ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? “የጋራ አብሮነት ውጤት ነው!” በምን ይገለፃል? “በአደዋ!” 

ይህ ፅሁፍ “ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? በምን ይገለፃል?” በሚል ከአዲስ አዳምስ ለቀረበልኝ ጥያቄ የሰጠሁት ምላሽ ነው፡፡

“ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? በምን ይገለፃል?” ለሚለው ጥያቄ የተሰጡ ምላሾች (ከአዲስ አድማስ ድረገፅ የተወሰደ)

ኢትዮጵያዊነት ዜግነት ነው፡፡ ዜግነት ደግሞ በአንድ የተወሰነ ሀገር ውስጥ የጋራ አብሮነትን የሚያሳይ ነው፡፡ አንድ ጆሴ ኦርቴጋ የሚባል ፖርቹጋላዊ ፀሐፊ አለ፡፡ ይህ ጸሐፊ፤ ሀገር የሚመሰረተው በምን ላይ ነው? ሲል ይጠይቃል፡፡ ሀገር የሚመሰረተው በእሱ አተያይ፣ በጋራ አብሮነት (common future) ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነትም የጋራ አብሮነት ውጤት ነው፡፡ የጋራ መሰረት ያለን፣ የጋራ ጉዳይ ያለን፣ ለወደፊትም የጋራ እድል ያለን ሰዎች ነን፤ በኢትዮጵያዊነት ስር ነው የተሰባሰብነው፡፡፡ ይሄ ማለት ዛሬ እና ትናንት ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ነገና ለወደፊትም አብሮ ለመኖር የጋራ ስምምነት ያለን ህዝቦች ነን፡፡ 

የአሁኗ ኢትዮጵያ እንዴት ተመሰረተች? የሚል ጥያቄ ከተነሳ ደግሞ የአሁኗ የቆመችው በአፄ ምኒልክ ዘመን ነው፡፡ አሁን ላይ ላለው የአንድነት ክፍፍልና የእርስ በእርስ መጠላለፍ መሰረት የሆነውም ያንን የኢትዮጵያ አመሰራረት የምንረዳበት መንገድ ለየቅል መሆኑ ነው፡፡ ግማሹ በቅኝ ግዛት (ወረራ) አይነት የተፈጠረች ነች ይላል፤ ግማሹ ደግሞ ቀድሞ የነበረችውና ኋላ ላይ በታሪክ አጋጣሚ የተበታተነች ኢትዮጵያን መልሶ አንድነቷን ማስጠበቅ ነው ይላል። በዚህ መሃል ግን የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች፣ ወደ ምስራቅ አፍሪካ መስፋፋት ሲጀምሩ፣ በወቅቱ ሸዋ፣ ወሎ፣ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ትግሬ በተባሉት አምስት ግዛቶች ላይ ብቻ ተወስና የቆየችው ኢትዮጵያ፣ ሀገራዊ ኃይልና አንድነት ለማጠናከር፣ ወደ ደቡብ፣ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫ መስፋፋት ጀመረች፡፡ 


አፄ ምኒልክ፤ በሉአላዊነት ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመመከት፣ ሁሉም በጋራ መቆም አለባቸው ከሚል መነሻ ነው መስፋፋትን ያደረጉት፡፡ በዚህ መሃል ግጭት ተፈጥሮ የብዙ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል፡፡ ይሄ ክስተት ነው፡፡ ዛሬ አንድ ሆኖ የሚታየው አብዛኛው ሀገር፣ አሁን ላይ የያዘው ቅርፅ በእንዲህ አይነት ክስተቶች አልፎ የመጣ ነው፡፡ የዚህ አይነት የማሰባሰብ ውጤት የታየው በአድዋ ጦርነት ላይ ነው፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በግልፅ ለአንዲት የጋራ ሉአላዊ ሀገር ተዋድቀዋል፡፡ ስለዚህ አድዋ የኢትዮጵያዊነት ታሪክ ነው፡፡ አድዋ ላይ የምናየው ኢትዮጵያዊነትን ነው፡፡ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች፣ በጋራ የሉአላዊነት አደጋን የቀለበሱበትና አብሮነታቸውን ያጠናከሩበት፣ ወደፊትም በነፃነት ለመኖር የተስማሙበትና መስዋዕትነት የከፈሉበት፣ ሁሉም ለወደፊት አብሮነታቸው አሻራቸውን ያሳረፉበት ነው አድዋ ማለት፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዊነት ለኔ አድዋ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊነት ማለት በአብሮነት፣የወደፊት ነፃነትን አስከብሮ፣ በጋራ ለማደግ የመስማማት ውጤት ነው፡፡ በዚህ መንፈስ ነው ነፃነታችንን አስከብረን ዛሬ ላይ የደረስነው፡፡ ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ቅኝ ግዛት ውስጥ የወደቁበት ሚስጥሩ፣ ይሄን አብሮነት ማጣታቸው ነው፡፡ ስለዚህ ለኔ ኢትዮጵያዊነት ማለት በወደፊት አብሮነት ላይ የተመሰረተ አንድነት ነው፡፡ በኢትዮጵያዊነት ነው ከቅኝ ግዛት ነፃ የሆንነውና ራሳችንን አስከብረን የኖርነው፡፡ 

የኢትዮጵያ አንድነትን ለማምጣት ብዙ ዋጋ ተከፍሏል፡፡ ብዙ ጭፍጨፋ ተፈፅሟል፡፡ ይሄ ግን እኛ ብቻ ሳንሆን  ሰልጥነዋል የተባሉ ሀገሮችም የዛሬ አንድነታቸውን ያገኙት፣ በእንዲህ ያለውና ከዚህም በከፋ ሂደት ነው፡፡ አኖሌ ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋ፣ የኢትዮጵያ አንድነት በሚመሰረትበት ሂደት ውስጥ የተፈጠረ ነው፡፡ አኖሌ ላይ ወገኖቻቸው የተጨፈጨፉባቸው ሰዎች ናቸው፣ አድዋ ላይ ለጋራ ነፃነት የተዋጉት፡፡ አድዋን ያለ ኦሮሞ ብሔር ተሳትፎ ማሰብ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም አብዛኛው የአፄ ምኒልክ ወታደር ኦሮሞ ነው፡፡ 

አሁን የሚንጸባረቀው  የመበደል ስሜትና የብሔርተኝነት ስሜትም ሂደት የፈጠረው ነው። በየትኛውም ተመሳሳይ የታሪክ አጋጣሚ ውስጥ ባለፈ ሀገር ይሄ ይፈጠራል፡፡ ለምሳሌ ፈረንሳይን ማንሳት እንችላለን፡፡ ይሄ የመበደል (ብሔርተኝት) ስሜትና የአንድነት ስሜትን የማራመድ ጉዳይ አዲስ ክስተት ሳይሆን ሊፈጠር የሚችል መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ልሂቃን እንደሚሉት፤የሀገር አብሮነትን ለማስጠበቅ፣ ይሄን አይነቱን የበደለኝነት ስሜት መዘንጋት ያስፈልጋል፡፡ አሰቃቂ ክስተቶችን መዘንጋትና አስተማሪ ወይም በጎ የሆኑትን መሰብሰብ ያስፈልጋል፡፡ እኛ ሀገር ያለው የብሔርተኝነት ስሜት መሰረቱ የበደለኝነት ስሜት ነው፡፡ ስለዚህ ይሄን መዘንጋት ያስፈልጋል፡፡ በአንድነት ጎራ ደግሞ የግድ ኢትዮጵያዊ አንድነትን መቀበል አለብን ብሎ መጫን አያስፈልግም፡፡ ኢትዮጵያዊነትን ከእንግዲህ ወዲህ፣ ፈቅደን መርጠን የምንወስደው እንጂ በግድ የሚጫንብን መሆን እንደሌለበት ማስተዋል አለብን። 

የብሔርተኝነቱና የአንድነቱ ጎራ ግጭት በዚህ መንገድ መታረቅና የጋራ የወደፊት አብሮነት መታሰብ ይኖርበታል። የበደለኝነት ስሜትን ትቶ አንድነትን ለማሰብ የአኖሌን ጭፍጨፋ ዘወትር ማንሳቱን ትተን፣ አንድ ያደረገንን አድዋን መዘከር አለብን፡፡ በጎ የታሪክ ገፅታችንን ማጉላት ይገባናል። የቀድሞ ታሪካችን ላይ ቆዝመን አንድነታችንን መሸርሸር ትተን፣ በወደፊት አብሮነታችንና የጋራ ራዕይ ላይ የተመሰረተ የጋራ አንድነትን ለመፍጠር መጣር አለብን፡፡ የፖለቲካ ሃይሎችም አቅጣጫቸው፣በወደፊት የጋራ አብሮነት ላይ የሚያጠነጥን መሆን አለበት፡፡ አሁን ልዩነቶችን ማጉላት ላይ ነው ያተኮርነው፡፡ 

ዛሬ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሲዳማ፣ ትግሬ እያልን እርስ በእርስ የምንከራከረው፣ የጋራ ጉዳይ፣ የጋራ አገር ስላለን ነው፡፡ ክርክሩ ራሱ የተመሰረተው በጋራ ጉዳያችን ላይ ነው፡፡ አሁን ማተኮር ያለብን “ለወደፊት በጋራ እንዴት እንኑር” በሚለው ጉዳይ ላይ ነው፡፡ በዚህ መንገድ እየከረረ የመጣውን ልዩነታችንን ማስታረቅ እንችላለን፡፡ 

ስዩም ተሾመ (የዩኒቨርሲቲ መምህር)

*****

ከእኔ ጋራ ሌሎች ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፣ ዶ/ር ንጋት አሰፋ፣ ያሬድ ሹመቴ እና ዳንኤል ብርሃኔ ለጥያቄው ምላሽ ሰጥተውበታል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ይህን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ! 

Advertisements

​ኢትዮጲያዊነትን መገንባትና ማፍረስ: ከአፄ ሚኒሊክ እስከ መለስ! 

የኢህአዴግ መንግስት ትላንት ነሃሴ 26/2009 ዓ.ም “የፍቅር ቀን” ብሎ አስደመመን። በቀጣይ ቀናት ደግሞ “የአገር ፍቅር ቀን”፣ “የአንድነት ቀን” እና “የኢትዮጲያ ቀን”  እያለ ሊያስገርመን ተዘጋጅቷል። “የአንድነት ቀን” የሚከበርበት መሪ ቃል “ኢትዮጵያዊ ኩራቱ ህብረ-ብሄራዊነቱ” የሚል ነው። “የሀገር ፍቅር ቀን” መሪ ቃል “እጃችን እስኪሻክር እንሰራለን ምክነያቱም ኢትዮጵያን እንወዳታለን” የሚል ሲሆን “የኢትዮጲያ ቀን” ደግሞ “እኛ ኢትዮጵያውያን የጥቁር ህዝቦች ተምሳሌት ነን” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገልጿል። በእርግጥ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የዘመን መለወጫን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ኢትዮጲያዊነትን፣ አንድነትንና የሀገር ፍቅርን ለማስረፅ ጥረት ማድረጉ እንደ በጎ ጅምር ሊወሰድ ይችላል። በፅንሰ-ሃሳብ ደረጃ ሲታይ ግን የኢህአዴግ መንግስትን ከፋፋይነት እና ፀረ-ኢትዮጲያዊነት በግልፅ የሚያሳይ ነው። 

ከለይ ለተጠቀሱት እያንዳንዱ ቀን የተሰጠው መሪ ቃል፣ እንዲሁም በመርሃ ግብሩ የተዘረዘሩት ተግባራት አንድነትን፣ የሀገር ፍቅርን እና ኢትዮጲያዊነትን አያንፀባርቁም። ለምሳሌ፣ በመርሃ ግብሩ መሰረት፣ ሀገራዊ አንድነትን ለማንፀባረቅ ከሚከናወኑ ተግባራት ውስጥ “ትምህርት ቤቶችን እና የስራ ቦታዎችን በጋራ ማጽዳትና ማደራጀት፣ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን በአብሮነት ስሜት በጋር ማከናወን፣ እንዲሁም በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎችን መጎብኘት” የሚሉት ተጠቅሰዋል። በተቀሩት ሁለት ቀናት የሚከናወኑት ዝርዝር ተግባራት ደግሞ ከመሪ ቃሉ የባሰ አስቂኝና የተሳሳቱ ናቸው። በአጠቃላይ፣ “የአንድነት ቀን”፣ “የሀገር ፍቅር” እና “የኢትዮጲያ ቀን” በሚል የተዘጋጀው መርሃ ግብር የኢህአዴግ መንግስት የሚከተለውን የተሳሳተ የፖለቲካ አቅጣጫ በተጨማሪ በስልጣን ላይ ያለው ቡድን ያለበትን ስር የሰደደ የዕውቀት እጥረት (knowledge deficiency) በግልፅ ያሳያል። ለምን እና እንዴት የሚለውን ከዚህ ቀጥሎ በዝርዝር እንመለከታለን። 

