በጭቁኖች ሀገር የመናገር ነፃነት ያላቸው “እብዶች” ብቻ ናቸው!

የአማርኛ መዝገበ ቃላት “ምሁር” የሚለውን ቃል “በትምህርት፥ በዕውቀት የበሰለ አዕምሮ ያለው ሰው” በማለት ይገልፀዋል። ነገር ግን፣ ትምህርት ሆነ ዕውቀት በማህብረሰቡ ሕይወት ላይ እሴት የማይጨምር ከሆነ ፋይዳ-ቢስ ነው። እንዲህ ያለ ትምህርት፥ ዕውቀት በማህብረሰቡ ዘንድ ዋጋና ክብር አይሰጠውም፣ ለራሳችንም ቢሆን እርካታ አይሰጥም! ስለዚህ “ምሁር” የሚባለው የተማረ ብቻ ሳይሆን በትምህርት ያገኘውን ዕውቀትና ክህሎት ተጠቅሞ በማህብረሰቡ ዘንድ ለውጥና መሻሻል … Continue reading በጭቁኖች ሀገር የመናገር ነፃነት ያላቸው “እብዶች” ብቻ ናቸው!

አብረን እየኖር ተለያይተናል: ነፃነት ያስፈልገናል! (ክፍል-2)

እስኪ ልጠይቅህ ወዳጄ፣…”ኢትዮጲያዊ ነህ?” መልስህ “አዎ” ከሆነ አንዴ ቆየኝ፣ “አይደለም” ከሆነ ደግሜ ልጠይቅህ፣ “እሺ…ምንድን ነህ?” ከዜግነት ይልቅ ብሔር አስቀድመህ፤ “መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ፥ አማራ ነኝ፥ ትግራዋይ ነኝ፥ … ቀጥሎ ደግሞ ‘ኢትዮጲያዊ ነኝ’” ከሚሉት ጎራ ነህ። አሁንም መልስህ “አዎ” ከሆነ መልካም፣ አይደለም ከሆነ ደግሞ “ታዲያ አንተ ማን ነህ?” ከደርግ ቀይ-ሽብር ወይም ከኢህአዴግ ፀረ-ሽብር በተዓምር ተርፈህ አሊያም በዲቪ-ሎቶሪ … Continue reading አብረን እየኖር ተለያይተናል: ነፃነት ያስፈልገናል! (ክፍል-2)

ሁሉም ሰው ለራሱ ነፃ-አውጪ፣ በራሱ ነፃ-ወጪ ነው!

ነፃነት ምንድነው? “ፍቃድ” (Will) ማለት በሃሳብ ላይ ብቻ በመመስረት አንድን ነገር ለመፍጠር ወይም ለማድረግ መሞከር ነው። አንድ ሰው፣ የተወሰነ ሃሳባዊ ወይም አካላዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ወይም ባለማድረግ ፍቃዱን በተግባራዊ እንቅስቃሴ ሲገልፅ መፍቀድ ወይም መምረጥ (willing or volition) ይባላል። “ፍቃደኛ” (voluntary) የሚለው ደግሞ በራስ ሃሳብ ላይ ተመስርቶና ያለ ምንም ውጫዊ ኃይል አስገዳጅነት መንቀሳቀስ ወይም ከእንቅስቃሴ መቆጠብ እንደማለት … Continue reading ሁሉም ሰው ለራሱ ነፃ-አውጪ፣ በራሱ ነፃ-ወጪ ነው!

የጄ/ል መንግስቱ ነዋይ ኑዛዜ

እናንት ዳኞች የበየናችሁብኝን የሞት ፍርድ ያለ ይግባኝ ተቀብያለሁ፡፡ ይግባኝ ብየ ጉዳየን የሚመለከትልኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ቢሆን ኖሮ ይግባኝ ማለት በፈለግሁ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ እንደማይሆን አውቃለውና በይግባኝ የአፄ ኃ/ስላሴን ፊት ማየት አልፈቅድም፡፡ በእግዚያብሄር ስም ተሰይማችሁ ከተቀመጣችሁበት የፍርድ ወንበር ላይ ከመቀመጣችሁ በፊት በእኔ ላይ የምትሰጡትን የዛሬውን ፍርድ ታውቁት እንደነበር ሳስብና ፍርድ እስከዚህ መርከሱን ስታዘብ ሀዘኔ ይበዛል፡፡ ለኢትዮጵያ … Continue reading የጄ/ል መንግስቱ ነዋይ ኑዛዜ