የትግራይ እናቶች እንደ ሚልዮን ወጥተው የቀሩ ልጆቻችሁን የምትጠይቁበት ሰዓት አሁን ነው !

ገና ሕይወትን በቅጡ ያላጣጣመ ወጣት ነው – ሚልዮን በየነ አስፍሃ ይባላል፡፡  አሸባሪው ቡድን በኢትዮጵያ ጥምር ጦር ክፉኛ ተደቁሶ ሲፈረጥጥ ከአጣዬ ወጣ ብሎ በድሮን አመድ ከሆነው በኦራል የተጫነ መድፍ አጠገብ ወድቅ የተገኘው መታወቂያው ጥቅርሻ ተራግፎ የሚነበበው መረጃ  እንደሚያስረዳው በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ነበር፡፡ 

ሚልዮን እንደ አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ወጣቶች ትምህርቱን አጠናቆ ለፍተው ደክመው ለቁም ነገር ያበቁትን ቤተሰቦቹን የመደገፍ ህልም ይኖረው ይሆናል ?  በተመረቀበት የሙያ መስክ በማገልገል ራዕዩን የማሳካት  ከፍተኛ ምኞትም ሰንቆ እንደነበር መገመት ይቻላል?  ይሁንና አሸባሪው የህወሓት ቡድን አንተ የተማርክበት መስክማ በአማራና በአፋር ክልል ለምንፈጽመው ዘረፋ ማሽን ለመፍታት ያግዛል፤ ያም ባይሆን ክላሽ አንግበህ ‹‹ጠላትን ትደመስሳለህ›› ብሎ ‹‹በግዳጅ›› ወደ ግንባር እንዲዘምት አድርጓል፡፡

የወጣቱ ሚልዮን ረጅም ጉዞ ግን ከአጣዬ ወጣ ብሎ በበላይነሸ አመዴ ተቋጭቷል፡፡ ከከሰለው መድፍ ጋር ከንቱ መስዋዕትነት የከፈለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እጣ ፈንታ ብዙዎች የትግራይ ወጣቶች በአማራና በአፋር ክልል አጋጥሟቸዋል፡፡ ይህን ለትግራይ እናቶች ማርዳት የፈራው ወራሪ ኃይል ደግሞ ዛሬም ‹‹እጅህ ከምን፤  ልጆቻችንንስ የት አደረስክ? ››  እንዳይባል ጦርነቱን መቀጠልና ማራዘም መርጧል፡፡ የትግራይ እናቶች ሆይ እንደ ሚልዮን ወጥተው የቀሩ ልጆቻችሁን የምትጠይቁበት ሰዓት አሁን ነው !