የሰው ልጅ አስተሳሰብ በወደፊቱ ግዜ ላይ የተመሰረተ ነው። ትላንትን የሚያስተወሰው የነገ ሕይወቱን ለማስተካከል ወይም ለማሻሻል ነው። ዛሬ ላይ የሚፈፅመው ተግባር ነገን ታሳቢ ያደረገ ነው። ምክንያቱም፣ ሰው የሚኖረው በወደፊት እና ለወደፊት ነው። “የሰው ልጅ የሚኖረው በተስፋ ነው” ወይም ደግሞ “Human being lives primarily in the future and for the future” የሚለው አባባል ይህን የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ይገልፃሉ። ስለዚህ፣ ከወደፊት ሕይወቱ የተነጠለ ወይም ተያያዥነት የሌለው ነገር ለሰው ልጅ ስሜት አይሰጥም። በዚህ መሰረት፣ ሀገራዊ አንድነት፥ ፍቅርና ዜግነት ትርጉም የሚኖራቸው በዜጎች የወደፊት ሕይወት ውስጥ ፋይዳ ሲኖራቸው ነው። በወደፊት ሕይወታችን ውስጥ ፋይዳ ከሌላቸው ግን ዛሬ ላይ ዋጋ አንሰጣቸውም። በቀጣይ ቀናት የሚከበሩት የአንድነት፣ የሀገር ፍቅር እና የኢትዮጲያ ቀናት ከዚህ አንፃር መታየት አለባቸው። 

ብዙዎቻችሁ እንደምትታዘቡት እገምታለሁ፣ በተለይ ባለፉት አስርና አስራ አምስት አመታት የኢህአዴግ መንግስት ስለ “አንድነት፣ የሀገር ፍቅር ወይም ኢትዮጲያዊነት” ምንም ቢናገር፥ ቢያደርግ በብዙሃኑ ዘንድ ተዓማኒነት የለውም። የኢህአዴግ መንግስት ስለ ብሔሮች መብትና እኩልነት እንጂ ስለ ሀገራዊ አንድነት፣ ፍቅርና ዜግነት ቢናገር፥ ቢከራከር ተቃዋሚዎች ቀርቶ የራሱ ደጋፊዎች እንኳን በሙሉ ልብ አምነው አይቀበሉትም። ምክንያቱም፣ የኢህአዴግ መንግስት የፖለቲካ መርህና አመለካከት ሙሉ በሙሉ በትላንትና ዛሬ እሳቤ ላይ የተመሰረተ ነው። ከሕገ-መንግስቱ ጀምሮ የሀገሪቱ ፖለቲካዊ መርሆችና ፖሊሲዎች በሙሉ ከቀድሞ ስርዓት ላይ ተነስተው የአሁኑ ስርዓት ላይ የሚቆሙ ናቸው። ከወደፊቱ ሕይወት ጋር ትስስር የላቸውም። ሃሳቡን ግልፅ ለማድረግ ከሀገር አመሰራረትና አንድነት አንፃር መመልከት ይኖርብናል። 

በቀጣይ ሳምንት ከሚከበሩት አንዱ “የአንድነት ቀን” ሲሆን “ኢትዮጵያዊ ኩራቱ ህብረ-ብሄራዊነቱ” የሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ከላይ ተገልጿል። ነገር ግን፣ የኢህአዴግ መንግስት ሀገራዊ አንድነትን “ከህብረ-ብሔራዊነት ወይም ብዙሃንነት” አንፃር የሚገልፅበት ምክንያት ምንድነው? “ኢትዮጵያዊ ኩራቱ ህብረ-ብሄራዊነቱ” የሚለው መሪ ቃልስ ከአንድነት ፅንሰ-ሃሳብ ጋር አብሮ ይሄዳል? በእርግጥ የኢህአዴግ መንግስት ሀገራዊ አንድነትን ከህብረ-ብሔራዊነት ጋር አንፃር የሚገልፅበት ዋና ምክንያት ራሱን ከቀድሞ አህዳዊ ስርዓቶች ለመለየት ነው። 

የኢህአዴግ መንግስት በተለይ በአፄ ሚኒሊክ ዘመን የተመሰረተችው የአሁኗ ኢትዮጲያ በአንድ ዓይነት ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ባህል፥ ሃይማኖት፥… እንደሆነ ይገልፃል። በዚህ መሰረት፣ በቀድሞ ስርዓት “አንድነት” ማለት አማርኛ ቋንቋ፣ የአማራ ባህልና ሃይማኖት፣ እንዲሁም የአማራ የበላይነት የተረጋገጠበት አስተዳደራዊ ስርዓት እንደነበር ይገልፃል። በሕወሃት መሪነት የተጀመረው የትጥቅ ትግልም ይህን አህዳዊ ስርዓት በማስወገድ የብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች መብትና እኩልነት የተረጋገጠበት ፖለቲካዊ ስርዓት ለመዘርጋት ዓላማ ያደረገ ነበር። የደርግን ስርዓት በማስወገድ የተዘረጋው በብሔር ላይ የተመሰረተ ፌዴራላዊ ስርዓት የዚህ ውጤት ነው። በመሆኑም፣ የኢህአዴግ መንግስት ሀገራዊ አንድነትን ከሕብረ-ብሔራዊነት ነጥሎ ማየት አይችልም። ሕብረ-ብሔራዊነትን ከቀድሞ ታሪክ፣ ከአሁኑና ከወደፊቱ ፖለቲካ አንፃር እንመልከት።  

የኢትዮጲያ አመሰራረትና አንድነት

የኢህአዴግ መንግስት በተደጋጋሚ ኢትዮጲያ እንደ ሀገር መቀጠል የቻለችው በሕብረ-ብሔራዊነቷ፥ በብሔር ልዩነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ስርዓት መዘርጋት በመቻሏ እንደሆነ ይገልፃል። እንደ ኢህአዴግ መንግስት አገላለፅ፣ በቀድሞ ስርዓት የነበረው የኢትዮጲያ አንድነት በአንድ ዓይነት ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ባህል፥ ሃይማኖት፣ እንዲሁም በአንድ ብሔር የበላይነት ላይ የተመሰረተ ከነበረ፣ ሀገሪቱ የኢህአዴግ መንግስት ወደ ስልጣን እስከመጣበት 1983 ዓ.ም እንደ ሀገር መቀጠል አትችልም ነበር። አፄ ሚኒሊክ የአሁኗን ኢትዮጲያ ከመመስረታቸው በፊት ሆነ በኋላ በአንድ አይነት ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ባህልና ሃይማኖት ሀገር ለመመስረት የተደረገው ሙከራ በተደጋጋሚ ውድቅ ሆኗል። በአጠቃላይ፣ በፍፁም አህዳዊ እሳቤ ሀገራዊ አንድነትን ማረጋገጥ አይቻልም። 

Jose Ortega y Gassett” የተባለው ፀኃፊ “THE REVOLT OF THE MASSES” በሚለው መፅሃፉ ስፔን በመካከለኛውና ደቡብ አሜሪካ ያጋጠማትን እንደ ማሳያ ይጠቅሳል። ከዚህ በተጨማሪ፣ እንደ እንግሊዝና ፈረንሳይ ያሉ ሀገራት በቅኝ-ግዛቶቻቸው በአንድ ዓይነት ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ባህልና ሃይማኖት ላይ የተመሰረተ አንድነት ለመፍጠር የሚያደርጉት ሙከራ እንደማይሳካ መፅሃፉ በወጣበት እ.አ.አ. 1929 ዓ.ም ላይ ሆኖ በግልፅ ጠቁሟል። በተለይ ስፔን በመካከለኛውና ደቡብ አሜሪካ በነበሯት ቅኝ-ግዛቶች የጋራ ታሪክ፥ የጋራ ቋንቋና ዘር እንደነበራት ይገልፃል። ሆኖም ግን ሀገራዊ አንድነት ሊኖራት እንዳልቻለ እንዲህ ሲል ገልፆታል፡- 

“With the peoples of Central and South America, Spain has a past in common, common language, common race; and yet it does not form with them one nation. Why not? There is one thing lacking which, we know, is the essential: a common future.”  The Revolt of the Masses, Ch. XIV: Who Rules the World?, Page 105.  

ከላይ በተገለፀው መሰረት፣ ስፔን በደቡብና መካከለኛው አሜሪካ በአንድ አይነት ታሪክ፥ ቋንቋና ዘር ላይ የተመሰረተ ሀገራዊ አንድነት ለመፍጠር ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም። እንደ ፈረንሳይ ያሉ ቅኝ-ገዢ ሀገራት የራሳቸውን ቋንቋ፥ ባህል፥ ስነ-ልቦና፥ የትምህርት ስርዓት እና ሌሎች ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ስርዓቶችን በአፍሪካና ኢሲያ ሀገራት ላይ በመጫን አህዳዊ አንድነት እንዲኖር ያልተሳካ ሙከራ አድርገዋል። አንዳንድ አክራሪ ብሔርተኞች የአፄ ሚኒሊክን መስፋፋት ከቅኝ-ግዛት ጋር ያያይዙታል። ሕወሃት/ኢህአዴግ ደግሞ የኢምፔሪያሊዝም መስፋፋት እንደሆነ ይገልፃል። ሁለቱም ወገኖች ግን ከአፄ ሚኒሊክ ጀምሮ እስከ ኢህአዴግ መንግስት ድረስ በአንድ ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ባህልና ሃይማኖት ላይ የተመሰረተ አንድነት እንደነበረ ይገልፃሉ። የስፔንና ፈረንሳይ ተሞክሮ የሚያሳየው ግን በዚህ ላይ የተመሰረተ አንድነት ቀጣይነት እንደሌለው ነው። 

የአሁኗ ኢትዮጲያ ግን መመስረት ከተመሰረተችበት ግዜ አንስቶ የኢህአዴግ መንግስት እስከ መጣበት ድረስ አንድ መቶ አመት ያህል አንድነቷን አስጠብቃ ቆይታለች። ከዚህ በተጨማሪ፣ ገና በምስረታ ሂደት ላይ እያለች የኢጣሊያን የተቃጣባትን የቅኝ-ግዛት ወረራ መመከት ችላለች። በወቅቱ የኢትዮጲያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች የወደፊት አብሮነት “common future” ካልነበራቸው የኢጣሊያን ወራሪ ጦር በጋራ ተረባርበው አይመክቱም ነበር። እንደ ሀገር አብሮ ለመቀጠል፥ የጋራ ዓላማና ግብ ከሌላቸው የተለያዩ ብሔር ተወላጆች አደዋ ላይ ከኢጣሊያን ጋር የሚዋጉበት ምክንያት የለም።

የኢትዮጲያ ብሔሮች አድዋ ላይ የተዋደቁት የጋራ ዓላማ፣ የወደፊት አብሮነት ስላላቸው እንጂ በቋንቋ፣ ታሪክ፣ ባህል ወይም ሃይማኖት አንድ አልነበረሩም። በተቃራኒው፣ ኢጣሊያ ኢትዮጲያን የወረረችበት ዓላማ በአንድ አይነት ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ሃይማኖት እና ግዛት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ስርዓት ለመዘርጋት ነበር። ይህን “Raymond Jonas” የተባለው የታሪክ ምሁር እንደሚከተለው ገልፆታል፡- 

“If any quality typifies Italian colonial efforts it would not be jingoism but apathy. The Italian statesman Marquis d’Azeglio, after Italian unification, commented that “We have made Italy. Now we must make Italians.” Italy was divided along religious, political, and regional lines. It was hoped by some, such as Prime Minister Crispi, that imperialism would improve the standing of the Italian government within the nation and across Europe.” When Ethiopia Stunned the World: Cambridge, Massachusetts: Belknap Press, 2011 

ኢትዮጲያ ከአደዋ ጦርነት በኋላም አንድነቷን የሚፈታተኑ ታሪካዊ ክስተቶች አጋጥመዋታል። ከእነዚህ ውስጥ የአምስት አመቱ የፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ እና የደርግ ወታደራዊ ፋሽስት አስተዳደር በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው። በአጠቃላይ፣ ከኢህአዴግ መንግስት መምጣት በፊት አንድነቷን ሊያፈርሱ የሚችሉ ብዙ አስቸጋሪ ወቅቶችን አልፋለች። አፄ ሚኒሊክ የአሁኗን ኢትዮጲያ ለመመስረት ወደ ደቡብ፥ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫዎች ካደረጉት መስፋፋት ጋር ተያይዞ ብዙ ችግሮች ሊነሱ ይችላል። ሆኖም ግን፣ እንደ ስፔን፥ ፈረንሳይና ኢጣሊያ ካሉ የቅኝ-ግዛት ኃይሎች በተለየ፣ የአፄ ሚኒሊክ መስፋፋትና የዘረጉት የፖለቲካ አስተዳደራዊ ስርዓት ሕብረ-ብሔራዊ ነበረ። 

ኢትዮጲያ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ አንድነቷን አስጠብቃ መቀጠል የቻለችበት ዋና ምክንያት ይሄ ነው። የአፄ ሚኒሊክ መስፋፋት ዋና ዓላማ እንደ አውሮፓዊያኑ የነባር ጎሳዎችን፥ ብሔሮችን ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ባህልና ሃይማኖት በአህዳዊ አንድነት ለማጥፋት ሳይሆን ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ለመመስረት እንደነበረ በወቅቱ ዓይን እማኝ የነበረው ሩሲያዊው ፀኃፊ “Alexander Bulatovich” እንደሚከተለው ገልፆታል፡-     

“These are the motives which led Menelik to aggressive acts; and we Russians cannot help sympathizing with his intentions, not only because of political considerations, but also for purely human reasons. It is well known to what consequences conquests of wild tribes by Europeans lead. Too great a difference in the degree of culture between the conquered people and their conquerors has always led to the enslavement, corruption, and degeneration of the weaker race. The natives of America degenerated and have almost ceased to exist. The natives of India were corrupted and deprived of individuality. The black tribes of Africa became the slaves of the whites.” With the Armies of Menelik II, trans. Richard Seltzer, Journal of an expedition from Ethiopia to Lake Rudolf, an eye-witness account of the end of an era. 

