ፕረዜዳንቱ ወደ ውጪ፣ ተማሪዎቹ ወደ ግቢ!!

የተማሪዎችን ጥያቄ ተቀብሎ ተገቢ ምላሽ መስጠት የዩኒቨርሲቲው ፕረዜዳንት ሥራና ሃላፊነት ነው፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መመሪያ በመምህራንና ተማሪዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ፣ ተግባራዊ እንዲደረግ አመራር መስጠት የፕረዜዳንቱ ድርሻና ሃላፊነት ነው፡፡ በዚህ መሠረት፣ በአንድ በኩል ተማሪዎቹ ስለ መመሪያው ዓላማና ግብ በማሳወቅ ማሳመን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጥያቄያቸውን ለትምህርት ሚኒስቴር በማቅረብ መመሪያው ያለበትን ክፍተት መጠቆምና የተሻለ የማሻሻያ ሃሳብ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡  … Continue reading ፕረዜዳንቱ ወደ ውጪ፣ ተማሪዎቹ ወደ ግቢ!!

​ትምህርት ሚኒስቴር መስማት ወይም መስራት አቁሟል! 

ባለፈው ሳምንት በዶችቬሌ ራዲዮ ላይ በፖለቲካ አለመረጋጋትና ትምህርት በሚል ርዕስ ዙሪያ በት/ት ሚኒስቴር የኮሚኑኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረግን ጨምሮ ከሌሎች ሁለት ተሳታፊዎች ጋር በስልክ ውይይት አድርገን ነበር። በውይይቱ ላይ በት/ት ተቋማት ውስጥ ለሚከሰቱ ግጭቶችና ተያያዥ ችግሮች በዋናነት ተጠያቂው የትምህርት ሚኒስቴር እንደሆነ ለመግለፅ ሞክሬያለሁ።  ለምሳሌ ባለፈው ሳምንት የፌደራል መንግስት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ኃላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት ባለፈው … Continue reading ​ትምህርት ሚኒስቴር መስማት ወይም መስራት አቁሟል! 

የዩኒቨርሲቲ ዕጩ ምሩቃን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሊወስዱ ነው

ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ በአገሪቱ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ለመመረቅ ዝግጁ የሆኑ ተማሪዎች፣ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሊወስዱ መሆኑ ታወቀ፡፡ ሰሞኑን በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፣ ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምረቃ ትምህርት መስኮች ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት የብቃት መለኪያ የሚሆነውን አጠቃላይ ምዘና ወስደው አጥጋቢና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ … Continue reading የዩኒቨርሲቲ ዕጩ ምሩቃን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሊወስዱ ነው

ሐኪም በአማርኛ ጠይቆ በእንግሊዘኛ መድሃኒት ካዘዘ እራሱ ጤነኛ አይደለም! የእኛ ተመራማሪዎችስ…?Part-III

"በሽተኛ ሐኪም እና ተመራማሪ” ሁለቱም አንድ ናቸው! በሚያግባባ ቋንቋ ጠይቀው በማያግባባ ቋንቋ የሚናገሩ! ነገር ግን፣ "በሽተኛው ሐኪም” ግለሰቡ ላይ ለፈፀመው ኢሰብዓዊ ድርጊት ተጠያቂ ሲሆን "በሽተኛው ተመራማሪ” ማህብረሰቡ ላይ ለሚፈፅመው ተመሣሣይ ተግባር ተጠያቂ አይሆንም። የድርግት ልዩነት በመኖሩ ሣይሆን ግለሰብ የመኖሪያ አድሯሻ አለው፤ የማህብረሰብ አድራሻ ሀገር ነው። ግለሰብ እራሱን ይወከላል ወይ ይወክላል… ማህብረሰብ ይወከ’ላል እንጂ አይ’ወክልም። ግለሰብ … Continue reading ሐኪም በአማርኛ ጠይቆ በእንግሊዘኛ መድሃኒት ካዘዘ እራሱ ጤነኛ አይደለም! የእኛ ተመራማሪዎችስ…?Part-III

