​አነጋጋሪዉ የክልል ፍርድ ቤቶች ስልጣን በፌደራል ጉዳዮች ላይ! (በቃሉ ፈረደ)

አሁን አሁን የክልል ፍርድ ቤቶች በፌደራል ጉዳይ ላይ ያላቸዉን የዉክልና ስልጣን አስመልከቶ አዲስ የክርክር ምዕራፍ እየተነሳ ይመስላል፡፡ እስካሁን ይህ ጉዳይ አነጋጋሪ ሳይሆን ቢቆይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሚታዩ ጉዳዮች በተለይም ከሽብረተኝነት ክስ ጋር በተገናኘ ጉዳዩ ተደገጋግሞ እየተነሳ ይገኛል፡፡ ከተነሱ ጉዳዮች ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ከተወሰኑት ዉስጥ፡- 1ኛ. … Continue reading ​አነጋጋሪዉ የክልል ፍርድ ቤቶች ስልጣን በፌደራል ጉዳዮች ላይ! (በቃሉ ፈረደ)

​የወልቃይት ሕዝብ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት በዳኛ  ዘርዓይ ወልደሰንበት ላይ ያቀረቡት ተቃውሞ

"ዳኛው በእንዲህ አይነት ግልፅ የሆነ ተቃራኒ አቋም ውስጥ ሆነው ከዚህ ጉዳይ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት ያለንን ተከሳሾች ጉዳይ ሚዛናዊ ዳኝነት ይሰጣሉ የሚል እምነት የለንም" በእኛ በኩል  እንኳን ይህ ግልፅ ማስረጃ ባለበት ይቅርና እንዲሁ ጥርጣሬ ቢያድርብን እንኳን ተቃውሞ የቀረበባቸው ዳኛ ክርክሩን በግድ እዳኛለሁ እንደማይሉ እና በመቃወማችን ብቻ የአዋጁን አንቀፅ 27(2) መሰረት በማድረግ ተቃውሟችን በሌሎች ዳኞች ከመወሰኑ በፊት … Continue reading ​የወልቃይት ሕዝብ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት በዳኛ  ዘርዓይ ወልደሰንበት ላይ ያቀረቡት ተቃውሞ

ተከሳሾች በዳኞች ላይ ተቃውሞ በማቅረባቸው ከ3-6 ወር በሚደርስ እስራት ተቀጡ! 

​አስቻለው የተባለ ተከሳሽ ሱሪውን አውልቆ በምርመራ ወቅት የተኮላሸውን ብልቱን በችሎት አሳይቷል።   በእነ ተሻገር ወልደሚካኤል ክስ መዝገብ እስረኞች አቤቱታ ሲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ሲያቋርጥ የሚናገረው ተከሳሽ ሀሳቡን እንዲጨርስ የተናገረ ሌላ ተከሳሽ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ከተቀመጠበት ወጠቶ ወደ ችሎቱ እንዲቀርብ ተደርጓል። ተከሳሹ እንዲወጣ ሲጠየቅ ሌሎች ተከሳሾች "እኛም እንወጣለን" ብለው ተቃውሞ አሰምተዋል። መሃል ዳኘው መጀመርያ " እንደሱ ከሆነ … Continue reading ተከሳሾች በዳኞች ላይ ተቃውሞ በማቅረባቸው ከ3-6 ወር በሚደርስ እስራት ተቀጡ! 

​በ16 እስረኞች ላይ በምርመራ ወቅት የደረሰ ጉዳት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የክስ መዝገብ በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ የተከሰሱ 16 እስረኞች ላይ በምርመራ  ወቅት የደረሰባቸውን ጉዳት በሪፖርቱ አኳትቷል። በዚህም መሰረት:_ ከበደ ጨመዳ: ቀኝ እጅ ላይ ትንሽ ጠባሳ፣ ቀኝ እግር አውራ ጣት ስብራት፣ ኢብራሂም  ካሚል: ቀኝ  እግር ላይ ጠባሳ፣  ግራ እጅ ላይ ጠባሳ፣ የካቴና እስር ምልክቶች አግባው ሰጠኝ: ግራ ታፋ … Continue reading ​በ16 እስረኞች ላይ በምርመራ ወቅት የደረሰ ጉዳት

በድብደባና ሕክምና እጦት ምክንያት ተከሳሾች ፍርድ ቤት መቅረብ አልቻሉም

በኦነግ ክስ የቀረበባቸው እነ መርጋ ደበሎ የክስ መዝገብ 2ኛ ተከሳሽ ቀናቴ ፈይሳ  ዛሬ በነበረው ቀጠሮ  አልቀረቡም። አቶ ቀናቴ በምርመራ ወቅት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ከደረሰባቸው ድብደባ በተጨማሪ  ህክምና ባለማግኘታቸው  በድብደባው የደረሰባቸው ጉዳት ወደ ካንሰር ተቀይሮባቸው በህመም ላይ መሆናቸውን 1ኛ ተከሳሽ መርጋ ደበሎ ለፍርድ ቤቱ ገልፀዋል።  አቶ ቀናቴ ህክምና እንዲያገኙ 1ኛ ተከሳሽ መርጋ ደበሎ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ … Continue reading በድብደባና ሕክምና እጦት ምክንያት ተከሳሾች ፍርድ ቤት መቅረብ አልቻሉም