ከላይ እንደተመለከትነው፣ ኢትዮጲያ ከአመሰራረቷ ጀምሮ ሕብረ-ብሔራዊ እንደነበረች ተመልክተናል። ለዚህ ደግሞ ሀገሪቷ አንድነቷን ጠብቃ ለአንድ ክፍለ ዘመን መቀጠል መቻሏ፣ አህዳዊ ስርዓት ለመዘርጋት በሚሞክሩ ቅኝ-ገዢዎች የተቃጣባትን ወረራ በጋራ መመከቷ መቻሏ፣ እንዲሁም እንደ “Alexander Bulatovich” አገላለፅ፣ የኢትዮጲያ ነባር ጎሳዎች፥ ብሔሮች ወይም ሕዝቦች ልክ እንደ አሜሪካ ነባር ሕዝቦች (ቀይ ሕንዶች) የመኖር ሕልውናቸውን አለማጣታቸው፣ ቋንቋ፥ ባህልና እምነታቸውን እስካሁን ይዘው መቀጠላቸው በማሳያነት መጥቀስ ይቻላል። 

የኢትዮጲያ አንድነት እና የኢህአዴግ አመለካከት

የኢህአዴግ መንግስት የዘረጋው ፖለቲካዊ ስርዓት “የቀድሞ ስርዓት አህዳዊ ነበር” በሚል አመለካከት ላይ የተመሰረተ ነው። በዚህ መሰረት፣ የሀገሪቱ አንድነት በአንድ ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ባህልና ሃይማኖት ላይ የተመሰረተ፣ ወይም የአማራ የበላይነት የተረጋገጠበት ነበረ። የኢትዮጱያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች መብትና እኩልነት ስላልተረጋገጠ ሕብረ-ብሔራዊነት አልነበረም። የኢትዮጲያ አንድነት እና ሕብረ-ብሔራዊነት የተረጋገጠው በኢህአዴግ መንግስት አማካኝነት ነው። ስለዚህ፣ የአንድነት ቀን “ኢትዮጲያዊ ኩራቱ ህብረ-ብሔራዊነቱ” በሚል መሪ ቃል የሚከበርበት ዋና ምክንያት፤ ከአፄ ሚኒሊክ ዘመን ጀምሮ የነበረው ፖለቲካዊ ስርዓት አህዳዊ እንደነበርና ይህም ስርዓት በ1987 ዓ.ም በፀደቀው ሕገ-መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ እንደተወገደ ለማሳየት ነው። 

በቀድሞ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ መሪነት የተዘረጋው መንግስታዊ ስርዓት ከአፄ ሚኒሊክ ዘመን ጀምሮ የነበረውን በመሻር ሀገሪቷን በአዲስ መሰረት ላይ እንዳቆማት ሲገልፅ ይስማል። በዚህ መሰረት፣ አንደኛ፡- ትላንት ላይ ሕብረ-ብሄራዊ ስርዓት ስላልነበረ ሀገራዊ አንድነት አልነበረም፣ ሁለተኛ፡- ዛሬ ላይ ሕብረ-ብሄራዊ ስርዓት ስለተዘረጋ ሀገራዊ አንድነት አለ። ነገር ግን፣ ዛሬ ኢትዮጲያ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት እንዲኖራት ትላንት ላይ ሕዝቦቿ የጋራ ታሪክና የወደፊት አብሮነት ሊኖራቸው ይገባል። ትላንት ላይ ሕብረ-ብሔራዊነት ካልነበረን የወደፊት አብሮነት አይኖረንም፤ የወደፊት አብሮነት ካልነበረን ዛሬ ላይ አንድነት ሊኖረን አይችልም። ሃሳቡን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ሃሳቡን በዝርዝር መመልከት ያስፈልጋል። 

በመጀመሪያ ደረጃ ከአፄ ሚኒሊክ ዘመን ጀምሮ ሕብረ-ብሔራዊነት ካልነበረ ሀገሪቱ ለአንድ ክፍለ ዘመን ያህል አንድነቷን ጠብቃ መቀጠል አትችልም ነበር። ምክንያቱም፣ አፄ ሚኒሊክ ወደ ደቡብ፥ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫዎች በመዝመት ከፊሉን በአስከፊ ጦርነት የተቀሩትን በሰላማዊ ድርድር የኢትዮጲያ አካል ያደረጓቸው የተለያዩ ጎሳዎች፥ ብሔሮችና ሕዝቦች ከተወሰነ ግዜ በኋላ ራሳቸውን ከአገዛዙ ነፃ ለማውጣት ትግል ይጀምራሉ። በተመሳሳይ ወቅት በአውሮፓ ቅኝ-ገዢዎች ስር የወደቁ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሕዝቦች ከግማሽ ክ/ዘመን በኋላ ራሳቸውን ከአገዛዙ ነፃ ማውጣት ችለዋል። የኢትዮጲያ ብሄሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች ግን የኢትዮጲያ አካል ከሆኑ አስር አመት ሳሞላቸው የኢጣሊያን የቅኝ-ግዛት ወረራ ለመመከት በጋራ ወደ አድዋ ዘምተዋል። 

ኢትዮጲያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ልዩ የሚያደርጋት በአደዋ ጦርነት በነጮች ላይ የተቀዳጀችው ድል አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ ከሌሎች አፍሪካዊያን በተለየ በኢትዮጲያ ስር የነበሩት ነባር ግዛቶች፡- ሸዋ፥ ጎንደር፥ ትግራይ፥ ጎጃምና ወሎ በደቡብ፥ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ከነበሩት ሌሎች ብሄሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች በመቀናጀት የቅኝ-ገዢዎችን በጋራ ለመመከት መስማማታቸው ነው። ስለዚህ፣ ኢትዮጲያዊያን በኩራት የሚጠቅሱት የአደዋ ድል የመጨረሻ ውጤት እንጂ መነሻ ምክንያት አይደለም። ከአደዋ ድል እና ከኢትዮጲያ ነፃነት በስተጀርባ ያለው ሚስጥር የኢትዮጲያ ብሄሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች በጋራ በመሆን ራሳቸውን ከቅኝ-ግዛት ወረራ ለመከላከል የፈጠሩት የወደፊት አብሮነት (common future) ነው። ሌሎች አፍሪካዊያን ይህን የወደፊት አብሮነት መፍጠር ስለተሳናቸው ለቅኝ-ግዛት ተዳርገዋል። ኢትዮጲያዊያን ግን ራሳቸውን ከቅኝ-ገዢዎች ወረራ መከላከልን ዓላማ አድርገው የፈጠሩት አብሮነት ለአንድነታቸው መሰረት ሆኗል። 

በሌላ በኩል፣ የአፄ ሚኒሊክ አገዛዝ ልክ እንደ ቅኝ-ገዢ ኃይሎች አህዳዊ ፖለቲካዊ ስርዓት የመዘርጋት ዓላማ ከነበረው በተለያዩ ብሄሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች ላይ አንድ ዓይነት ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ባህልና ሃይማኖት ይጭኑ ነበር። ይህ ከሆነ ደግሞ በደቡብና መካከለኛው አሜሪካ እንደነበረው የስፔን አገዛዝ፣ እንዲሁም በአፍሪካ ኢሲያ እንደ ነበረው የፈረንሳይ አገዛዝ ለውድቀት ይዳረግ ነበር። አሊያም ደግሞ የሀገሪቱን ብሔሮች፥ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አንድ ላይ በማቀናጀት የኢጣሊያን ወረራ መመከት ይሳነው ነበር። በመሆኑም፣ በአፄ ሚኒሊክ ዘመን የተዘረጋው አገዛዝ ሕብረ-ብሔራዊነት ካልነበረው፣ እንደ ኢህአዴግ መንግስት አገላለፅ ወይም እንደ ቀኝ-ገዢ ኃይሎች ፍፁም አህዳዊ ስርዓት ከነበረ ከግማሽ ከፍለ ዘመን በፊት በወደቀ፣ ሀገሪቷም አንድነቷን አስጠብቃ ማስቀጠል በተሳናት ነበር። ስለዚህ፣ ኢትዮጲያ እንደ ሀገር መቀጠል የቻለችው በሕብረ-ብሔራዊነት ላይ የተመሰረተ አንድነት ስለነበራት ነው። 

የፈረሰ አንድነት

የኢህአዴግ መንግስት “ዛሬ ላይ በሀገራችን የብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች መብትና እኩልነት ተረጋግጧል” የሚለውን እውነት ነው ብለን እንቀበል። በሕገ-መንግስቱ መሰረት፣ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን እና ራስን በራስ የማስተዳደር መብታቸው ተከብሯል። የኢትዮጲያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች በራሳቸው ቋንቋ የመናገር፥ የመማርና የመፃፍ መብት፣ ባህላቸውን መግለጽና ማሳደግ ችለዋል። በመሆኑም፣ ሀገራችን ብዙሃንነት የሚንጸባረቅባት ሕብረ-ብሔራዊ ሆናለች። ይሄ ዛሬ ላይ ያለው፥ የሆነውና እየሆነ ያለ ነገር ነው። ነገ ግን ሌላ ቀን ነው። ዛሬ ላይ ያለው፣ የሆነው ወይም እየሆነ ባለው ነገር ብቻ መኖር አይቻልም። 

ትላንት ላይ ሆነን የዛሬውን ህብረ-ብሔራዊነት ስንመኝ፥ ስናስብና ስናቅድ ስለነበር በተግባር እውን ማድረግ ችለናል። ነገር ግን፣ በትላንት ሃሳብ፥ ዕቅድና ምኞት ዛሬን መኖር አንችልም። ምክንያቱም፣ የሰው ልጅ ትላንትን የሚያስታውሰው ሆነ የዛሬ ተግባሩን የሚፈፅመው ነገ ላይ የተሻለ ነገር ለማግኘት ነው። የቀድሞውን የኢትዮጲያን የቀድሞ ታሪክ የምናስታውሰው፣ የዛሬውን ህብረ-ብሔራዊነት የምናወድሰው፣ ነገ ላይ የተሻለ ፖለቲካዊ ስርዓት ለመዘርጋት እንዲያስችለን ነው። ይሁን እንጂ፣ የኢህአዴግ መንግስት ከቀድሞ ስርዓት ስህተት እና ከአሁኑ ስርዓት ፍፁማዊነት ትርክት ባለፈ ለነገ ምን ሰንቋል? 

