ፖለቲካችን የስሜት ምርኮኛ መሆኑ ብሔራዊ መተማመን ያሳጣናል!

በያሬድ ኃይለማርያም ባለፉት በርካታ አመታት የአገራችን ፖለቲካ ተናዳፊ ስለነበር ብዙዎች መስሎ ማደርን ወይም ዝምታን መርጠው እንዲኖሩ አድርጓል። ጥቂቶች ብቻም ህይወታቸውን፣ ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ገንዘባቸውን እና ነጻነታቸውንም ጭምር ሰውተው አፋኝ ከሆነው ሥርዓት ጋር ሲተናነቁ ቆይተዋል። ከሥርዓቱ መዳከም ዋዜማ ጀምሮ ደግሞ አብዛኛው በዝምታ ይኖር የነበረው የህብረተሰብ ክፍል ሲነቃቃ ተስተውሏል። የአገዛዝ ሥርዓቱ በለውጥ ማዕበል ተመቶ ጉልበቱ ከተብረከረከበት እና ተረቶም … Continue reading ፖለቲካችን የስሜት ምርኮኛ መሆኑ ብሔራዊ መተማመን ያሳጣናል!

ከደጋፊ ጋራ መወያየት ሆነ መግባባት አይችልም!

ከደጋፊዎች ጋር መሰረታዊ የሆነ ተቃርኖ ያለኝ ይመስለኛል። ከመንግስት ብቻ ሳይሆን ከየትኛውም አካል ደጋፊዎች ጋር የምስማማ አይመስለኝም። አሁንማ ቃሉ ራሱ ሲጠራ የሆነ ጎዶሎ፥ የራሱ የሆነ ነገር የሌለው፥ በራሱ መቆም የማይችል፥… ወዘተ የሚል ስሜት ይሰማኛል። ታዲያ ዛሬ የአማርኛ መዝገበ ቃላትን ከፍቼ የቃሉን ፍቺ መፈለግ ጀመርኩ። በመጀመሪያ “ደገፈ” ማለት “1. ድጋፍ ሆነ። 2. ረዳ፥ አገዘ። 3. ቀደም ሲል … Continue reading ከደጋፊ ጋራ መወያየት ሆነ መግባባት አይችልም!