“ሸዋ የሌለበት፣ ሴት የበዛበት ካቢኔ!” በያሬድ ጥበቡ

በትላንትናው ዕለት ዶክተር አቢይ አህመድ የኢትዮጵያን የሚኒስትሮች ምክርቤት በግማሹ በሴቶች በመሙላታቸው ደሰታውን የሚገልፀው ወንድ ብዙ ነው። ለብዙ አስርተ ዓመታት ለሴቶች እኩልነት የተሟገትኩ በመሆኔና በትጥቅ ትግሉ ረጅም ዓመታትም የነበራቸውን የመንፈስም ሆነ የአካል ጥንካሬ ስላየሁ እንደብዙው የዓለም ወንድ በጉዳዩ ላይ ችግር የለኝም። ዛሬ ግን ምስቅልቅል ስሜት ነው የተሰማኝ፣ የደስታም የስጋትም ። በትላትናው ዕለት የተሾሙት ሴት ሚኒስትሮች ከዓለሙ … Continue reading “ሸዋ የሌለበት፣ ሴት የበዛበት ካቢኔ!” በያሬድ ጥበቡ

ኦሮማራ ክፍል 2፡ አፓርታይድ ከደደቢት እስከ ቤተ-መንግስት

የኦሮማራ ጥምረት መሰረታዊ ዓላማን ለመረዳት በቅድሚያ በህወሓት መሪነት ስለተዘረጋው መንግስታዊ ስርዓት ግልፅ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል። የህወሓትን ዓላማና ግብ ጠንቅቀው ከተረዱ የፖለቲካ ልሂቃን መካከል ደግሞ አቶ ያሬድ ጥበቡ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። የኢህዴን/ብአዴን መስራችና አመራር የነበረው አቶ ያሬድ በአክራሪ ብሔርተኝነት ላይ የተመሰረተው የህወሓት የፖለቲካ አጀንዳ እንኳን ለተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመጣበት የትግራይ ህዝብ የማይበጅ መሆኑን ቀድሞ ተገንዝቧል። የመሰረተውን … Continue reading ኦሮማራ ክፍል 2፡ አፓርታይድ ከደደቢት እስከ ቤተ-መንግስት

“ያልተሰማው ነብይ – ያሬድ ጥበቡ!” በተመስገን ደሳለኝ

በ1960ዎቹ አጋማሽ በ“ጥናት ክበብ” ስም በየመንደሩ ለውይይት መሰባሰብ ፋሽን በነበረበት በዚያን ዘመን፣ ታላላቅ አገራዊና ወቅታዊ አጀንዳዎችን በግራ-ዘመም አስተምህሮ በማጥናት የፖለቲካ “ፊደላትን” ሀሁ… ብሎ መቁጠር የጀመረው ያሬድ ጥበቡ፣ ከአቻዎቹ ጋር “አብዮት” የተሰኘ ፀረ ዘውድ ምስጢራዊ ቡድን ከመመሥረት ያገደው አልነበረም፡፡ ግና፣ ለውጥ በብሶት ክምችት እንጂ በቀጠሮ አይመጣምና እነያሬድ በ‹ዳስ-ካፒታል› ሲራቀቁ፣ በስታሊን ከራቫት ሲወዘገቡ፣ በማኦ ሰላምታ ሲነታረኩ፣ በሆችሚኒ … Continue reading “ያልተሰማው ነብይ – ያሬድ ጥበቡ!” በተመስገን ደሳለኝ