የኢህአዴግ መንግስት የዘረጋው ፖለቲካዊ ስርዓት፤ የኢትዮጲያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች ትላንት ላይ የጋራ ታሪክና አብሮነት ወይም አንድነት አልነበራቸውም፣ ዛሬ ላይ ግን ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት አላቸው፣ ነገ ላይ ደግሞ በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 39(1) መሰረት በማንኛውም መልኩ የማይገደብ የራስ እድልን በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል መብት አላቸው። ስለዚህ፣ ትላንት ላይ የጋራ አብሮነት አልነበረንም፣ ዛሬ ላይ በልዩነት አብረን አለን፣ ነገ ላይ መለያየት እንችላለን። በዚህ መሰረት፣ የኢህአዴግ መንግስት አቋምና አመለካከት ስህተት ነው። 

አንደኛ፡- ዛሬ ላይ አብረን እንድንሆን ትላንት ላይ አብረን መሆን ነበረብን። ምክንያቱም፣ ትላንት ላይ አብረው ያልነበሩ ወገኖች ዛሬ ላይ ስለ ወደፊት አብሮነት ሆነ መለያየት ለመነጋገር መሰረት የላቸውም። ዛሬ ላይ አብረን እንድንሆን ትላንት ላይ በወደፊት አብሮነት (common future) የተመሰረተ አንድነት ሊኖረን ይገባል። ትላንት ላይ የወደፊት አብሮነት ከነበረን ደግሞ የጋራ አንድነት እንደነበረን መገመት ይቻላል። ስለዚህ፣ የኢህአዴግ መንግስት በህብረ-ብሄራዊነት ላይ የተመሰረተ አንድነት በ1987 ዓ.ም እንደሆነ የሚገልፀው ፍፁም ስህተት ነው። 

ሁለተኛ፡- ዛሬ ላይ አንድነት እንዲኖረን የወደፊት አብሮነት ሊኖረን ይገባል። የወደፊት አብሮነት እንዲኖረን ስለ ወደፊቱ ግዜ በጋራ ማሰብ፥ መመኘት፥ ማቀድ፥ መነጋገርና መግባባት አለብን። ይህን ለማድረግ ደግሞ ለወደፊት በአብሮነት ለመኖር መወሰን አለብን። ነገር ግን፣ የትኛውም ብሔር፥ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ መቼና ለምን እንደሆነ ባልታወቀ ምክንያት ከሌሎች የኢትዮጲያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች ጋር አብሮ መቀጠል ባለመፈለጉ ምክንያት ሊገነጠል ይችላል። 

በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 39(1) ላይ በተደነገገው መሰረት፣ ማንኛውም የኢትዮጲያ ብሔር፥ ብሔረሰብ፥ ሕዝብ በማንኛውም መልኩ ያልተገደበ የመገንጠል መብት አለው። በድንጋጌው መስረት፣ “የራስን እድል በራስ የመወሰን እስከመገንጠል መብቱ በማንኛውም መልኩ ያለ ገደብ የተጠበቀ ነው” እንደማለቱ፣ ሌሎች ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች ወይም ሕዝቦች፣ ወይም አግባብነት ያለው ማንኛውም አካል አንድን ብሔር እንዳይገነጠል ወይም ከሌሎች ጋር በአብሮነት እንዲቀጥል ሊያደርጉት አይችሉም። በአጠቃላይ፣ ትላንት ላይ አንድነት አልነበረንም፣ ዛሬ ላይ በልዩነት አለን፣ ነገ ላይ ግን ለመለያየት አቅደናል። ለመለያየት እቅዱ ባይኖር እንኳን መንገዱን አዘጋጅተናል። ስለዚህ፣ ዛሬ ላይ አብረን እያለን ነገ ላይ ተለያይተናል።

የኢህአዴግ መንግስት ስለ ቀድሞ ስርዓት የተሳሳ ተግንዛቤ አለው። ፖለቲካዊ ስርዓቱም በተሳሳተ መርህ ላይ የተመሰረተ ነው። ከምንም በላይ ደግሞ ፖለቲካዊ ስርዓቱ በትላንት እና ዛሬ ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው።  ይህ ማለት ስለ ትላንቱ የጋራ ታሪክ ወይም ዛሬ ላይ ስላለን የጋራ ጉዳይ አይደለም። “አንድነት” ማለት ነገ ላይ ያለን የጋራ ተስፋና አብሮነት ነው። በትላንቱ ወይም በዛሬ እሳቤ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ስርዓት የሀገር አንድነትን፥ ፍቅርንና የዜግነት ክብርን ያጠፋል፡-  

“If the nation consisted only in past and present, no one would be concerned with defending it against an attack. Those who maintain the contrary are either hypocrites or lunatics. But what happens is that the national past projects its attractions- real or imaginary into the future. A future in which our nation continues to exist seems desirable. That is why we mobilise in its defence, not on account of blood or language or common past. In defending the nation we are defending our to-morrows, not our yesterdays.” The Revolt of the Masses, Ch. XIV: Who Rules the World?, Page 103. 

የሀገር አንድነት የወደፊት አብሮነት ነው። ወደፊት ለመለያየት እቅድ ያለን ወይም መንገዱን ያዘጋጀን ሕዝቦች የወደፊት አብሮነት የለንም። የወደፊት አብሮነት ከሌለን ሀገራዊ አንድነት የለንም ወይም ሊኖረን አይችልም። በአጠቃላይ፣ የአሁኗ ኢትዮጲያ አንድነት የላትም። አሁን ያለው ፖለቲካዊ ስርዓት እስካለ ድረስ አንድነት ሊኖራት አይችልም። በዚህ ሁኔታ፣ ዜጎች የሀገር ፍቅር ሆነ የዜግነት ክብርና ኩራት ሊኖራቸው አይችልም። የላቸውም! ምክንያቱም፣ ሀገር የሚመሰረተው፣ አንድነት የሚረጋገጠው፣ እንዲሁም ዜጎች ሀገራዊ ፍቅርና ክብር የሚኖራቸው በሌላ ሳይሆን የወደፊት አብሮነት ሲኖራቸው ነው። ለወደፊት ለመለያየት እቅድ ያለን ሕዝቦች የወደፊት አብሮነት የለንም!!! 

በመጨረሻም፣ “ኢትዮጲያዊነት” ማለት በወደፊት አብሮነት ላይ የተመሰረተ አንድነት፣ የሀገር ፍቅር እና የዜግነት ክብር ነው። የኢህአዴግ መንግስት የሀገር አንድነት፣ ፍቅርና የዜግነት ክብር ከአብዛኛው ኢትዮጲያዊ አመለካከት ውስጥ ተፍቆ እንዲወጣ በማድረግ ይህን የአብሮነት መንፈስ ለማጥፋት ተቃርቧል። ጎጠኝነትና ጠባብ ብሔርተንነት ገኖ እንዲወጣ በማድረግ ኢትዮጲያዊነትን ትርጉም አሳጥቶታል። በአንፃሩ፣ የውስን አመለካከት ነፀብራቅ የሆነው ብሔርተኝነትና ጎጠኝነት በብዙሃኑ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። በመሆኑም፣ በግብዝ ዕውቀትና ግንዛቤ ላይ ተመስርቶ ሀገር ማፍረሱን ቀጥሎበታል። 

የብሔር ፖለቲካ፣ የኢትዮጲያ ታሪክ እና የመሪዎቿ ተጠያቂነት

“በአንድ ሀገራዊ ጀግና ላይ እንኳን መግባባት ያቅተን?!” ይህ ባለፈው ሳምንት በአንዱ የፌስቡክ ገፅ ላይ ያነበብኩት ነው። በእርግጥ ፅሁፏ አንድ ዓ.ነገር ናት። በጥያቄው ውስጥ የታጨቀው ሃሳብ ግን የአንድ ክፍለ ዘመን ታሪክ ያህል ረጅምና ውስብስብ ነው። ጉዳዩ ከጄ/ል ጃጋማ ኬሎ ሞት ጋር ተያይዞ እንደተነሳ መገመት ይቻላል። በተለይ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በአንዱ ወገን በጄ/ል ጃጋማ ሞት የተሰማን ሀዘን መግለፅ የጄ/ል ታደሰ ብሩን መቃብር እንደመቆፈር ተቆጠረ። በሌላ ወገን ያሉት ደግሞ የጃጋማን ጀግንነት ለማድነቅ የጄ/ል ታደሰ ብሩን እና የዋቆ ጉቶን ታሪክ ማጣጣል ጀመሩ። ይህን ተከትሎ እንደተለመደው ሰሞኑን “የባንዳ እና ሽፍታ” ፖለቲካ ተጧጧፈ።

እንኳን በቀድሞ የጦር መሪ በሀገራችን መሪዎች ላይ እንኳን በጋራ መግባባት አልቻልንም እኮ! ለምሳሌ፣ አፄ ዩሃንስ፣ አፄ ሚኒሊክ እና ጄ/ል ጃጋማ ኬሎ፣ በቅደምተከተላቸው መሰረት የሀገር ሉዓላዊነትን፣ አንድነትን እና ሥርዓትን ከማስከበር አንፃር የነበራቸው የመሪነት ሚና በአረዓያነት የሚጠቀስ ነው። ነገር ግን፣ በሀገር ሉዓላዊነትና፣ አንድነት እና ሥርዓት ሰበብ በንፁሃን ዜጎች ላይ አሰቃቂ በደል፣ ጭቆና እና ክህደት ተፈፅሟል። በዚህ ፅሁፍ እነዚህን መሪዎች በምሳሌነት በመውሰድ ከሀገሪቱ ታሪክ፣ ከነበራቸው ሚና እና አሁን ካለው ፖለቲካዊ አለመግባባት ጋር አያይዘን በዝርዝር እንመለከታለን።

በመጀመሪያ ደረጃ ከሦስቱ መሪዎች ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ የሚነሱ ሁለት ተፃራሪ ሃሳቦችን ለማሳያ ያህል ወስደን እንመልከት፡-
1ኛ) አፄ ዩሃንስ “የግብፅ ተደጋጋሚ ወረራ በመመከት የኢትዮጲያን ሉዓላዊነት አስከብረዋል” – “የወሎ ሙስሊሞችን እጅ ቆርጠዋል”፣2ኛ) አፄ ሚኒሊክ “የኢትዮጲያን አንድነት በማረጋገጥ ሀገሪቱን ከቅኝ-ገዢ ኃይሎች ተከላክለዋል” – “በአኖሌ የእናቶችን ጡት ቆርጠዋል”፣3ኛ) ጄ/ል ጃጋማ ኬሎ “ፋሽት ኢጣሊያን የተጋሉ ብሔራዊ ጀግና ናቸው” – “ጄ/ል ታደሰ ብሩን አሳልፈው የሰጡ ከሃዲ ናቸው”

​ከላይ በተጠቀሰው መሰረት፣ የሦስቱ መሪዎች ስም በተነሳ ቁጥር አንዱ ወገን “ጥሩ” ሥራቸውን በማጉላት “መጥፎ” ሥራቸውን ያጣጥላል። ሌላኛው ወገን ደግሞ “መጥፎ” ሥራቸውን በማጉላት “ጥሩ” ሥራቸውን ያጣጥላል። በአጠቃላይ፣ የቀድሞ መሪዎች ስም ሲነሳ ያለቅጥ የተጋነነ ሙገሳና አድናቆት ወይም ቂምና ጥላቻ የታጨቁ ቃላት እርስ-በእርስ እየተወራወሩ መለጣጠፍ የተለመደ ተግባር ሆኗል።

በእርግጥ በቀድሞ መሪዎች ሚና እና በታሪካዊ ክስተቶች ዙሪያ የተለያየ አቋምና አመለካከት መኖሩ በራሱ እንደ ችግር ሊወሰድ አይገባም። ሁሉም ታሪካዊ ክስተቶች “ጥሩ እና መጥፎ”፣ የሀገሪቱ መሪዎችም “ባንዳ እና ሽፍታ” ተብለው በጅምላ የሚፈረጁ ከሆነ ግን በጣም አሳሳቢ ነው። በመሰረቱ፣ የሰው ልጅ ሕይወትንና የሀገር ታሪክን እንዲህ በጅምላ መፈረጅ የመንጋ አስተሳሰብ ነው።

የብሔር ፖለቲካና የኢትዮጲያ ታሪክ

“Jose Ortega y Gassett” የተባለው ታዋቂ ምሁር “The Revolt of the Masses” በተሰኘው መፅሃፉ ይህ አስተሳሰብ በዋናነት ፖለቲካዊ አብዮትን ተከትሎ የሚከሰት ማህበራዊ ቀውስ እንደሆነ ይገልፃል። አብዮቱን ተከትሎ ወደ ስልጣን የመጣው የፖለቲካ ኃይል የራሱን ቅቡልነት ለማረጋገጥ የቀድሞው ሥርዓት በሀገሪቱ ታሪክና በሕዝቡ ሕይወት ውስጥ ያለውን ሚናና አስተዋፅዖ ያለ ማቋረጥ በመጣጣሉ፣ እንዲሁም በዕውቀት ላይ ከተመሰረተ ግንዛቤና አመለካከት ይልቅ ጭፍን ድጋፍና ተቃውሞ በማበረታታቱ ምክንያት የሚፈጠር ማህበራዊ ቀውስ ነው። ለምሳሌ፣ ምዕራባዊያን በ18ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ በምዕራብ አውሮፓ ሀገራትና በአሜሪካ የተካሄደውን የፖለቲካ አብዮት ተከትሎ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ለተመሣሣይ ችግር ተጋልጠው ነበር።

ባለፈው ሩብ ክፍለ ዘመን በኢትዮጲያ የተዘረጋው የብሄር ፖለቲካ ሀገሪቱን ለተመሣሣይ ቀውስ ዳርጓታል። በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በሕዝብ ዘንድ ያለውን ቅቡልነት ለማረጋገጥ በሚያደረገው ያላሳለሰ ጥረት የቀድሞ ሥርዓትና መሪዎች በሀገሪቱ ታሪክና በሕዝቡ ሕይወት ውስጥ የነበራቸውን ሚና እና አስተዋፅዖ አሳጥቷቸዋል። በዚህ ምክንያት፣ በአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ዘንድ በሀገሪቱ ታሪክና የቀድሞ መሪዎች ዙሪያ የጋራ መግባባት እንዳይኖር አድርጓል። የብሔር ፖለቲካን ያለ ቅጥ በማጦዝ የብሔር ፅንፈኝነትን እያስፋፋ እና ለሉዓላዊነትና ነፃነት የታገሉ ብሔራዊ ጀግኖችን እየገፋ በመሄዱ ሀገራዊ መግባባትና የአንድነት ስሜት ከሕብረተሰቡ ውስጥ ተሟጥጦ በማለቅ ላይ ይገኛል።

