​የነዋሪዎች ጥያቄ፣ የሚድሮክ ብዝበዛ እና ኦህዴድ እርምጃ!

አውሮፓውያን ቀኝ ገዢዎች የአፍሪካን አንጡራ ሃብት በበዘቡበት አመታት ”ያልሰለጠነውን ሀገርና ህዝብ ማሰልጠን” በሚል ሽፍን የአፍሪካን ሀብት በመበዝበዝ የራሳቸው ነዋይ ማሳደግና አውሮፓን ማበልጸግ ችለው ነበር፡፡ በዚህ የቀጥታ የአውሮፓዊያን ቀኝ ግዛት ዘመን የአንጡራ ሀብቶቹ ባላቤት የሆኑት አፍሪካውያን እጅጉን አሳዛኝ በሆነ መልኩ ህይወታቸውንና አካላቸውን አጥተዋል፡፡ በተቃራኒው ግን አውሮፓ እጅጉን አድጋለች፡፡ ለዚህም ነው በአፍሪካና አፍሪካዊያን ስቃይ አውሮፓ አድጋለች የሚባለው፡፡ … Continue reading ​የነዋሪዎች ጥያቄ፣ የሚድሮክ ብዝበዛ እና ኦህዴድ እርምጃ!

ኦዶ ሻኪሶ: ወርቅ ‘መርዝ’ የሆነባት ምድር (BBC) 

ወ/ሮ ሑጤ ደንቆ የሁለት ልጆቻቸው ሞት እንዲሁም የሴት ልጃቸው አካል መጉደል ካደርሰባቸው የሐዘን ስብራት ጋር በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ዲባ በቴ ቀበሌ ውስጥ ይኖራሉ። እኚህ እናት የመጀመሪያ ልጃቸውን ሁለት እግሯን አልታዘዝ ከማለት በተጨማሪ በኋላ የወለዷቸው ወዲያውኑ እንደተወለዱ ሞተውባቸዋል። ወ/ሮ ሑጤ ነፍሰጡር በነበሩበት ወቅት ከባድ የጤና እክል አጋጥሟቸው የነበረ ቢሆንም አሁንም የአጥንት ሕመም ህይወታቸውን አቀበት … Continue reading ኦዶ ሻኪሶ: ወርቅ ‘መርዝ’ የሆነባት ምድር (BBC) 

ከሰው እና ከወርቅ የቱ ይበልጣል? 

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ለገ-ደንቢ (Lege Dembi) እና ሳካሮ (Sakaro) በሚባሉ አከባቢዎች ከሚገኙት የሜድሮክ (MIDROC) ወርቅ ማውጫዎች የሚወጣው መርዛማ የሆነ ኬሚካል በአከባቢው ነዋሪዎች፣ እንስሳት እና ስነ-ምህዳር ላይ የከፋ ጉዳት እያስከተለ ይገኛል፡፡ የአዶላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቡሻ ባላኮ ለOBN በሰጡት አስተያየት ከፋብሪካው የሚወጣው መርዛማ ኬሚካል በሰውና እንስሳት ፅንስና አወላለድ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል፡፡ ለምሳሌ ባሳለፍነው የፈረንጆች … Continue reading ከሰው እና ከወርቅ የቱ ይበልጣል?