቤት  የህወሓት ታጣቂዎች ግድግዳ ላይ ጽፈውት የተገኘ ነው፡፡ ‹‹ብታምኑም ባታምኑም እኛ ትግራዋይ የዓለም ምርጡ የሰው ዘር (ፍጡራን)  ነን›› ይላል በግርድፉ ሲተረጎም፡፡ 

ናዚ በ20 ኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓና ሌላውን የአለም ክፍል የደም መሬት ያደረገ ጦርነት የቀሰቀሰው የጀርመን ህዝብ ከሌላው የተለየ ነው በሚል ፕሮፖጋንዳ ዜጎቹን በማደንዘዝ ነበር፡፡ እኛ የጀርመን ህዝቦች ‹‹አርያን›› ከተባለው ዘር ነው የመጣነው፡፡ ይህ ዘር ከሁሉም የበለጠ  (master race) ሲሆን፤ የዘር ጥራት የሌላቸው አይሁዶች፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የአዕምሮ ችግር ያለባቸው ሰዎች ፣ ጂፕሲዎች እና ሌሎችም ከምድረ ገጽ መጥፋት አለባቸው ያለው የናዚው ቁንጮ አዶልፍ ሂትለር  የአርያን ዘር አባል አይደሉም ያላቸውን ከ 6 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ሰዎች በዘግናኝ ሁኔታ እንዲጨፈጨፉ አደረገ፡፡ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት እስከ 90 ሚልዮን ሰዎች እንዲያልቁም ምክንያት ሆነ፡፡

ይህ ምስል በቆቦ ከተማ ከሚገኝ አንድ ሆቴል መኝታ ቤት  የህወሓት ታጣቂዎች ግድግዳ ላይ ጽፈውት የተገኘ ነው፡፡ ‹‹ብታምኑም ባታምኑም እኛ ትግራዋይ የዓለም ምርጡ የሰው ዘር (ፍጡራን)  ነን›› ይላል በግርድፉ ሲተረጎም፡፡    ጽሁፉ ናዚ  የጀርመን ህዝብ ከሌላው የተለየ ነው በሚል ፕሮፖጋንዳ ዜጎቹን ሲሰብክ እንደነበረ ሁሉ፤ ህወሓትም ትግራዋይ  ከዓለም የተለየ ዘር  እንደሆነ ታዳጊዎችን  ኮትኩቶ እያሳደገ እና እያደነዘዘ ስለመሆኑ ተጨባጭ ማሳያ ነው፡፡

ህወሓት በአማራና በአፋር ክልል ያሰማራቸው ታጣቂዎች ከናዚ ያልተናነሰ ግፍ ፈጽመዋል፡፡ በጅምላ ከጨፈጨፏቸው የአማራና የአፋር ንጹሃን ባሻገር ልክ እንደ ናዚ በተለያዩ ከተማዎች   ያገኟቸውን የአዕምሮ ህመምተኞች የመኖር መብት የላቸውም በሚል መነሻነት በስናይፐር አነጣጥረው በመተኮስ ገድለዋል፡፡ ይህ ‹‹የተለየን ዘር  ነን›› የሚለው አመለካከት የህወሓት ታጣቂዎች በወረራ በያዟቸው  ከተማዎች በሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ግድግዳ ላይ በተጻፉ ጽሁፎች በሰፊው ተንጸባርቋል፡፡ ይህ አመለካከት ‹‹ሳይቃጠል በቅጠል›› ሊባል የሚገባው ነው፡፡  በኢትዮጵያ የተሳካ ብሔራዊ ውይይት ማድረግ ካስፈለገም እንደዚህ አይነቱ ናዚያዊ አመለካከት ከስሩ መነቀል አለበት ! 

One thought on “ህወሓት እና ናዚ ምን አገናኛቸው?

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