ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አቅርበው ስልጣን ላይ ያሉ ሹመኞች ጉዳይ እየተጣራ ነው

ዋዜማ ራዲዮ-በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ይዘው የሚገኙ ግለሰቦችንና ሌሎች የክልልና የፌደራል መንግስት ሰራተኞችን የትምህርት ማስረጃዎች የማጣራት ስራ ተጀመረ። ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) ከትምህርት ሚንስቴር ጋር እያደረገ ባለው ምርመራ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሀሰተኛ ሰነድ በማቅረብ ተለይተዋል። ከቅርብ ወራት ወዲህ በኢትዮጵያ ክልሎችን ጨምሮ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ለበርካታ ዓመታት በተጭበረበረና በሐሰት የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው በሚሰሩ … Continue reading ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አቅርበው ስልጣን ላይ ያሉ ሹመኞች ጉዳይ እየተጣራ ነው

ነብሩ፣ ሊቀመንበሩ እና አያ ጅቦ

አያ ጅቦ እና ቄሮ መስማማት ቀርቶ መግባባት አይችሉም፡፡ ዶ/ር አብይ ያደገው በአያ ጅቦ መንደር ነው፡፡ ነገር ግን፣ በቅርቡ በሁለቱ ባላንጣዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት አሳዳጊዎቹን ከድቶ ከነብሮች ጎን ቆመ፡፡ ነብሮችም ይህን ከግምት በማስገባት ከሰፈራቸው አልፎ የቀበሌው ሊቀመንበር ሆኖ እንዲመረጥ አስችለወታል፡፡ አሳዳጊዎቹ ጅቦች ግን ከድቷቸው ከቄሮዎች ጎን ስለቆመ፣ እንዲሁም ቀድሞ በቀበሌው ውስጥ የነበራቸውን የአድራጊ-ፈጣሪነት ስልጣን ስላሳጣቸው ሥር-የሰደደ … Continue reading ነብሩ፣ ሊቀመንበሩ እና አያ ጅቦ

“ምሁራን በሀገሪቱ እየተስፋፋ ስለመጣው ብሔርተኝነት ጥናት ሊያደርጉ ይገባል” ጠ/ሚ አብይ አህመድ

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን ጎሠኝነትና ብሔርተኝነት ከሃገራዊ ማንነት ጋር ማስታረቅ የሚቻልበትን የመፍትሄ ሐሳብ እንዲያፈላልጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለምሁራን ጥሪ አቀረቡ፡፡ የአገሪቱ ፖለቲካዊ ችግሮች የተወሳሰቡ በመሆናቸው ችግሮቹን አገናዝቦ መውጫ መንገድ የሚያሳይ ምሁር ያስፈልገናል፤ ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት የባሕር ዳር ቆይታቸው፤ በዐውደ ጥናት ላይ የነበሩ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራንን ያነጋገሩ ሲሆን፤ ምሁራኑ ለሀገሪቱ … Continue reading “ምሁራን በሀገሪቱ እየተስፋፋ ስለመጣው ብሔርተኝነት ጥናት ሊያደርጉ ይገባል” ጠ/ሚ አብይ አህመድ

ጦር፥ ግብር እና ምርጫ: “ከዶ/ር አብይ ምን ዓይነት ለውጥ ይጠብቃሉ?”

እርስዎ ምን ዓይነት ለውጥ እንዲያመጣ ይጠብቃሉ? ​ሰሞኑን አብዛኛው የጠየቀው ወይም የተጠየቀው ጥያቄ "ዶ/ር አብይ ለውጥ ያመጣል ብለህ ታስባለህ?" የሚለው ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን፣ "አንተ በራስህ ዶ/ር አብይ ምን ዓይነት ለውጥ እንዲያመጣ ትሻለህ?" ብላችሁ ብትጠይቁት አብዛኛው ጠያቂ ሆነ ተጠያቂ ግራ የሚጋባ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም አብዛኞቻችን "ለውጥ ያመጣል ወይስ አያመጣም?" ከማለት በዘለለ የምንፈልገውን ለውጥ በተጨባጭ የተገነዘብን አይመስኝም፡፡ በእርግጥ አሁን … Continue reading ጦር፥ ግብር እና ምርጫ: “ከዶ/ር አብይ ምን ዓይነት ለውጥ ይጠብቃሉ?”

ከሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ጋር ግልጽ ውይይትና ድርድር ሊደረግ ይገባል!

ዶ/ር አብይ የኦህዴድ ጽ/ቤት አላፊ በነበሩበት ወቅት ኦህዴድ ሁሉንም  ሰላም ወዳድ ዜጋን ያስደሰተ ጥሪ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ  ላሉ ተቃዋሚዎች አቅርቦ ነበር፡፡ ይህ ጥሪ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ  የቀረበ በመሆኑ አንዳንድ በኦሮሞ ስም የሚታገሉ በውጪም  በውስጥም ያሉ ተቃዋሚዎች በደስታ የተቀበሉት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ የኦህዴድ ጥሪ ምንም ያህል ለሀገሪቱ ሰላም  ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ቢሆንም ያለ … Continue reading ከሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ጋር ግልጽ ውይይትና ድርድር ሊደረግ ይገባል!