ባለፈው ሩብ ክፍለ ዘመን በኢትዮጲያ የተዘረጋው የብሄር ፖለቲካ ሀገሪቱን ለተመሣሣይ ቀውስ ዳርጓታል። በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በሕዝብ ዘንድ ያለውን ቅቡልነት ለማረጋገጥ በሚያደረገው ያላሳለሰ ጥረት የቀድሞ ሥርዓትና መሪዎች በሀገሪቱ ታሪክና በሕዝቡ ሕይወት ውስጥ የነበራቸውን ሚና እና አስተዋፅዖ አሳጥቷቸዋል። በዚህ ምክንያት፣ በአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ዘንድ በሀገሪቱ ታሪክና የቀድሞ መሪዎች ዙሪያ የጋራ መግባባት እንዳይኖር አድርጓል።

የብሔር ፖለቲካን ያለ ቅጥ ሲጦዝ የብሔር ፅንፈኝነትን እያስፋፋና ብሔራዊ ጀግኖችን እያጠፋ መሄዱ እርግጥ ነው። ነገር ግን፣ አሁን ያለው የብሄር ፖለቲካ የችግሩ መሰረታዊ መንስዔ ተደርጎ መወሰድ የለበትም። ምክንያቱም፣ ሀገራዊ አለመግባባቱ በስፋት የሚስተዋለው ከወቅታዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ይልቅ በሀገሪቱ ታሪክና የቀድሞ መሪዎች ዙሪያ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ፣ የብሄር ፖለቲካ በራሱ ከሀገሪቱ ታሪክና መሪዎች ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። ስለዚህ፣ የችግሩ መሰረታዊ መንስዔ ለመረዳት ከወቅታዊ ፖለቲካ ይልቅ በቀድሞ የሀገራችን ታሪክና መሪዎች ሕይወት ዙሪያ ማተኮር ይኖርብናል። በተመሣሣይ፣ “Jose Ortega y Gassett” የችግሩ መሰረታዊ መንስዔ አብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ስለ ሀገር ታሪክና የመሪዎች ሕይወት ያለው የተዛባ ግንዛቤና አመለካከት እንደሆነ እንዲህ ሲል ይገልፀዋል፡-

“All the features of the present day, and in particular the rebellion of the masses, offer a double aspect. Any one of them not only admits of, but requires, a double interpretation, favourable and unfavourable. …On the contrary, I believe that all life, and consequently the life of history, is made up of simple moments, each of them relatively undetermined in respect of the previous one, so that in it reality hesitates, walks up and down, and is uncertain whether to decide for one or other of various possibilities. It is this metaphysical hesitancy which gives to everything living its unmistakable character of tremulous vibration.” The Revolt of the Masses, CH_IX, Page 51

ሁሉም ሰው ለራሱ ትክክል ነው
በመሰረቱ፣ አንድ ተግባር “ጥሩ” ወይም “መጥፎ” የሚሆነው በራሱ ትክክል ወይም ስህተት ስለሆነ አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ ጥሩነት ወይም መጥፎነት የሚወሰነው ከተግባሩ አግባብነት አንፃር ነው። አግባብነት ያለው ተግባር (expedient) መደረግ ባለበት ሁኔታ ውስጥ የተደረገና ተቀባይነት እና ጠቀሜታ ያለው ነው። በዚህ መሰረት፣ መደረግ ባለበት ሁኔታ ውስጥ የተደረገ ተግባር ትክክል (right) ስለሆነ ጥሩ (good) ነው። አግባብነት የሌለው (inexpedient) ደግሞ ስህተት (wrong) እንደመሆኑ መጥፎ (bad) ነው።

ስለዚህ፣ ስለ ቀድሞ መሪዎች ጥሩነት ወይም መጥፎነት መናገር ከመጀመራችን በፊት በቅድሚያ በዘመናቸው የፈፀሟቸውን ተግባራት ትክክለኝነት ወይም ስህተትነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ነገር ግን፣ አንድን ተግባር “ትክክል” ወይም “ስህተት” ለማለት ደግሞ ከተፈፀመበት ግዜ፣ ቦታና ምክንያት አንፃር አግባብነቱን ማጤን ያስፈልጋል።

አንድን ተግባር ከቦታ፥ ግዜና ምክንያት አንፃር አግባብነቱን ለማጤንና “ትክክል” ወይም “ስህተት” መሆኑን በመወሰኑ ሂደት ውስጥ ብዙ አማራጮች ይኖራሉ። ትክክለኛ እና ስህተት የሆኑ ተግባራት በግልፅ ተለይተው አልተቀመጡም። በመሆኑም፣ ሰው አንድን ተግባር የሚፈፅመው ካለበት ቦታና ግዜ አንፃር፣ እንዲሁም በራሱ ምክንያታዊ ግንዛቤ መሰረት አግባብ ስለሆነ ነው።

በዚህ መሰረት፣ እያንዳንዱ ግለሰብ በተወሰነ ግዜና ቦታ በራሱ ግንዛቤ መሰረት የሚፈፅመው ተግባር ቢያንስ ለራሱ “ትክክል” ነው። ነገር ግን፣ ከቅፅበት በኋላ ለራሱም ሆነ ከሌሎች ሰዎች እይታ አንፃር ስህተት ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ፣ ተግባሩን በሚፈፅምበት ቅፅበት ግን ከሁኔታውና ከግንዛቤው አንፃር ቢያንስ ለራሱ ትክክል ነበር። ማንኛውም ሰው አንድን ተግባር የሚፈፅመው በራሱ አመለካከት ተገቢና ትክክል ስለሆነ ነው። ሰው በቦታውና በሰዓቱ ትክክል አለመሆኑን እያወቀ ስህተት አይሰራም። ምክንያቱም፣ አውቆና ፈቅዶ ስህተት መስራት ከምክንያታዊ አስተሳሰብ ጋር አብሮ አይሄድም። በራሱ አውቆና ፈቅዶ ስህተት የሚሰራ ሰው ተግባርና እንቅስቃሴውን መቆጣጠር የማይችል ከሆነ ብቻ ነው።

በአጠቃላይ፣ የአንድን ተግባር ትክክለኝነት ወይም ስህተትነት መወሰን ከውጪ ሆኖ “ጥሩ” ወይም “መጥፎ” ብሎ እንደመፈረጅ ቀላል አይደለም። ስለ ሌላ ሰው ተግባር ያለን አመለካከት ከቦታ፥ ግዜና ምክንያት አንፃር ባለን ግንዛቤ ላይ የተመሰረተ ነው። በመሆኑም፣ ተግባሩ ስለተፈፀመበት ቦታ፥ ሰዓትና ምክንያት ያለን ግንዛቤ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የግለሰቡ ተግባር ይበልጥ “ትክክል” ይመስለናል። በተቃራኒው፣ ተግባሩ ስለተፈፀመበት ቦታ፥ ሰዓትና ምክንያት ያለን ግንዛቤ እየቀነሰ በሄደ ቁጥር የግለሰቡ ተግባር ይበልጥ “ስህተት” ይመስለናል። የአንድን ሰው ተግባር ከቦታ፥ ግዜና ምክንያት አንፃር ምሉዕ የሆነ ግንዛቤ ሊኖረን የሚቻለው የዚያን ሰው አከባቢያዊ፣ አካላዊና መንፈሳዊ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ መገንዘብ ስንችል ነው። በዚህም፣ ግለሰቡ ራሱን በአካልና በመንፈስ መሆን የሚጠይቅ ነው። ይህ ሲሆን ደግሞ ቀድሞ ግለሰቡ የፈፀመውን መልሶ ከመድገም ሌላ ምርጫ የለንም።

የቀድሞ መሪዎች ተጠያቂነት
ቀደም ሲል የሰዎችን ተግባር “ጥሩ” ወይም መጥፎ” ብሎ ለመፈረጅ በቅድሚያ ከተፈፀመበትን ቦታ፥ ግዜና ምክንያት አንፃር መታየት እንዳለበት ተገልጿል። ለምሳሌ፣ ባለፈው ሳምንት ከአህያ ቄራ መከፈት ጋር ተያይዞ በሀገራችን የአህያ ስጋን መብላት ተቀባይነት የለውም በሚል “አህያ የጅብ ናት” ሲባል ነበር። ነገር ግን፣ በአስገዳጅ ሁኔታ (necessity) ውስጥ እንኳን አህያን ጅብን መብላት በራሱ ተቀባይነት ሊኖረው እንደሚችል “ጅብ ከሚበላኝ ጅብ በልቼ ልጠመቅ” ከሚለው አባባል መገንዘብ ይቻላል። በተመሳሳይ፣ በየትኛውም ሕግ ሰውን መግደል ተቀባይነት የሌለው ተግባር ቢሆንም ሊገድል የመጣን ሰው በአልሞት-ባይ ተጋዳይነት መግደል ግን ተቀባይነት አለው።

በአስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ የሚፈፀም ተግባር አግባብነቱ የሚመዘነው በአይቀሬ ሕግ (laws of inevitability) ነው። ምክንያቱም፣ “ማንኛውም ሰው በተመሳሳይ ቦታ፥ ሰዓትና ምክንያት ውስጥ ቢሆን ያንኑ መድገሙ አይቀሬ (inevitable) ነው” ተብሎ ይታሰባል። በአስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ ያለ ሰው ያደረገውን ከማድረግ ውጪ ሌላ ምርጫና አማራጭ የለውም። ስለዚህ፣ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የፈፀመው ተግባር አግባብና “ትክክል” ነው። ሆኖም ግን፣ አስገዳጅ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ በራሱ ፍቃድ (free will) የሌሎችን ሰዎች ነፃነት የሚፃረር ተግባር መፈፀም ግን “ስህተት” ነው።

በዚህ መሰረት፣ በታሪክ የተፈፀሙ ተግባራትን “ትክክል” ወይም “ስህተት” ከማለታችን በፊት ተግባራቱ የተፈፀሙት በአስገዳጅ ሁኔታ ወይስ በመሪዎቹ ፍቃድ የሚለውን ከግዜ፣ ቦታና ምክንያት አንፃር ጠንቅቀን ማወቅ ይኖርብናል። በዚህ ፅሁፍ መግቢያ ላይ በማሳያነት የተጠቀሱት የቀድሞ መሪዎች ተግባራት ከ50 ዓመት በፊት የፈፀሙ ናቸው። ከወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ጋር ተያይዘው እየተነሱ ለአለመግባባት ምክንያት ይሁኑ እንጂ አግባብነታቸው መታየት ያለበት ከታሪክ አንፃር ነው። ስለዚህ፣ የቀድሞ መሪዎች እነዚህን ተግባራትን የፈፀሙት በአስገዳጅ ሁኔታ (necessity) ወይም በራሳቸው ፍቃድ (free will) ስለመሆኑ መወሰንና የተግባራቱን ትክክለኝነት እና ስህተትነት መለየት የሚቻለው በታሪክ ፍልስፍና መርህ መሰረት ነው። በዚህ ረገድ ፈር-ቀዳጅ የሆነው ልሂቅ ¨Leo Tolstoy” ሲሆን ፅንሰ-ሃሳቡን እንዲህ ሲል ገልፆታል፡-

“In the experimental sciences what we know we call the laws of inevitability, what is unknown to us we call vital force. Vital force is only an expression for the unknown remainder over and above what we know of the essence of life. …So also in history what is known to us we call laws of inevitability, what is unknown we call free will. Free will is for history only an expression for the unknown remainder of what we know about the laws of human life.” War And Peace, EP2|CH10, Page 1193

ከላይ እንደተገለፀው፣ የቀድሞ መሪዎች በታሪክ የፈፀሟቸው ተግባራት በሙሉ በአስገዳጅ ሁኔታ (necessity) ውስጥ የተፈፀሙ እንደመሆናቸው አግባብና ትክክል ናቸው። ከዚህ በተቃራኒ፣ እነዚህ ተግባራት በቀድሞ መሪዎች ነፃ ፍቃድ (free will) የተፈፀሙ ማሰብ፣ እንደ “Leo Tolstoy” አገላለፅ፣ ከቦታ፥ ግዜና ምክንያት አንፃር ያለን ግንዛቤ ውስን ስለመሆኑ በራሳችን ለይ ከመመስከር ሌላ ትርጉም የለውም።

