የሰው ልጅን ማቃጠል ለወያኔዎች ሰርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል!

የትግሬ ወራሪ የአጀንዳ ድርቅ ገጥሞት ነበር። “ተከበናል” ወዘተ የሚለው ፕሮፖጋንዳ እየደረቀበት ነበር። ቤንሻንጉል ላይ የተፈፀመው የፕሮፖጋንዳ መና አወረደለት። ያ ጉዳይ እንደተሰማ ወዲያውኑ አማራ ክልል አስመስለው ሰሩት። አማራ ላይ ሌላ የስድብና ዘለፋ የሚያወርዱበት አጀንዳ ሲያገኙ በየሚዲያው ዘለሉ። “አይ አማራ ክልል አይደለም” ሲባል ትንሽ ጋብ አድርገውት ቆዩ። ትንሽ አሰላስለው “ቤንሻንጉል ነው። ያው ነው አማራ ክልል በሉት” ብለው ቀጠሉ። ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች እንደፈፀሙት ሲነገር “ያው የአማራ ኃይል ማለት ነው” ብለው ቀጠሉ። መንግስት አወገዘ። መንግስት ያቋቋማቸው የሰብአዊ መብት ተቋማት አወገዙ። “አንሰማም፣ አናይም” ብለው ምንም እንዳልተፈጠረ አጀንዳውን ቀጠሉ።

ደብረፅዮን ማታ የተናገረውን፣ ጠዋት ትንሽ ቀንሰው እንደ አዲስ ያቀርቡታል። ትናንት የወጣውን መግለጫ ዛሬ ትንሽ እርማት አድርገውበት ያወጡታል። እያንዳንዱ ተላላኪና ጫጩት ፓርቲ መግለጫ እንዲያወጣ ታዘዘ፣ እያንዳንዱ ማሕበር ውግዘት እንዲያወርድ ተደረገ። አንዴ ብቻ ስለማይበቃ የእያንዳንዱን መግለጫ ትንሽ ቀየር አድርገው ደግመው ያስተላልፉታል። ሁሉም መግለጫ በተለያዩ የውጭ ቋንቋዎች ተተርጉመው ለውጭ ተቋማት፣ ለኤምባሲዎች፣ ለሚዲያዎች፣ ለግለሰቦች ደርሷል። ችግሩ የዩክሬኑ ጦርነት ነው።

የዩክሬን ጦርነት “ሸፈነብን” ብለው ስላሰቡ ብዙ ርቀት ሄዱ። እነ ቴዎድሮስ አድሃኖም ገቡበት። የወተወቷቸው የአሜሪካ ሴናተሮች ገቡበት። ትግሬ ብቻ ሲሞት ብቅ የሚሉት ማቲያስ ብቅ ብለው በርካታ የሀሰት ፕሮፖጋንዳን እውነት አድርገው ወስደው ተናገሩ።

ይህ ሁሉ የሚያሳየው የትግሬ ወራሪ የአጀንዳ ድርቅ ላይ እንደነበር ነው። የተቃጠሉትን የአጀንዳቸው ሻማ አደረጓቸው። ደስታቸው ወደር አጥቷል። እያንዳንዷን ጉዳይ እየበለቱ እያቀረቡ ነው። ትህነግ ያዋቀረው የፕሮፖጋንዳ ቲም “ሌላውን ነገር ትታችሁ የተቃጠሉት ላይ አተኩሩ” ተብሏል። ሁሉም ነገር ወደ ቤንሻንጉል ተብሏል። በዚህ ፕሮፖጋንዳ በዋነኛነት አጥቂው አማራ እንደሆነ፣ ጉዳዩን የፈፀሙት የሌሎች ፀጥታ ኃይሎች ቢሆኑም ቅሉ የአማራ አስተሳሰብ ተደርጎ፣ ከዚያም ሲያልፍ አማራ አደረገው ብለው ድርቅ እንዲሉ ትዕዛዝ ተላልፏል። ፌስቡከኛው፣ ሚዲያው፣ ፓርቲው፣ ማሕበሩ ሁሉ ይህን አጀንዳ ይዞ እንዲሰራ ተብሏል። መሃል አገር ያሉ ሚዲያዎች፣አክቲቪስቶችና አጋር ሚዲያዎቻቸው በሙሉ ከዚሁ ላይ አተኩሩ ተብለዋል። ማቲያስ ድረስ የደረሰው የትህነግ የሸቀጥ ፕሮፖጋንዳ አላማው ሁለት ነው። አንደኛ በቅርቡ የተጋለጡበት ሰቅጣጭ የሰብአዊ ወንጀል እንዲሸፈን ነው። ኢሰመኮ የትግሬ ወራሪ በአማራና አፋር ክልሎች የፈፀመውን ወንጀል ባጋለጠው ቀን ነው ይህ አጀንዳ የመጣው። በሁለተኛነት በቀጣይ ሊከፍቱት ላሰቡት ጦርነት ሽፋን መሆኑ ነው። በፕሮፖጋንዳው ሄደውበት ቀጥለው በወረራ ይመጣሉ።

