መንግስትን መተቸት የምሁራን መብት ሳይሆን “ግዴታ” ነው!

ዩጋንዳዊያን “የዝሆን ኩምቢ ያለ ቅጥ የረዘመው በትችት እጦት ነው” የሚል አባባል አላቸው። የተለያዩ ማህበራዊ፥ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ስር የሚሰዱት በትችት (Criticism) እጦት ምክንያት ነው። ችግሮችን ቀድሞ መለየትና በዚያ ላይ የሰላ ትችት መሰንዘር ጉዳዩ በሚመለከተው አካል ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝና የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ያስችላል። የሃሳብና አመለካከት ነፃነት በሌለበት ማህብረሰብ ዘንድ ችግሮችን በግልፅ የመተቸት ልማድ አይኖርም። በዚህ ምክንያት … Continue reading መንግስትን መተቸት የምሁራን መብት ሳይሆን “ግዴታ” ነው!

ከፖለቲካ ነፃ የሆነ ምሁር የለም!

እስር ቤት ሳለሁ ፖሊሶች በተደጋጋሚ ሲጠይቁኝ የነበረውና በቀጥታ ለመመለስ የተሳነኝ ጥያቄ እንዲህ ይላል፡- "ከሰለጠንክበት የመምህርነት ሙያ ውጪ የፖለቲካ ፅሁፎችን እንድትፅፍና እንድታሳትም ማን ፈቀደልህ?” ይህን ጥያቄ ለመመለስ ያደረኩት ጥረት ፍሬ-አልባ ነበር። ይህ እንደ በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 29 መሰረት ዴሞክራሲያዊ መብቴ፣ እንዲሁም በከፍተኛ ት/ት ተቋማት አዋጅ አንቀፅ 4(3) እና በአምቦ ዩኒቨርሲቲ መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 13(2) መሠረት ማህበራዊ ግዴታዬ … Continue reading ከፖለቲካ ነፃ የሆነ ምሁር የለም!