በዚህ ፅሁፍ በማሳያነት የተጠቀሱት፣ አፄ ዩሃንስ፣ አፄ ሚኒሊክ እና ጄ/ል ጃጋማ ኬሎ በመሪነት ዘመናቸው የፈፀሟቸውን ተግባራት ከግዜ፥ ቦታና ምክንያት አንፃር ሲታዩ ሁሉም በአስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ የተፈፀሙ ናቸው። ለምሳሌ፣ አፄ ዩሃንስ፡- “የግብፅን ተደጋጋሚ ወረራ በመመከት የኢትዮጲያን ሉዓላዊነት ማስከበራቸው”፣ አፄ ሚኒሊክ “የኢትዮጲያን አንድነት በማረጋገጥ ሀገሪቱን ከቅኝ-ገዢ ኃይሎች መከላከላቸው”፣ እንዲሁም ጄ/ል ጃጋማ ኬሎ “የፋሽት ኢጣሊያን ጦር ለአምስት አመት በፅናት መፋለማቸው” አግባብነት ያላቸው ተግባራት ናቸው። ምክንያቱም፣ በወቅቱ የግብፅ ወረራ በኢትዮጲያ ሉዓላዊነት ላይ፣ የቅኝ-ገዢ ኃይሎች በሀገሪቷ አንድነት ላይ፣ እንዲሁም የጄ/ል ታደሰ ብሩ ሴራ በመንግስታዊ ሥርዓቱ ላይ የሕልውና አደጋ ተጋርጦ ነበር። በሕልውና ላይ የተቃጣ ጥቃት ደግሞ ፍፁም አስገዳጅ (necessity) ነው። በአይቀሬ ሕግ (laws of inevitability) መሰረት፣ የራስን ሕልውና ለመታደግ የሚፈፀም በማንኛውም ተግባር ትክክል ነው። በእንዲህ ያለ አስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ ሌሎችን ሕልውና በማሳጣት የራስን ሕልውና መታደግ ተቀባይነት አለው።

ነገር ግን፣ በሀገር ሉዓላዊነት፣ አንድነትና ሥርዓት ላይ የተጋረጠውን የሕልውና አደጋ በማስወገድ ሂደት ውስጥ በንፁሃን ዜጎች ላይ አሰቃቂ በደል፣ ጭቆና እና ክህደት ተፈፅሟል። ለምሳሌ፣ አፄ ዩሃንስ ከግብፅ ጋር አሲራችኋል በሚል ሰበብ “የወሎ ሙስሊሞችን እጅ ቆርጧል”፣ አፄ ሚኒሊክ የሀገር አንድነትን ለማረጋገጥ በሚል “በአኖሌ የእናቶችን ጡት ቆርጧል”፤ እንዲሁም ጄ/ል ጃጋማ ኬሎ “የፊውዳሉ ሥርዓትን ለመታደግ ጄ/ል ታደሰ ብሩን አሳልፎ በመስጠት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ክህደት ፈፅሟል።”

በመሰረቱ፣ በአፄ ዩሃንስ ዘመን በሀገሪቱ ሉዓላዊነት ላይ የሕልውና አደጋ የተጋረጠው በግብፅ ጦር እንጂ በወሎ ሙስሊሞች ወረራ አልነበረም። በአፄ ሚኒሊክ ዘመን በሀገሪቱ አንድነት ላይ የሕልውና አደጋ የተጋረጠው በአውሮፓ ቅኝ-ገዢዎች አንጂ በአርሲ ኦሮሞዋች አልነበረም። እንዲሁም፣ ጄ/ል ታደሰ ብሩ በዘውዳዊው ሥርዓት ላይ ያሴረው ለኦሮሞ ሕዝብ እኩልነትና ነፃነት እንጂ ለግል ጥቅሙ አልነበረም።
ስለዚህ፣ ምንም እንኳን በሀገር ሉዓላዊነት፥ አንድነትና መንግስታዊ ሥርዓት ላይ የሕልውና አደጋ ተጋርጦ የነበረ ቢሆንም በዚያ ሰበብ አሰቃቂ በደል፥ ጭቆና እና ክህደት የተፈፀመው ግን ለአደጋው መንስዔ ባልሆነ የሕብረተሰብ ክፍል ላይ ነው። ይህ ደግሞ በማንኛውም አግባብ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም። ይህን እንቆቅልሽ የሚፈታው ብቸኛ የሞራል ሕግ “Immanual Kant” እንዲህ ሲል ገልፆታል፡-

“‘Necessity has no law’. And yet there cannot be a necessity that could make what is wrong lawful.” The Science of Right, tran. W. Hastie CH1, Page 6

በሕልውና ላይ የተቃጣን ጥቃት በሞራል ሆነ በሕግ መዳኘት አይቻልም። ምክንያቱም፣ ሕልውናን ማጣት በየትኛውም ደንብ ሊጣል ከሚችለው ቅጣት ይበልጣል። በዚህ መሰረት፣ ከላይ የተጠቀሱት የቀድሞ መሪዎች ተግባራት በሀገር ሉዓላዊነት፣ አንድነትና ሥርዓት ላይ የተቃጣውን የሕልውና አደጋ ለመከላከል የፈፅሟቸውን ተግባራት “ስህተት” ማለት አይቻልም። በተመሣሣይ፣ በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈጸሙት አሰቃቂ በደሎች፥ ጭቆናዎች እና ክህደቶች “ትክክል” ሊሆኑ አይችሉም።

በአጠቃላይ፣ በቀድሞ መሪዎች የተፈፀሙ ተግባራትን “ትክክል” ወይም “ስህተት” ብሎ ለመፈረጅ የሚያስችል ምንም ዓይነት የሞራል ሕግ የለም። በዚህ ላይ የጋራ ግንዛቤ እስካልተፈጠረ ድረስ በሀገራችን ታሪክ እና በቀድሞ መሪዎቻችን ዙሪያ ሀገራዊ መግባባት ሊኖር አይችልም።

#Adigrat_for_Sale!

አፄ ሚኒሊክ ለፈረንሳይ መንግስት ጁቡቲን ለ100 ዓመት በሊዝ መሸጣቸው፣ በተለይ በትግራይ እና በኦሮሞ ተወላጆች ዘንድ፣ እንደ ከፍተኛ የሀገር ክህደትና ወንጀል ተደርጐ ሲጠቀስ መስማት የተለመደ ነው። መቼም ታሪክን አለማወቅ ለጭፍን ፍርድ ያመቻልና፣ አፄ ሚኒሊክን ብቻ ተወቃሽ ማድረግ የአላዋቂ ፍርደ-ገምድልነት ነው።

የታሪክ እውቀት አንድን ክስተት ጠቅሶ በዚያ ላይ መንጫጫት አይደለም። ከክስተቱ ጀርባ ያለውን ነባራዊ እውነታ መረዳት፣ በገሃድ የታየውን ብቻ ሣይሆን ‘ሊሆን ይችል የነበረና በተለያዩ ምክንያቶች እውን ሳይሆን የቀረን’ ጭምር መገንዘብ ይጠይቃል። የኢትዮጲያን ታሪክ ከዚህ የታሪክ እሳቤ አንፃር ካየነው፣ እርግጥ “የኢትዮጲያን መሬት ቆርሶ መሸጥ ብርቅ ነው’ዴ” ያስብላል?

ለዚህ ፅሁፍ ርዕስ መነሻ የሆነኝና ላነሳሁት ሃሳብ አይነተኛ ማሳያ የሚሆነውን፣ በትግራይ ክልል የዓዲ-ግራት አከባቢን፣ “የአጋሜ አውራጃ” በመውሰድ እ.ኤ.አ ከ1840 -1889 ዓ.ም በነበረው ግዜ ውስጥ በማንና ለማን ተሸጦ እንደነበር የታሪክ መዛግብትን እያጣቀስን ብንመለከት የታሪክ ቁስልን እንደማከክ ይሆናል። እስኪ ይህን አስቀያሚ የታሪክ ቁስላችን አከክ…አከክ እናድርግ።   

ጳውሎስ ኞኞ፣ “አጤ ቴዎድሮስ” በሚለው መፅሃፉ #እቴጌ_መነን ኢትዮጲያን እየከፋፈሉ ሊሸጡ ካስማሙ ባላባቶች አንደኛይቱ እንደነበሩ ይነግረናል። ጳውሎስ እንደፃፈው “…በአልክሳንድርያ የቤልጅግ መንግስት ቆንስል የነበረው ኤድዋርድ ብሎንዲል ከእቴጌ መነን (የራስ አሊ እናት) ጋር በመነጋገር #አጋሜንና_እንጣሉን በ15000 ማርትሬዚያ ብርና በሶስት ሺህ ጠመንጃ ለመግዛት ተስማምተው ነበረ። ለዚህም ጉዳይ ኢትዮጲያዊው አባ ገብረ ማሪያም ለኢትዮጲያ መንግስት ኃላፊ ሆነው ለሽያጩ ተግባር ዋና ደላላና ተዋዋይ ነበሩ።”

“… አባ ገብረ ማሪያም ካይሮ ውስጥ ከቤልጅጉ ቆንሲል ከብሎንዲል ጋር የተዋዋሉት ውል እንዲህ የሚል ነበር። “በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም። እኔ ገብረ ማሪያም የኢትዮጲያ እጨጌ፣ በኢትዮጲያ ገዢ በራስ አሊ ስም የሚከተለውን ተስማምቻለሁ። #ለቤልጅግ_ንጉሥ ግርማዊ ቀዳማዊ ሊዎፖልድና ለእሳቸው ወራሾች ሁሉ እንዲሆን #የአጋሜን_አውራጃ_በሙሉ ከአዲግራት እስከ ባህሩ ድረስ ሰጥተናል” የሚል ነበር።
(ጳውሎስ ኞኞ፥ 1985፥ አጤ ቴዎድሮስ፥ ገፅ 40 – 41)

ከዓዲግራት እስከ ቀይ ባህር ድረስ ያለውን የኢትዮጲያ መሬት ቆርሶ ለመሸጥ ከቤልጅግ ቆንፅላ ጋር ውል ተገብቶ የነበረ ቢሆንም የሽያጭ ስምምነቱ ውድቅ የሆነው በሌላ ምክኒያት ሣይሆን ገዢው አካል ጥናት አድርጐ ቦታው አዋጭነት እንደሌለው ስላመነ ነበር። ከላይ በተጠቀሰው መፅሃፍ እንዲህ ይላል፣ “የቤልጅግ መንግስት ጉዳዩ እንዲጠና አደረገ።…በጥናቱ መሰረት የቀይ ባህርን አከባቢ መያዝ እንደማይጠቅም ታወቀ። …ምክንያቱም ያኔ የስዊዝ ቦይ አልተቆፈረ ስለነበረ በመርከብ ወደ ቀይ ባህር ለመምጣት በደቡብ አፍሪካ ዞሮ በመሆኑ ወጪ እንደሚያስወጣና ጉዞው ረጅም በመሆኑ አያስፈልግም ተብሎ ተወሰነ (ጳውሎስ ኞኞ፥ 1985፥ አጤ ቴዎድሮስ፥ ገፅ 42)።

በመቀጠል፣ “ማን ማንን ሸጠ?” የሚለውን የጭፍን ብሔርተኞችን ጥያቄ እናንሳ። የሽያጭ ስምምነቱ “በኢትዮጲያ ገዢ በራስ አሊ ስም የሚከተለውን ተስማምቻለሁ” እንደማለቱ በሺያጭነት የሚጠቀሱት ራስ አሊ ናቸው። #ራስ_አሊ_አሉላ ማን ናቸው? የጎንደርን መሳፍንት አገዛዝ የጀመሩት ትልቁ ራስ አሊ ልጅ ራስ ጉግሣ፣ የራስ ጉግሣ ልጅ አሉላ፣ የራስ አሉላ ልጅ ራስ አሊ። እንግዲህ፣ የዘር ሀረጉ እንደሚያሳየን ራስ አሊ የራስ አሉላ እና እትጌ መነን (በትክክለኛ ስሟ “ፋጡማ“) ልጅ ነው። ራስ አሊ የአጎታቸውን የራስ ዶሪን ሞት ተከትሎ በ1822 ዓ.ም በ12 ዓመታቸው የኢትዮጲያ ገዢ የነበሩ ሲሆን የትውልድ አገራቸው #የጁ ነው። በዚህ መሰረት፣ የኢትዮጲያን መሬት ቆርሶ ለባዕዳን በገንዘብና በቁስ ከሸጡ የሀገር ገዚዎች ውስጥ ራስ  አሊ አንዱ ሲሆኑ የዘር ግንዳቸው ሙሉ-በሙሉ የየጁ #ኦሮሞ ነው። 

የሽያጩን የብሔር ማንነት ካወቅን፣ (አሁንም ከፅንፈኞች እይታ አንፃር ለማቅረብ ካልሆነ በስተቀር የሚከተለው ጥያቄ ኢ-ሰብዓዊ የሆነ ድምፀት እንዳለው አሳስባለሁ) ‘ማንን ነው የሸጠው?” ብለን ስንጠይቅ የአጋሜ አውራጃን ነዋሪ፣ የአጋመ/አጋሜ ማህብረሰብ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።