ቤንሻንጉል ውስጥ የተፈፀመው ለትግሬ ወራሪ ታጣቂ በእየቀኑ እየተነገረ ነው። “ኢትዮጵያ ውስጥ ከእነ ነፍሳቸው ለሚቃጠሉት ትግሬዎች ደርሰን ነፃ ልናወጣቸው ይገባል” እየተባለ ነው። በድምፅ ማጉያ ለሕዝቡ እየቀረበ ነው። በየሚዲያዎቻቸው አብዛኛው የአየር ሰዓት ይሄው ጉዳይ ሆኗል። ራዲዮ ጣቢያዎቻቸው ከዘግናኝ ጥላቻ ጋር ሕዝብን እየጋቱት ነው።

ተራበ ያሉትን ሕዝብ ጉዳይ ረስተውታል። ተከበብን የሚሉትን ጋብ አድርገውታል። ሌላውን ሌላውን ረስተውታል። የተቃጠሉትን የፕሮፖጋንዳ ስንቅ አድርገው እየዘለሉ ነው። ሌሎች ቢቃጠሉላቸው ደስታውን አይችሉትም። ምን አልባትም ራሳቸው አቃጥለው ሁሉ ተጨማሪ ፕሮፖጋንዳ ይከፍታሉ። በተቃጠለ ሰው ይህን የመሰለ ንግድ ይሰራሉ። ሰሞኑን ደስታ ነው። ጭፈራ ነው። “ቢንጎ” ብለው ፕሮፖጋንዳውን ተያይዘውታል።

ሌላውን ሁሉ እርሱት ብለው በተቃጠሉት ላይ አተኩረዋል። በተቃጠሉት ላይ ፖለቲካ፣ ንግድ ይዘውታል። ለእነሱ የተቃጠለው የሚያጠግብ ፕሮፖጋንዳ ነው። በየቀኑ ሕዝብን የሚያጎርሱት አጀንዳ ሆኗል።

እነሱ በሰው ልጅ ላይ በምድር የተፈፀመውን ሁሉ እንዳልፈፀሙ መሰል አጀንዳዎችን ሲያቀርቡ ሰብአዊ መስለው ነው። የፖለቲካ ሸቀጥ መስራትን ያውቁበታል። ጳጳስ ሆነ ካድሬ ልዩነት የላቸውም። ምሁር ወዘተ ልዩነት የላቸውም።

3 thoughts on “የሰው ልጅን ማቃጠል ለወያኔዎች ሰርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል!

 1. To me, the most interesting thing is the simplicity of the framework. Bezmenov lays out a four-step framework for ideological subversion on a national scale, as practiced by the USSR around the world. This is intentional, directional, change that occurs out in the open. The greater openness of some societies makes them susceptible to this process.

  Demoralization. For this step in the process, 15 – 20 years are needed. That is the amount of time required to educate a generation. Helping along the way are media and teachers who have become sympathetic (consciously or unconsciously) to the theoretical causes of the subverting nation. Bezmenov claims that the USSR was surprised at how easy this phase was in the US.
  Destabilization. Following the earlier phase, this is a two to five year period to change the target country’s foreign relations, defense, and economy.
  Crisis. Perhaps six weeks of chaos as a climatic turning point.
  Normalization. This stage changes the appreciation of what the status quo looks like. Bezmenov’s description of this phase also includes military take over.
  This is one of his charts of the process in more detail (from a grainy 1980s video that’s hard to read, I know).

  Yuri Bezmenov – How to Subvert a Nation

  Like

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.