ኢትዮጵያ ላይ የተደቀነው ፈታኝ አደጋ፦ HR 6600 Bill!


በኒው ጀርሲው ኮንግረስማን ሚስተር ማሊኖውስኪ የተረቀቀው H.R 6600[1] በኢትዮጵያውያን እና በኢትዮጵያ መንግስት የተጀመረውን የሰላም ጥረት በሚከተለው መልኩ በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንደሚጥል በማስፈራራት ተነስቷል ።

ህጉ ከጸደቀ በሀገርና በዜጎች ላይ የሚደርሰው ጉዳቶች ምንድናቸው?

1. ደኅንነት፦ የጸጥታ ዕርዳታን ማገድ ኢትዮጵያን የሚያዳክም እና በአፍሪካ ቀንድ አለመረጋጋትን ይፈጥራል።

2. ፋይናንስ፡ በብድር፣ በፋይናንሺያል ጥቅማጥቅሞች እና በቴክኒካል ድጋፍ ኢኮኖሚያዊ የእድገት እድሎችን መሻር። ቢል ኤች አር 6600 በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ዕርዳታ የሚገድብ ወይም የሚገድበው ለዚህ የገንዘብ እገዳ ሌሎች አጋሮችን እና አገሮችን ማደራጀት እንዳለበት አጥብቆ ይናገራል።

3. ኢንቨስትመንት፡- ኢትዮጵያን ከዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽኖች በመከልከል የዩናይትድ ስቴትስ ኢንቨስትመንቶችን እና የምንዛሬ ልውውጦችን መከልከል።

4. መሠረታዊ መብት፡ ሕጉ መሠረታዊ የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን እንቅስቃሴን ለመከልከል እና የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች እና የኢትዮጵያ አጋሮች የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመደገፍ በገንዘብም ይሁን በርዕሰ ጉዳይ እውቀት ለመለዋወጥ የሚሹ ባለሙያዎችን ለመቅጣት ያለመ ነው።

5. ኢሚግሬሽን፡ ሕጉ በኢትዮጵያውያን ላይ የኢሚግሬሽን ክልከላዎችን የሚያስፈጽም ሲሆን ይህም ግጭቱን ደግፏል ተብሎ ለተከሰሰ የውጭ ሰው ወይም አካል ከማዕቀብ እና ከንብረት መከልከል በተጨማሪ የቪዛ አመልካቾችን እና የወደፊት የብዝሃነት ቪዛ ማመልከቻዎችን መሻርን ይጨምራል።

ይህ ህግ ከጸደቀ የሀገሪቱ ኢኮኖሚን በከፍተኛ መልኩ በማድቀቅ በእያንዳንዱ ዜጋ ኑሮ ላይ ከባድ ጫና በማድረስ እጅግ አደገኛ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑን ፣ከዚሁ ጋር የሀገርን ደህንነት ከፈተኛ ተጋድሎ የሚፈጽሙ እንደ ፋኖና ሌሎች ያሉ አደረጃጀቶችንም ጭምር መርዳት እንዳይቻል የሚያደርግ መሆኑን በመገንዘብ ማንኛውም ሀገሩን የሚወድና የወገኑን ካለበት መከራ የባሰ የከበደ ችግር ውስጥ እንደይገባ ሳይዘገይ የሚቻለውን ማድረግ ይጠበቅበታል!!

ይህን አደገኛ ህግ እንዳይጸደቅ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ማህበራዊ አደረጃጀቶች በፊርማ ማሰባሰብና በተለያዩ መንገዶች ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ሲሆን በተቃራኒው እጅግ በሚያሳፍር ሁኔታ በመንግስት ላይ ቅሬታ አለን የሚሉ ኢትዮጵያውያን የህውሃትና ሌሎች ፅንፈኞች በቀደዱት ቦይ ገብቶ ይህ ቢል አንዲጸድቅና በሀገራቸው ላይ ገደብ እንዲጣል በሰልፍና በሜዲያ ፕሮፓጋንዳ ለመደገፍ መነሳታቸውን እየተሰማ ነው።

በመንግስት ላይ ቅሬታና ከዚያ ላይ መከፋት መኖሩ አይካድም ።ነገር ግን በዚህ ምክንያት ይህን ህግ እንዲጸደቅ አይንን ጨፍኖ መደገፍ ታሪክ የማይረሳው የባንዳነት ስራ መሆኑን ምንም ማስተባበያ ሊቀርብበት አይችልም!!

ስለዚህም የኢትዮጰያ ህዝብ የወቅቱ ጦርነት ወያኔ በሰሜኑ ዕዝ በማጠቃት በሰማ ጊዜ ሆ! ብሎ እንደተነሳ፣ በኋላም በአማራና በአፋር ክልል መወረርና ጊዜ ወረራውን ለመቀልበስ በአልህና በቁጭት እንደተነሳ፣ ታላቁ የአድዋ በዓል በምኒሊክ አደባባይ እንደማይከበር በሰማ ጊዜ በአንድ ሌሊት በቁጭትና በእልህ እንተነሳ በዚህ አጭር ጊዜ የHR 6600 bill እንዲጸድቅ ባንዳዎች የተነሱበትን
አጥፊ ዓላማ በከፍተኛ ቁጭትና እልህ የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ የመቀልበስ ታሪካዊ ሃላፊነት ወድቆበታል።
ስለዚህ ይህ የሀገርና የህዝብ ጥቃት የሚከነከነው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ መነነሳት ይኖርበታል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቧን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅልን።

One thought on “ኢትዮጵያ ላይ የተደቀነው ፈታኝ አደጋ፦ HR 6600 Bill!

  1. Abboo Waqinii Ethiyoophiyaa Siif Hintasisiin , Waan Namatti Tolu keessaa Ethiopian Yoomillee Yoo ta’ee ,Haalumaa Kamuu Keessatu Qamaa Ishee Tuqee kan Salphatee malee kan milka’eef hin argine ,Siif Hin tatuu ,Nutu Keesoo Keenya Cimuu, Walidhagefachuu, iddoo walii kennuu yoo jiratee Maqaa Rabbitiin wantii takkalee hin ta’uu

    Like

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.