ሰው ወይም አውሬ፡ እስከ መቼ እንደ አውሬ እያደናችሁን፣ እንደ ሰው እየተሰቃየን እንኖራለን?

በመጀመሪያ ለዚህ ፅኁፍ መነሻ ከሆነኝ የሰቆቃ ታሪክ የተወሰነ ቀንጭቤ ላካፍላችሁ፡- “…ሴትነቴን ተመስርተው ጥቃት ፈፅመውብኛል፤ ሴት ሆኜ መፈጠሬን እንድጠላ የሚያደርጉ ተግባራትን ፈፅመውብኛል፣ እርቃኔን አቁመው ተሳልቀውብኛል፣ የእግር ጥፍሮቼን መርማርዎቼ ነቃቅለዋቸዋል። ጥፍሮቼን ከነቀሉ በኋላም ጥፍሮቼ የነበሩበትን ቦታ ቁስል እየነካኩ አሰቃይተውኛል፣…” በእርግጥ ይህ ነፍስህ ሲዖል ስትገባ የሚያጋጥማት ስቃይና መከራ አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ የኢህአዴግ መንግስትን በመቃወምህ ብቻ ተይዘህ መሃል አዲስ … Continue reading ሰው ወይም አውሬ፡ እስከ መቼ እንደ አውሬ እያደናችሁን፣ እንደ ሰው እየተሰቃየን እንኖራለን?

አመፅና ተቃውሞ በራሱ ልማትና ዴሞክራሲ ነው

ባሳለፍነው የ2008 ዓ፣ም የታየው ህዝባዊ ተቃውሞና አመፅ በአመቱ የመጨረሻ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ እንደነበር ይታወሳል። በአዲሱ አመትም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ግጭትና አለመረጋጋት እንደቀጠለ ነው። ነገር ግን፣ በ2008 ሐምሌና ነሃሴ ላይ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የነበረው አይነት እንቅስቃሴ አሁንም አለ ለማለት አያስደፍርም።  ይህን በማስመልከት አንዳንድ የገዢው ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ሀገሪቷን ሊበታትናት ተቃርቦ የነበረው የፖለቲካ … Continue reading አመፅና ተቃውሞ በራሱ ልማትና ዴሞክራሲ ነው

ኢህአዴግ ካልታደሰ አይወድቅም

አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች “ኢህአዴግ በቅርቡ ይወድቃል” ሲሉ፣ ደጋፊዎቹ ደግሞ “በቅርቡ ይታደሳል” እያሉ ይገኛል። ከመቼውም ግዜ በላይ በሀገሪቱ ፖለቲካ ለውጥ ስለማስፈለጉ ግን ሁለቱም ወገኖች አምነው የተቀበሉት ይመስላል። ይህ ለውጥ ደግሞ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ከኢህአዴግ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። የሀገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እንደ መንግስት በኢህአዴግ ላይ ውድቀት ወይም ተሃድሶ ሊያስከትል ይቻላል። ታዲያ እዚህ ጋር ቁልፉ ጥያቄ … Continue reading ኢህአዴግ ካልታደሰ አይወድቅም

ኢህአዴግ፡ ከለውጥ እና ከሞት አንዱን ምረጥ!

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህብረሰብ ሊሰጥ የታቀደው ስልጠና ዛሬ ላይ ተጀምሯል። ለስልጠናዉ ከተዘጋጁ ሰነዶች ውስጥ የመጀመሪያው “የሩብ ምዕተ ዓመታት የልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ጉዞ…” የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል። በመረሃ-ግብሩ መሰረት ጠዋት ላይ በአሰልጣኞቹ ገለፃ ሲሰጥ እንደተለመደው በአሰልጣኝነት የተመደቡት የመንግስት ኃላፊዎች ለታዳሚው የሚመጥን ስልጣና ለመስጠት የአቅምና ክህሎት ችግር እንዳለባቸው በግልፅ ያስታውቃል። ይህ ግን ላለፉት አስር አመታት የታዘብኩት … Continue reading ኢህአዴግ፡ ከለውጥ እና ከሞት አንዱን ምረጥ!

አመፅ የማን ልጅ ነው፡ የልማት ወይስ የአምባገነንነት?

በተለያዩ አከባቢዎች አመፅና ተቃውሞ ሲነሳ አንዳንድ የኢህአዴግ ባለስልጣናት የሀገሪቱ ልማት ያስከተለው ችግር እንደሆነ ሲናገሩ ይደመጣል። በእርግጥ የሀገር ልማት ለአመፅና አለመረጋጋት መንስዔ ሊሆን ይችላል? አመፅ የልማት ወይስ አምባገነንነት ተግባር ውጤት ነው? በዚህ ፅሁፍ እነዚህንና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን በዝርዝር እንመለከታለን። በቅድሚያ ልማት ምንድነው የሚለውን በአጭሩ መመልከት ያስፈልጋል። ልማትን “ሰላም፥ ጤና፥ ትምህርት እና መሰረተ-ልማት” በማለት በአጭሩ መግለፅ ይቻላል። … Continue reading አመፅ የማን ልጅ ነው፡ የልማት ወይስ የአምባገነንነት?

ግልፅ ደብዳቤ ለጠ/ሚ ኃ/ማሪያም፡ “በሕዝብ ላይ ጦርነት አውጀዋል”

ክቡር ጠ/ሚኒስተር ኃ/ማሪያም ሰላምና ጤና ከእርስዎ ጋር ይሁን። ስሜ ስዩም ተሾመ ይባላል። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የወሊሶ ካምፓስ መምህር ነኝ። በትርፍ ግዜዬ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የትንታኔ ፅሁፎችን እፅፋለሁ። በእርግጥ መፃፍ የጀመርኩት ከዘጠኝ ወር በፊት ሲሆን እኔ በምኖርበት ወሊሶ ከተማ የታየውን ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ በማስመልከት ነው። ከዚያ በኋላ ከ50 በላይ ፅሁፎችን በድረገፅ ላይ አውጥቼያለሁ። ከፅሁፎቼ ውስጥ “በቀውሱ የህዳሴን … Continue reading ግልፅ ደብዳቤ ለጠ/ሚ ኃ/ማሪያም፡ “በሕዝብ ላይ ጦርነት አውጀዋል”