በነገሠ ጉተማ ኢትዮጵያ የዘውጎችና የባህሎች ውቅር ኢትዮጵያ ታድላለች። ከ87 ባላነሱ ዘውጎች ተሞልታለች። በባህልና በቋንቋ ቀለሞች አሸብርቃለች። እንደኢትዮጵያ የታደሉ ሀገሮች በዓለም ላይ በጣም ጥቂቶች ናቸው። ባለብዙው ዘውጎችና ባሕሎች የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በየጊዜው የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች አብሮ ተቋቁሞ፣ ተከባብሮ ፣ተጋብቶና ተዋልዶ፤ አብሮ በልቶ፤ አብሮ ጠጥቶ፤ አብሮ ተርቦ፤ አብሮ ስቆ፤ አብሮ አልቅሶ፤ አብሮ ጨፍሮ፤ አብሮ ሞቶ፤ አብሮ ተቀብሮ፤ አብሮ … Continue reading ዘረኝነት እና ኢትዮጵያ፦ በብሔር ላይ የተመሠረተው የፌደራሊዝም ስርዓት ዘረኝነትን ያስቀጥላል!
Author: Negesse Gutema
የህወሐት ገንዳ፦ “ያረጀን ውሻ አዲስ ዘይቤ ማስተማር አይቻልም!”
ህወሓት ግን መቼ ነው የምትለወጠው፥ የምትማረው? ከነገሠ ጉተማ “ያረጀን ውሻ አዲስ ዘይቤ ማስለመድ/ማስተማር አይቻልም” ሁላችንም ህወሐት በለውጡ አምና ያለፈውን ጥፋትዋን ተቀብላ እንደ አንድ ቤተሰብ ወደፊት ብንራመድ እንመኛለን። እንደዚያ ቢሆን ኖሮ አንድ ትልቅ ችግር ተቃሎ ሌሎች ችግሮችን በአንድነት መፍታቱ ላይ ማተኮር በቻልን ነበር። የህወሐት “አሻፈረኝ” ማለት መታየት ያለበት ከቀየሰችው ጎዳና እና ለመተግበር ከምትፈልገው ራዕይ አንፃር ነው። … Continue reading የህወሐት ገንዳ፦ “ያረጀን ውሻ አዲስ ዘይቤ ማስተማር አይቻልም!”
“ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት” እና አምባገነንነት በኢትዮጵያ ያስከተለው ሰቆቃ!
መግቢያ ይህ ፅሁፍ ስለአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ምንነትና አመጣጥ እንዲሁም ባለፉት 40 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕልውናና አድገት ላይ ያሳደረውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የባህላዊ ተጽእኖ ይዳስሳል። በማጠቃለያውም ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ዴሞክራስያዊ ድርጅቶች ያለባቸውን ታሪካዊ ኃላፊነት በአንድነት እንዲወጡ ይጠይቃል። በመጨረሻም – ጠለቅ ያለ ምርመራ ማድረግ ለሚፈልጉ በማጣቀሻዎች ሥር ያሰፈርኳቸውን መፃሕፍትና ድረገጾች መመርመር ጠቃሚ ነው። ነገሠ ጉተማ ካርል ማርክስ፣ ቭላድሚር ሌኒን … Continue reading “ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት” እና አምባገነንነት በኢትዮጵያ ያስከተለው ሰቆቃ!