እንግዲህ የታሪክ ቁስልን የማከክ ውጤቱ ይሄ ነው! በብሔር፣ ብሔረሰቦች ላይ የተመሠረተ የአስተዳደርና ፖለቲካ መዋቅር የሚመፃደቁና መዋቅሩ በአፄ ሚኒልክ ተቀርፆ የተዋቀረና በመለስ ዜናዊ ተደርሶ የቀረበ መሆኑን መገንዘብ ተስኗቸው፣ አፄ ሚኒልክን በ”ሀገር ሺያጭነት!” ሲፈርጁ የሚውሉ አንዳንድ የትግራይ እና ኦሮሞ ተወላጆች፣ ይሄው በዚህ ታሪካዊ እውነታ ራሳቸውን ሺያጭና ተሺያጭ ሆነው ያገኙታል።

ነገር ግን፣ አንድ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ያደረሰው ታሪካዊ በደል ተደርጐ ሊወሰድ አይገባም። ለምሳሌ፣ ከላይ በተጠቀሰው መልኩ፣  “የየጁ ኦሮሞ ትግራይን ለባዕዳን ሸጠ” ለማለት እንደማይቻል የሚያሳይ ሌላ የታሪክ እከክ ልጥቀስ።

“ዓፄ ሚኒልክ እና የኢትዮጲያ አንድነት” በሚለው መፅሃፉ ተክለ-ፃዲቅ መኩሪያ በግልፅ እንዳስቀመጠው፣ የአከባቢው ገዢ  የነበሩ ሰውች ከጣሊያን ጋር በማበርና ለወራሪ ሃይል መሣራያ በመሆን ራሳቸውንና ሀገራቸውን አሳልፈው ሸጠዋል። “…የየጣሊያን ጦር አስመራ ከገባ በኋላ #የአጋሜው_ደጃች_ስብሐት እና የአካለ ጉዛዩ ደጃች ባሕታ ሐጎስ ለኢጣልያ ታመኝ ሆነው ስለገቡለት፣ በማናቸውም ረገድ የኢጣሊያን አቅም ለጊዜው እየበረታ ሔደ…”
(La Prima Guerra D’Africa –R Battaglia pp 355 – 360)።

በመጨረሻ፣ በብሔር ተደራጅቶ፣ በብሔር እያሰበ፣ በብሔር እየጠላ፣ በብሔር እየተጋባ፣ ብሔርን አስቦ፣ ፈቅዶና መርጦ ያገኘው መገለጫ ባሕሪው ላደረገው ይህ ትውልድ፣ አስቀያሚውን ያለፈ ታሪክ በብሔር ከፋፍሎ ቁስል መለጣጠፍ ከተጀመረ መጨረሻው አሰቃቂ ይሆናል። ግለሰብ እንጂ ብሔር አድራሻ የለውም። ብሔር ስም አለው እንጂ የግል ስብዕና የለውም። በስሙ ግፍና ወንጀል ይሰራል እንጂ ብሔር በአካል ቀርቦ አይከስም፣ አይከሰስም። ተጠያቂነት መውሰድ ለማይችል “ብሔር” የሚባል አካል የሰጠንው ሃላፊነት በመጨረሻመዓት ይዞብን ይመጣል!!!
******
ስዩም ተ.

ethiothinkthank.com

የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪክ ከአራት ሺሕ ዓመታት የሚያዘልለው ግኝት – (ሔኖክ ያሬድ )

ጥንታዊው የኢትዮጵያ ታሪክ ሲነሳ ‹‹የሦስት ሺሕ ዓመት›› የሚለው ጎልቶ ይሰማል፡፡ የሥልጣኔው መንደርደሪያ ከአክሱም ዘመን ሲያልፍም የይሓ እና የደአማት ሥርወ መንግሥትም ይጠቀሳሉ፡ከሦስት ሺሕ ዘመን ጋርም የንግሥተ ሳባና የልጇ ቀዳማዊ ምኒልክ ታሪክ ይነሳል፡፡ በምሥራቅ ትግራይ የቀድሞው ዓጋመ አውራጃ ዋና ከተማ ዓዲግራት በሰሜን አቅጣጫ 8 ኪሎ ሜትር ተሂዶ የሚገኘው የጉለ መኸዳ ወረዳ ከቀዳሚቷ ንግሥት ጋር የሚያያዝ ታሪክ አለው፡፡ ንግሥቲቱ በኢትዮጵያ ታሪክ ሦስት ዓይነት ስም ሳባ፣ ማክዳ እና አዜብ አላት፡፡ የወረዳው መጠሪያ ‹‹ጉለ መኸዳ›› ከማክዳ ጋር ሲያያዝ ‹‹ጉለ›› (ጐል) የሚለው ቃልም በረት የሚል ትርጉም እንዳለው ይነገራል፡፡ ሳባ ጋር የተያያዘው ስምም ሶበያ በሚባል የሚጠራውና በወረዳው ውስጥ የሚገኘው ጥንታዊ ስፍራ ነው፡፡

ከ43 ዓመት በፊት በጉለ መኸዳ አካባቢ ጥናት ያደረገው ፈረንሣዊው አንፍረይ፣ ባገኛቸው መረጃዎች መሠረት ከሦስት ሺሕ ዓመት በፊት አካባቢው ሰዎች ይኖሩበት እንደነበር ገልጿል፡፡

በቀጣይ ጥናትና ምርምር የሚደገፍ ቢሆንም ንግሥተ ሳባ በዚህ አካባቢ ትኖር እንደነበረ ለመረዳት አያዳግትም ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጉሎ መኸዳ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ሥልጣኔ የሚያመለክቱ በርካታ ቅርሶች  እየተገኙበት ነው፡፡ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሌክቸረሩ አቶ ሐጎስ ገብረማርያም እንደሚገልጹት፣ ከ10 ዓመት በፊት የጉለ መኸዳን ኦርኪዮሎጂካዊ ሀብቶችም ሕቡዕ ምሥጢር አስመልክቶ ለሁለት ዓመት ዳሰሳና ጥናት ተካሂዶ ነበር፡፡

ጥናቱ የምሥራቅ ትግራይ አርኪኦሎጂ ፕሮጀክት የሚባል ሲሆን፣ መቀመጫውን በካናዳ ባደረገው ሳይመን ፍሬሰር ዩኒቨርሲቲ የሚደገፍና በዩኒቨርሲቲው የአርኪዮሎጂ ፕሮፌሰር ካትሪን ዲአንድሪያ የሚመራ ነው፡፡ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በመስቀል በዓል አጋጣሚ ባዘጋጀው ሁለተኛው የአርኪዮሎጂ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ የጉለ መኸዳ አዳዲስ ግኝቶችን የተመለከተ ጥናት በፕሮፌሰሯ ቀርቦ ነበር፡፡

እንደ ፕሮፌሰር ካትሪን ማብራሪያ የሁለት ዓመቱ ዳሰሳዊ ጥናት ከተጠናቀቀ በኋላ በቀጥታ የተገባው ወደ ቁፋሮ ነበር፡፡ የመጀመሪያው ቁፋሮ የተካሄደበት ቦታ የተመረጠው መዝበር ከአክሱም ሥልጣኔ በፊት የነበረን ከተማ የሚያመላክት ፍርስራሽ ሕንፃ ስለተገኘበት ነው፡፡ ይህም ከተማ ከክርስቶስ ልደት በፊት 800 ዓመት ላይ የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ሁለተኛው ቁፋሮ የተካሄደበት ቦታ ዖና ዓዲ የሚባልና በሸዊት ለምለም ቀበሌ መነበይቲ መንደር የሚገኝ ነው፡፡

መነበይቲን ከመዝበር የሚለየው ከአክሱም ሥልጣኔ በፊትና በዘመነ አክሱም መካከል መኖሩ ነው፡፡ እንደ ፕሮፌሰር ካትሪን ማብራሪያ መዝበር ጥንታዊ ማዕከል ሲሆን፣ መነበይቲና አካባቢው ደግሞ ከአክሱም ሥልጣኔ ጋር የሚያመሳስለው ቅሪቶችን ይዞ መገኘቱ ነው፡፡ በዋናነት በመዝበር የተካሄደው ጥናት እጅግ ጥንታዊና በጊዜው የነበረውን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊን ይዞታ ምን ይመስል እንደነበር ምላሽ የሚሰጥ ነው፡፡

መዝበር

በጻሕዋ አካባቢ የሚገኝና ለአምስት ዓመት ያህል ቁፋሮ የተካሄደበት ስፍራ ነው፡፡ ግኝቱም የሚያሳየው በአክሱም ሥልጣኔ በፊት ከክርስቶስ ልደት 1000 – 1500 ዓመት በፊት ታላቅ ማዕከል ሆኖ መኖሩ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ትልቅ ቦታ ካለው ከይሓም ከ400 እስከ 450 ዓመት በፊት እንደሚቀድም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በመዝበር ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረ ሥልጣኔ እንደነበረም ተረጋግጧል፡፡ ይህም ከደቡብ ዓረቢያ የፈለሱ ሰዎች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት የነበረ ሥልጣኔ መሆኑን መረጋገጡን ፕሮፌሰር ካትሪን ገልጸዋል፡፡

እንደ ፕሮፌሰሯ አገላለጽ፣ ቀደም ሲል የአርኪዮሎጂ ተመራማሪዎች ጥንታዊ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ መነሻን ከዓረብ ከፈለሱ ሰዎች ጋር የተያያዘ ነው የሚለው እምነታቸው ትክክል አለመሆኑን ኢትዮጵያውያን የራሳቸው ጥንታዊ ሥልጣኔ እንደነበራቸው በመዝበር የተገኘው መረጃ አረጋግጧል፡፡ የመዝበር ሥልጣኔ ፍልሰተኞች ከመምጣታቸው 800 ዓመታት በፊት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ሲሉም አስምረውበታል፡፡

ሌሎቹ ግኝቶች በዘመኑ የተላመዱ የቤት እንስሳት እነ በግ፣ ግመል፣ ፍየል፣ ውሻ፣ አህያ፣ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ የተሟላ መረጃ የያዘ የዶሮ ቅሪተ አካል በዚሁ ስፍራ መገኘቱም ተጠቁሟል፡፡ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ጥንታዊ የድንጋይ መሣርያዎችም መገኘታቸው የዘመኑን ዕደ ጥበብና ሥነ ጥበብ ምን ያህል እንደነበርም ተመራማሪዋ አመልክተዋል፡፡

ዖና ዓዲ (መነበይቲ)

መነበይቲ ከአዲስ አበባ 916 ኪሎ ሜትር ግድም የምትገኝ ከፋፂ ወደ ዛላምበሳ በሚወስደው አውራ ጎዳና በምሥራቅ አቅጣጫ ተገንጥሎ ሁለት ኪሎ ሜትር ተጉዞ የሚገኝ ስፍራ ነው፡፡

በአፈ ታሪክ የንግሥተ ሳባ ጥንታዊ ቤተ መንግሥት የሚገኝበት፣ ቀዳማዊ ምኒልክ ማይበላ (አስመራ አካባቢ) ከተወለደ በኋላ ወደዚህ ቤተ መንግሥት መምጣቱና ማደጉ ይነገራል፡፡ የመንደሩ ነዋሪ የሆኑት ቄስ ገብረ ሕይወት ምኒልክ እዚህ ቦታ እንዳገሩ ባህል ቃርሳ እየተጫወተ ማደጉን ወላጆቻችን ያቆዩልን ታሪክ ነው ይላሉ፡፡

በመነበይቲ በቁፋሮ የተገኙት የሕንፃ ፍራሾች፣ የሸክላ ሥራዎች፣ የሰውና የእንስሳት ቅሪተ አካል ቅድመ አክሱምና በዘመነ አክሱም የነበሩ መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡

የመነበይቲ ቁፋሮ ተጀመረ እንጂ አልተገባደደም የሚሉት ፕሮፌሰር ካትሪን ለሦስት ዓመት የተከናወነው ቁፋሮ ተጨማሪ ሰባት ዓመታት ያስፈልገዋል፡፡ በመነበይቲ እየተካሄደ ያለው ቁፋሮ ለበርካታ ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጥ፣ ይህም የአክሱም ሥልጣኔ ገንኖ በነበረበት ጊዜ በመነበይቲ የነበረው የንግድ እንቅስቃሴ  ምን ይመስል እንደነበር፣ ራሱን ችሎ ነው ወይስ ከሌሎች ጋር ተሳስሮ ነው የሚለው ወደፊት የሚታይ ነው፡፡

እንደ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዓለም መብርሃቱ አገላለጽ፣ የትግራይ አካባቢ የሃይማኖቶች ሁሉ መጀመሪያ፣ የሥልጣኔዎችም ከይሓና ከአክሱም ጀምሮ የሚታወቅ ነው፡፡ በዋናነት ደግሞ መነበይቲ የንግሥት ማክዳ (ሳባ) የቅድመ የሓ የቅድመ አክሱም ቤተ መንግሥት እንደነበረ የካናዳ ፕሮፌሰሮች ከኢትዮጵያውያን ምሁራን ጋር ሆነው እየሠሩት ያለው ጥናት እንዲሁም በመነበይቲ የተገኘው የንግሥት ማክዳ ቤተ መንግሥት ፍራሽ የኢትዮጵያን ታሪክ በአንድ ዕርምጃ ወደፊት የሚወስድ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በመዝበርም ሆነ በተለያዩ አካባቢዎች የተገኙ ልዩ ልዩ ቅርሶችን የሚቀመጡበት ሙዚየም ለማስገንባት እንቅስቃሴ የተጀመረ መሆኑንና የዓዲግራት ከተማ አስተዳደርም ለሙዚየሙ መገንቢያ የሚፈለገውን ያህል መሬት ለመስጠት በዓለም አቀፍ ጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ቃል ገብቷል፡፡
*****
October 18, 2015 – ምኒሊክ ሳልሳዊ — Comments ↓

ethiothinkthank.com

ለነፃነት ዋጋ በሚሰጥበት ሀገር ለጀግኖች ተገቢው ክብር ይሰጣል!