ሐኪም በአማርኛ ጠይቆ በእንግሊዘኛ መድሃኒት ካዘዘ እራሱ ጤነኛ አይደለም! የእኛ ተመራማሪዎችስ….? Part-II

በከፍተኛ ት/ት ተቋማት የሚሰሩ ጥናታዊ ሥራዎች ችግር-ፈቺ፣ ተደራሽ እና ስርፀት በተጠቃሚው ዘንድ እንዳይሰርፁ በማድረግ ረገድ እጅግ በጣም ከፍተኛ ተፅዕኖ አለው። አንድ ሐኪም ለሕክምና የመጣውን ግለሰብ በሚገባው ቋንቋ ህመሙን፣ ስሜቱን እና ታሪኩን ጠይቆ፣ ታካሚው የነገረውንና ያለውን የሞያ ክህሎት ተጠቅሞ መድሃኒት ያዝለታል። ሆኖም ግን፣ የመድሃኒት ማዘዣውን እና አጠቃቀሙን ታካሚው በማይረዳው ቋንቋ ፅፎ ቢሰጠው ተግባሩ የሞያውን ሥነ-ምግባር የጣሰ … Continue reading ሐኪም በአማርኛ ጠይቆ በእንግሊዘኛ መድሃኒት ካዘዘ እራሱ ጤነኛ አይደለም! የእኛ ተመራማሪዎችስ….? Part-II

ሐኪም በአማርኛ ጠይቆ በእንግሊዘኛ መድሃኒት ካዘዘ እራሱ ጤነኛ አይደለም! የእኛ ተመራማሪዎችስ…? Part-I

ለመሆኑ፣ 'የጥናትና ምርምር ሥራዎች ስርፀት ለምን በሚፈለገውደረጃ ለውጥ እና መሻሻል አልመጣም?” ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት በሀገር ውስጥ የሚሰሩ ጥናታዊ ሥራዎች የጋራ መገለጫ የሆነን አንድ ነገር እንደመነሻ በመውሰድ ስለጉዳዩ ያለኝ ሃሣብ ለማብራራት እሞክራለሁ። በማህበራዊ ሣይንስ ዘርፍ የሚሰሩ ጥናቶች በሙሉ በ'አባሪነት’ የሚያይዙት 'የመጠይቅ ቅፅ’ አለ። ይህ ቅፅ፣ ጥናቱ በግብዓትነት የተጠቀመውን ሃሣብ፣ አስተያየት፣ መረጃ፣ አመለካከት፣…ወዘተ ለመሰብሰብ የዋለ ነው። … Continue reading ሐኪም በአማርኛ ጠይቆ በእንግሊዘኛ መድሃኒት ካዘዘ እራሱ ጤነኛ አይደለም! የእኛ ተመራማሪዎችስ…? Part-I

እሁን የእኛ ዩንቨርሲቲ መምህራን #የAnglo_Amharic_Remixን ቢተውት እና….

እሁን የእኛ ዩንቨርሲቲ መምህራን #የAnglo_Amharic_Remixን ቢተውት እና…. ***************************** በተማሪነት ከዛም በአስተማሪነት ሕይወት ውስጥ፣ #እንግሊዘኛ ቋንቋን በሙሉ ልብ የሚናገር አትዮጲያዊ አጋጥሞኝ አያቅም። መቀሌ እያለሁ ግን አንድ ተማሪ ልክ እንደ ተፈራ ገዳሙ (Meet ETV)፣ በእንግሊዘኛ ዘና ብሎ ሲያወራ አግኝቼ የሚከተለውን ተወያየን። መጀመሪያ "Hey! ...Your English is awesome!” ብዬ ተንተባተብኩ። "Oh..thanks m..a..n!” "I thought you’re from western England!..haha‘ … Continue reading እሁን የእኛ ዩንቨርሲቲ መምህራን #የAnglo_Amharic_Remixን ቢተውት እና….

ኢትዮጲያ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን EXPORT ታደርጋለች እንዴ?

ኢትዮጲያ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን EXPORT ታደርጋለች እንዴ? *************************** "የጥናት እና ምርምር ሥራዎች #ችግር_ፈቺ መሆን አለባቸው” አለን አየደል? መረጃውን ሕብረተሰቡ በሚናገረው ቋንቋ ለምሣሌ፡- በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሶማሊኛ፣ ትግርኛ፣….ወዘተ "መጠይቅ” አዘጋጅተን ለጥናቱ የሚያስፈልገውን መረጃ ሰበሰብን። እኔን ግራ ግብት ያለኝ፣ መረጃውን ("ችግሩን”) በሕብረተሰቡ ቋንቋ ሰብስበን፣ የጥናቱን ውጤት ("መፍትሄውን”) #በእንግሊዘኛ የምንፅፍለት "ም....ን ያድርግው" ብለን ነው? እንግሊዘኛ ቢረዳ ኖሮማ ችግሩንም በእንግሊዘኛ … Continue reading ኢትዮጲያ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን EXPORT ታደርጋለች እንዴ?