​ተከሳሾች ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት እንዲነሱላቸው ጥያቄ አቀረቡ

"እሱ ተከራካሪ፣ እሱ መልዕክት አስተላላፉ፣ እሱ ዳኛ ሊሆን አይችልም"  አቶ አታላይ ዛፌ "የተከሰሳችሁት በወልቃይት አማራ ማንነት ነው ወይስ በሽብርተኝነት የሚለው የሚታይ ይሆናል" ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት "እኚህ ዳኛ  በማህበራዊ ሚዲያ ያቀረቡት የህወሓትን አቋም ነው" ዘመነ ጌቴ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የግራ ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት ሊዳኙን አይገባም ሲሉ ተከሳሾች ጥያቄ አቅርበዋል። ዛሬ … Continue reading ​ተከሳሾች ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት እንዲነሱላቸው ጥያቄ አቀረቡ

​አቶ ማሙሸት አማረ  ዐቃቤ ሕግ  ባቀረበባቸው  የሰነድ ማስረጃ ላይ ያቀረቡት ትችት 

"በደህንነት ሪፖርቱ ተዘጋጀ የተባለው፣ ተከሳሽ ሲጠቀምባቸው ነበሩ የተባሉ ሰባት የሚደርሱ ተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥሮች ተጠልፈዋል በሚል ነው፤ ነገር ግን እነዚህ በማስረጃነት ቀረቡ የተባሉት ስልክ ቁጥሮች በእርግጥም በተከሳሽ ስም ስለመመዝገባቸው ከኢትዩ-ቴሌኮም ጋር የተደረገ የደንበኝነት ውል ማስረጃ አልቀረበም፣ የማን እንደሆኑም አይታወቅም፣ ይበልጡኑ ደግሞ፣ የደህንነቱ ሪፖርቱ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ የጸዳ ሆኖ ትክክለኛ ፍትህ መስጠት እንዲቻል፣ ተደረገ የተባለው የተጠለፈው የስልክ ልውውጥ … Continue reading ​አቶ ማሙሸት አማረ  ዐቃቤ ሕግ  ባቀረበባቸው  የሰነድ ማስረጃ ላይ ያቀረቡት ትችት 

“መሳሪያ ይዛችሁ የመጣችሁት ስርዓት ለማስከበር ነው!” የመሃል ዳኛ፣ “ዳኛ መሆን ከባድ ነው!” እስረኛ

"በዚህ ፍትህ በሌለበት ሀገር እንደኛ መሆን መታደል ነው። ዳኛ መሆን ከባድ ነው።……ቢገባችሁ የምንታገለው ለእናንተም  ነው!" ቴዎድሮስ አስፋው "መሳሪያ ይዛችሁ የመጣችሁት ስርዓት ለማስከበር ነው! " መሃል ዳኛው ለማረሚያ ቤቱ  ፖሊስ አዛዥ   "የዘገየ ፍትህ  እንደተከለከለ ይቆጠራል ያላችሁን ራሳችሁ ናችሁ"   ፍሬው ተክሌ ዛሬ ህዳር 8/2010 ዓም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በእነ ትንሳኤ … Continue reading “መሳሪያ ይዛችሁ የመጣችሁት ስርዓት ለማስከበር ነው!” የመሃል ዳኛ፣ “ዳኛ መሆን ከባድ ነው!” እስረኛ

​በንግስት ይርጋ ላይ የተፈፀመ ጭካኔ

መስከረም 5/2009 ዓም ከምሽቱ 1:00 ሳንጃ ከተማ የተያዝኩ ሲሆን ወዲያውኑ እንደተያዝኩ በተፈፀመብኝ ድብደባ አእምሮዬን በመሳቴ  24 ሰዓት  ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዴትና በምን እንደመጣሁ ሳላውቅ መስከረም 6/2009 ዓም  ከጠዋቱ 4:00  ላይ የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በሰው ተደግፌ እና በጭቃ ተለውሼ  ስቀርብ ማስታወስ ጀመርኩ። በጭካኔ በዱላ ተቀጥቅጬ መቁሰሌ  እየታየ  ወደ ሀኪም ቤት በመውሰድ … Continue reading ​በንግስት ይርጋ ላይ የተፈፀመ ጭካኔ

​በፀረ ሽብር አዋጁ የተበተነ ቤተሰብ!

የፀረ ሽብር አዋጁ ሲወጣ በርካታ ትችቶች ቀርበውበታል። የመደራጀትና ሀሰብን በነፃነት የመግለፅ መብትን የሚፃረር ገዳይ ሕግ ስለመሆኑ ብዙ ተብሎለታል። የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የሚረገጡበት ሕግ ስለመሆኑ ቀድሞ ተተንብዮለታል። በጭላንጭል ላይ ያለውን የተቃውሞ ጎራ በማዳፈን የሀገርን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ  ግብአተ መሬት እንደሚከት ታምኖበታል።  ይህ አዋጅ እንደተባለለትም  በርካታ ኪሳራዎችን አድርሷል። ለአሁኑ የቁልቁለት ጉዞ የፀረ ሽብር አዋጁ አይነት መግዢያ ሕጎች … Continue reading ​በፀረ ሽብር አዋጁ የተበተነ ቤተሰብ!