መለስ Vs አብይ: አገር፥ የመሪ ስብዕና እና ተቋማት!

የግለሰብ ስብዕና በአገር እና በሕዝብ ላይ ያለውን ፋይዳ ለመታዘብ መለስ ዜናዊን እና ዶ/ር አብይ አህመድን ማሰብ በቂ ነው። በያሬድ ሃይለማሪያም ሰሞኑን በድህረ ገጾችና በየዜና ማሰራጫው አፍቃሪ መለሶች ግለሰቡ የሰራውንም ያልሰራውንም እያነሱ ሲያወድሱት ሳይ ይህ ሃሳብ ወደ አዕምሮዮ መጣ። የአንድ አገር ጥንካሬ፣ የወደፊት ተስፋ፣ አስተማማኝ የሆነ ሁለንተናዊ እድገት አቅጣጫ፣ ብልጽግና እና ሰላም የሚወሰነው አገሪቱ ባፈራቻቸው እና … Continue reading መለስ Vs አብይ: አገር፥ የመሪ ስብዕና እና ተቋማት!

IS ABYE AHMED A LIBERAL OR A PROGRESSIVE?

By Kebour Ghenna Let’s change a bit the ethnic discourse and ask who from Dr. Abye Ahmed or the late Meles Zenawi is considered a liberal or a progressive? For now, let’s define a ‘Liberal’ (in common speech) as a capitalist, who recognizes the flaws of capitalism and is dedicated to remedying them though taxation; … Continue reading IS ABYE AHMED A LIBERAL OR A PROGRESSIVE?

አምስት ጥያቄ አለኝ፦ ይድረስ ለቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ

መቼም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ ሰው “ጤናህ እንደምን አለህ? እንዴት ሰንብተሃል? ኑሮ እንዴት ይዞሃል?... ወዘተ የሚሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ አያስፈልግም። ለነገሩ እንዲህ ያሉ የሰላምታ ጥያቄዎች ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ዓይነት ጥያቄ መጠየቅ መጠየቅ ተገቢ አይመስለኝም። ሆኖም ግን፣ ከኢትዮጵያና ኤርትራ ጋር በተያያዘ የሚነሱቱን ጥያቄዎች ከእርስዎ በስተቀር በተገቢ ሁኔታ የሚመልስ ሰው እስካሁን አላገኘሁም። ምክንያቱም ጥያቄዎቹ በአብዛኛው ከእርስዎ የፖለቲካ አመለካከትና … Continue reading አምስት ጥያቄ አለኝ፦ ይድረስ ለቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ

የአልጄርስ ስምምነት ከመፈረሙ 4 ቀናት በፊት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል! (የሰነድ ማስረጃ)

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጄርስ ስምምነትን ለመቀበል መወሰኑን ተከትሎ ጉዳዩ አነጋጋሪ ሆኗል። በተለይ በአንዳንድ የትግራይ አከባቢዎች የአልጄርስ ስምምነት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል። ለዚህ ደግሞ በምክንያትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ፤ በተለይ ባድመ ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች መስዕዋት ሆነዋል፣ በአከባቢው የሚኖሩ የማህብረሰቦችን ለሁለት ይከፍላል፣ እንዲሁም የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሀገሪቱ መሬትና ሉዓላዊነት ላይ በተናጠል የመወሰን ስልጣን የለውም … Continue reading የአልጄርስ ስምምነት ከመፈረሙ 4 ቀናት በፊት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል! (የሰነድ ማስረጃ)

ምፅዋ፥ አሰብና ባድመ፤ የትግራይ መሪዎች የፈፀሟቸው ታሪካዊ ስህተቶች!

ከሁለት ቀን በፊት የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጄርስ ስምምነትን ለመቀበል ያሳለፈውን ውሳኔ አስመልክቶ የትግራይ ልሂቃን በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰጡትን ሃሳብና አስተያየት ስመለከት በጣም ግርም ብሎኛል። ከዓረና ትግራይ እስከ የህወሓት/ኢህአዴግ ደጋፊዎች፣ እንዲሁም “ገለልተኛ” ነን የሚሉት ልሂቃን በውሳኔው ዙሪያ ተመሳሳይ አቋም በማንፀባረቅ ላይ ናቸው። በአጠቃላይ አብዛኞቹ የትግራይ ልሂቃን የአልጄርስ ስምምነትን መቀበል “የኢትዮጲያን መሬትና ሉዓላዊነት አሳልፎ መስጠት” እንደሆነ ይገልፃሉ። … Continue reading ምፅዋ፥ አሰብና ባድመ፤ የትግራይ መሪዎች የፈፀሟቸው ታሪካዊ ስህተቶች!

​ኢትዮጲያዊነትን መገንባትና ማፍረስ: ከአፄ ሚኒሊክ እስከ መለስ! 