ባለፈው ወር ከአብዲሳ አጋ ልጅ ጋር በተያያዘ አንዲት ፅሁፍ እዚህ ፌስቡክ ላይ አውጥቼ ነበር። ያን ተከትሎ አንዳንድ ግለሰቦች ለአብዲሳ አጋ ቤተሰብ በራሳቸው ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት አንዳላቸው በመግለፅ፣ የቤተሰቡን አድራሻ እና አንዳንድ መረጃዎች ጠይቀውኝ ነበር። በዋናነት ማህሌት በላቸው ያሳየችው ተነሳሽነት እና ያደረገችው ጥረት በጣም የሚመሰገን ነው።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል በቅድሚያ ስለ ቤተሰቡ እና የኑሮ ሁኔታ የተሟላ መረጃ ሊኖር ይገባል። በዚህ መሰረት፣ ዛሬ የአብዲሳ አጋ ልጅ ከሆነው ከኤልያስ አብዲሳ ጋር የግማሽ ሰዓት (29.22 ደቂቃ) ያህል ቆይታ በማድረግ ውይይታችንን በሞባይሌ መቅረፀ-ድምፅ ቀድቼዋለሁ። ስለ አብዲሳ አጋ ቤተሰብ ያለውን ነባራዊ እውነታ ለማወቅና በተቋም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ድጋፍ ለማድረግ ለምትሹ ግለሰቦች የድምፅ መረጃውንና ሌሎች ማስረጃዎችን በኢሜል አድረሻችሁ መላክ ይቻላል።

በምናባዊ እሳቤ ካልሆነ በስተቀር በእውን ለማሰብ ከሚከብደው የጀግንነት ታሪኩ ውስጥ የተወሰነች ነገር ለማለት ያህል….አብዲሳ አጋ በፋሽስቶች ተማርኮ ወደ ሮም ከተወሰደና ከእስር ቤት አምልጦ ከወጣ በኋላ እዚያው በኢጣሊያን ሀገር የሸፈተ፣ የራሱን አማፂ ቡድን አቋቁሞ በሁለተኛው አለም ጦርነት በፋሽስቶች እና ናዚዎች መቃብር ላይ የነፃነት ችቦ የአበራ…በተለይ ፋሽስት ጣሊያን ሲወድቅ የኢትዮጲያን ሰንደቅ-አላማ እያውለብለበ ከፊት ቀድሞ ሮም ከተማ የገባ፣ ቀጥሎ የጀርመን ናዚ ሲወድቅም ደግሞ በተመሳሳይ የሀገሩን ሰንደቅ-አላማ እያውለበለበ በርሊን የገባ ከሀገሩ አልፎ በአለም የነፃነት ትግል ውስጥ አኩሪ ታሪክ የፈፀመ፣ የነፃነት ፈር-ቀዳጅ ኢትዮጲያዊ ነው። 

ከዚህ ጀግና ልጅ፣ ከኤልያስ አብዲሳ አጋ ጋር በነበረኝ ቆይታ ስለ ቤተሰብ እና የኑሮ ሁኔታ የተገነዘብኳቸውን አንዳንድ ነጥቦችን ለመጥቀስ ያህል… አብዲሳ አጋ ከአውሮፓ ወደ ሀገሩ ከተመለሰ በኋላ በአስቸጋሪ ሕይወት ውስጥ ትዳር መስርቶ ይኖር የነበረ ቢሆንም በግምት ከዛሬ 50 ዓመት በፊት (1950ቹ መጨረሻ አከባቢ) የመጀመሪያ ሚስታቸው በሞት ተለይተዋቸዋል። በመቀጠል፣ እስከ አሁን በሕይወት የሚገኙትን ወ/ሮ ቀለሟን በማግባት የ48 ዓመቱ ኤልያስ አብዲሳን ወልዷል። አብዲሳ አጋ በሞት እስከተለየበት 1970 ዓ.ም ድረስ፣ አዲስ አበባ ውስጥ ወሎ-ሰፈር ከወ/ሮ ቀለሟ እና ከእና ኤልያስ ጋር የኖረ ሲሆን፣ በተለይ ኤልያስ በጥንታዊት ኢትዮጲያ የጀግኖች አርበኞች ማህበር፣ “የአርበኛው ተተኪ ልጅ“ በሚል ሙሉ እውቅና የተሰጠው ከመሆኑም በተጨማሪ፣ አባቱ በተለያዩ የጦርነት አውድማዎች የተሸለማቸው ሜዳሊያዎች፣ ኒሻኖች፣ የተለያዩ የክብርና ወታደራዊ ማዕረጎች፣ እንዲሁም የግል ሕይወት ታሪክ (ድያሪ) ጥራዝ ጭምር በኤልያስ እጅ ይገኛሉ። 

ከኤልያስ ጋር ባደረኩት ቆይታ፣ የአብዲሳ አጋ’ን ጀግንነትና ክብርን እንዲያስጠብቅ “የአርበኛው ተተኪ ልጅ“ የሚለውን የክብር ስያሜ ልዩ መታወቂያን በማየቴ በጣም አስደንቆኛል።  የሆነ ልዩ የሆነ ክብር ስሜት ይፈጥራል። ነገር ግን፣ አብዲሳ አጋ እስከ ሕይወታቸው መጨረሻ አብረዋቸው የኖሩት የወ/ሮ ቀለሟ ሆነ የኤልያስ ሕይወት በጣም አሳዘኝ ነው። በተለይ፣ አብዲሳ አጋ አዲስ አበባ፣ ወሎ ሰፈር 1300 ካሬ ሜትር ስፋት ባለው ግቢ ውስጥ መኖሪያ ቤት ሰርቶ ለቤተሰቡ አውርሶ ኖሯል። ባለቤቱም ቀድሞ ያገኙት በነበረው 163 ብር የጡረታ ገንዘብ ፈፅሞ መኖር ስለማያስችላቸው፣ የመኖሪያ ቤቱን የተወሰኑ ክፍሎች እያከራዩ ጥሩ የሚባል ኑሮ ይኖሩ ነበር። ነገር ግን፣ የስድስት መቶ ሺህ ብር ካሳና የ1300 ካሬ ሜትር ቦታ ወስዶ 200 ካሬ ሜትር ቦታ በምትኩ በመስጠት አብዲሳ አጋ ለቤተሰቡ ሰርቶ ያወረሰው መኖሪያ ቤት መንግስት አፍርሶታል። በዚያ ላይ፣ ለቤቱ የተከፈለው የካሳ ገንዘብ ከቀድሞ ሚስታቸው ከተወለዱት ልጆች ጋር የተካፈሉ መሆኑ ሲታሰብ፣ ወ/ሮ ቀለሟ ከባለቤታቸው ጋር በጋራ የሰሩትን የመኖሪያ ቤት መስራት ቀርቶ፣ አንዲት ማረፊያ ጎጆ የተሰራው እንኳን በሌሎች ሰዎች ድጋፍ ነው። በዚህ በተረፈ፣ በአሁን ወቅት ወ/ሮ ቀለሟ የሚተዳደሩበት የአብዲሳ አጋ ባለቤትነታቸው በሚያገኙት የጡረታ ገንዘብ ሲሆን፣ ይህም በወር 500 ብር ነው። ደሃ ሀገር ለአለምና ለጀግናዋ የምትከፍለውን የጡረታ ገንዘብ መጠንን አያችሁልን?

መንግስት አብዲሳ አጋ በጡረታ ዘመኑ ሰርቶ ለቤተሰቡ ያወረሰውን ንብረት አፍርሶ በምትኩ ፍፁም ተመጣጣኝ ያልሆነ የካሳ ክፍያ ከፍሎ ሚስትና ልጆቹን አፈናቅሏቸዋል። ይህ ለኢትዮጲያ ነፃነት የወጣትነት ዘመኑን ሙሉ-በሙሉ አሳልፎ ለሰጠ ብሔራዊ ጀግና፣ ለአብዲሳ አጋ ፍፁም የማይገባ ድርጊት ነው። የነፃነት ትርጉምና ፋይዳ የገባን ኢትዮጲያኖች፣ ለሀገራችን ነፃነት ዋጋ የምንሰጥ ዜጎች ለአብዲሳ አጋ ቤተሰብ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ለጀግኖቻችን ክብር እንስጥ!!!

ስዩም ተ.

ethiothinkthank.com

An ancient African genome has been sequenced for the first time.

Researchers extracted DNA from a 4,500-year-old skull that was discovered in the highlands of Ethiopia.
A comparison with genetic material from today’s Africans reveals how our ancient ancestors mixed and moved around the continents.

The findings, published in the journal Science, suggests that about 3,000 years ago there was a huge wave of migration from Eurasia into Africa.
This has left a genetic legacy, and the scientists believe up to 25% of the DNA of modern Africans can be traced back to this event.

“Every single population for which we have data in Africa has a sizeable component of Eurasian ancestry,” said Dr Andrea Manica, from the University of Cambridge, who carried out the research.

Petrous bone
Ancient genomes have been sequenced from around the world, but Africa has proved difficult because hot and humid conditions can destroy fragile DNA.
However, the 4,500-year-old remains of this hunter gatherer, known as Mota man, were found in a cave and were well preserved.

Importantly, a bone that is situated just below the ear, called the petrous, was intact.

Dr Manica, speaking to Science in Action on the BBC World Service, said: “The petrous bone is really hard and does a really good job of preventing bacteria getting in and degrading this DNA.

“What we were able to get is some very high quality undamaged DNA from which we could reconstruct the whole genome of the individual.

“We have the complete blueprint, every single gene, every single bit of information that made this individual that lived 4,500 years ago in Ethiopia.”

Mass moves
The genome revealed that Mota man had purely African DNA, his ancestors had never moved from Africa.

But the comparison of this with modern African genomes highlighted that about 1,500 years after his death, the make-up of the continent had changed.

Genetic studies have shown that after the great migration out of Africa, which happened about 60,000 years ago, some people later returned to the continent.

But this study shows that about 3,000 years ago there was a much larger migration than had been thought.

The Neolithic farmers from western Eurasia who, about 8,000 years ago, brought agriculture to Europe then began to return to Africa.

“We know now that they probably corresponded to a quarter of the people that already lived in East Africa (at that time). It was a major backflow, a very sizeable movement of people,” said Dr Manica.

It is unclear what caused this move – potentially changes happening in the Egyptian empire – but it has left a genetic legacy.

“Quite remarkably, we see in Ethiopia about 20% – so a fifth – of the genome of people living there right now is actually of Eurasian origin, it actually comes from these farmers,” explained Dr Manica.

“But it goes further than that, because if you go to the corners of Africa, all the way to West Africa or South Africa, even populations that we really thought were purely African have 5-6% of their genome that dates back to these western Eurasian farmers.”

Neanderthal genes
The Eurasians’ return also introduced some extra genetic material to Africa.
The genes their ancestors had picked up from interbreeding with Neanderthals were then passed to Africans, and can still be seen today.

Commenting on the research, Dr Carles Lalueza-Fox, from the Institute of Evolutionary Biology in Barcelona, Spain, said: “What is nice is that it places in time the origin of the Eurasian backflow into Africa already detected some years ago from modern genome data, and it turns out to be the farming.

“Once again, like in the case of Europe where we see dramatic genomic turnover, the spread of agriculture has had a huge impact even in a continent where large groups continued to be hunter gatherers.

“And it is also interesting to discover now that even sub-Saharan Africans have a bit (0.3-0.7%) of Neanderthal ancestry.”

Prof David Reich, from Harvard Medical School in the US, added: “The claim that all sub-Saharan Africans today have a substantial amount of ancestry due to back-to-Africa migrations is quite interesting, and while I won’t be 100% convinced until I look at the data myself, I think the analyses seem careful and thoughtful.

“While previous studies have documented substantial West Eurasian ancestry in some sub-Saharan African populations, including Nigerians and KhoeSan from southern Africa, if the findings of this paper are right, they are important because they extend these claims to populations that were previously thought to have little or no West Eurasian ancestry, for example Mbuti hunter gatherers from central/east Africa.”

Courtesy of http://www.bbc.com/worldservice

ethiothinkthank.com