የኢህአዴግ መንግስት ትላንት ነሃሴ 26/2009 ዓ.ም “የፍቅር ቀን” ብሎ አስደመመን። በቀጣይ ቀናት ደግሞ “የአገር ፍቅር ቀን”፣ “የአንድነት ቀን” እና “የኢትዮጲያ ቀን”  እያለ ሊያስገርመን ተዘጋጅቷል። “የአንድነት ቀን” የሚከበርበት መሪ ቃል “ኢትዮጵያዊ ኩራቱ ህብረ-ብሄራዊነቱ” የሚል ነው። “የሀገር ፍቅር ቀን” መሪ ቃል “እጃችን እስኪሻክር እንሰራለን ምክነያቱም ኢትዮጵያን እንወዳታለን” የሚል ሲሆን “የኢትዮጲያ ቀን” ደግሞ “እኛ ኢትዮጵያውያን የጥቁር ህዝቦች ተምሳሌት … Continue reading ​ኢትዮጲያዊነትን መገንባትና ማፍረስ: ከአፄ ሚኒሊክ እስከ መለስ! 

ወይኔ…ስድብ አማረኝ! ኢህአዴግን መስደብ አማረኝ!

እናንተ! ዛሬ በጣም ስድብ አምሮኛል። መሰደብ ለምጄዋለሁ። እኔያማረኝ መሳደብ ነው። ይሄው ከነጋ ጀምሮ፤ ስድብ…ስድብ፣ ስደብ…ስደብ ይለኛል፣ ያለ ወትሮዬ መሳደብ፥ መስደብ አምሮኛል። ችግሩ ማንን ልስደብ? “ራስህን ሰደብ” እንዳትሉኝ። ራሴን ሁሌ እንደሰደብኩት ነው። በሰራሁት ስራ አንድም ቀን ረክቼ አላውቅም። ስለዚህ፣ ሁልቀን ራሴን እንደወቀስኩ፥ እንደሰደብኩ ነው። ዛሬ ግን ያማረኝ ሌላን ሰው መስደብ ነው። እ…እ… የቀድሞ ጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ … Continue reading ወይኔ…ስድብ አማረኝ! ኢህአዴግን መስደብ አማረኝ!

ክቡር ጠ/ሚኒስትር: “የእርስዎ ከሥልጣን መውረድ ለኢትዮጲያ ትልቅ ውለታ ነው!

ባለፈው ባወጣነው ፅሁፍ የፖለቲካ አመራር ብቃት የሌላቸው መሪዎች ለሀገር ሰላም፥ ልማትና ዴሞክራሲ “እንቅፋት” እንደሚሆኑ በዝርዝር ተመልክተናል። በመጨረሻም፣ በሀገራችን ወቅታዊ ፖለቲካ ላይ በግልፅ የሚስተዋለው ችግር የመልካም አስተዳደር ወይም የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር ሳይሆን የፖለቲካ አመራር ብቃት ማነስ እንደሆነ በፅሁፉ ተጠቁሟል። ከዚህ አንፃር፣ “የኢህአዴግ መንግስት የፖለቲካ አመራር ብቃት እንዴት ይታያል?” የሚለውን በዚህ ፅሁፍ በዝርዝር እንመለከታለን። በእርግጥ በሀገራችን ፖለቲካዊ … Continue reading ክቡር ጠ/ሚኒስትር: “የእርስዎ ከሥልጣን መውረድ ለኢትዮጲያ ትልቅ ውለታ ነው!

ለተከሰተው አመፅና አለመረጋጋት ዋናው ተጠያቂ አንድ ሰው ነው

ካለፈው ዓመት ጀምሮ በሀገራችን የታየውን አመፅና አለመረጋጋት በማነሳሳት ረገድ ተጠያቂ ናቸው የሚባሉት አካላት ብዙ ናቸው። ግብፅና ኤርትራ፣ ኦነግና ግንቦት7፣ የኒዮሊብራል አራማጆች እና የቀለም-አብዮት አቀንቃኞች፣…ወዘተ። ከእነዚህ ውስጥ እኔ በየትኛው እንደምመደብ ባላውቅም “ሕዝብን ለአመፅ በማነሳሳት” በሚል ወንጀል ተከስሼ ለ82 ቀናት ያህል በእስር ቤት እና በተሃድሶ ስልጠና ላይ ቆይቼያለሁ። በጦላይ በተሰጠኝ የተሃድሶ ስልጠና መሰረት አንድ የተገነዘብኩት ነገር ቢኖር … Continue reading ለተከሰተው አመፅና አለመረጋጋት ዋናው ተጠያቂ አንድ ሰው ነው

ልማትና ዴሞክራሲ፡ የመለስ ዜናዊ ፍልስፍና- ክፍል-1

አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ “ዴሞክራሲ ቅንጦት ነው” በማለት ለቢቢሲ ሬድዮ በሰጠው አስተያየት ዙሪያ ሁለት ተከታታይ ፅሁፎችን፤ በመጀመሪያ ኃይሌ አስተያየቱን በሰጠበት አግባብ ዙሪያ፣ በመቀጠል ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ስለሆነው ነፃነትና ከሰው-ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ጋር ስላለው ቁርኝት በዚሁ ድረገፅ ላይ አውጥቼ ነበር፡፡ በእርግጥ በአስተያየቱ መሰጠቱ፣ ወይም ደግሞ በማህበራዊ ድረገፆች መነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ ለእኔ ይኽን ያህል አሳሳቢ አይደለም፡፡ ከዚያ ይልቅ፣ አሁን … Continue reading ልማትና ዴሞክራሲ፡ የመለስ ዜናዊ ፍልስፍና- ክፍል-1