ደሃን በማጥፋት ድህነትን መዋጋት አይቻልም!

በያሬድ ሃይለማሪያም (የሰብዓዊ መብት ተሟጋች) የአዲስ አበባ መስተዳደር የከተማዋን ገጽታ የሚያበላሹ በሚል የፈረጃቸውን የእኔ ቢጤዎች እና ሴተኛ አዳሪዎችን ከከተማዋ ጎዳናዎች ላይ ለማወገድ የሚያስችል እርምጃ ለመውሰድ ሽር ጉድ እያለ መሆኑን እና ሕግ ያረቀቀ መሆኑን በቅርቡ ገልጿል። ህብር ሬዲዮ እንደገለጸው በመስተዳድሩ የከንቲባው ጽ/ቤት የፕሬስ ጉዳይ ሹም ከፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (ኤኤፍ ፒ) ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "የአገሪቱን እና … Continue reading ደሃን በማጥፋት ድህነትን መዋጋት አይቻልም!

የአብዛኛው ኢትዮጲያዊ ሕይወት የሚሰማው ድምፅ የማቃት ስርቅርቅታ እንጂ የመቻል ፉከራ አይደለም!!

‘…መጀመሪያ አለማችን ተፈጠረች። ሕይወትን ያለውን ሕይወት በሌለው ጉያዋ ቀላቀለች። በዚያውም ተፈታኟን ኮለኮለች። ከእንስሳት መሀል ልብ ብሎ ሊያያት የቻለው እንስሳ እራሱን ‘ሰው” ብሎ ጠራው። እኛም ኢትዮጲያዊያን ነበርንበት።…ስልጣኔ የሚሉት ነገር እየተክተፈተፈ ተከትሏል። እኛም ኢትዮጲያዊያን ነበርንበት። ሁሉም በየአገሩ ከተፈጥሮ ጋር ግብግቡን አጧጧፈ። እኛ ኢትዮጲያዊያን ግን የነበርንበት መሆኑን እንጃ። ‘ስልጣኔን መጀመራችንን እንጂ ግብግቡ ስለመቀጠሉ መረጃው አይታይም። በአብዛኛው የሚታየው ያልተቋረጠው … Continue reading የአብዛኛው ኢትዮጲያዊ ሕይወት የሚሰማው ድምፅ የማቃት ስርቅርቅታ እንጂ የመቻል ፉከራ አይደለም!!

“ደሃ” ገነት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ይሻላል!!!

በሰው ልጅ የሚደርስ እጅግ በጣም መጥፎ ክፋት; በጣም ከፍተኛው ወንጀል ድህነት ነው:: ከድህነት መሸሸጊያ ጥጋት የሌለው ሰው ነፃነት የለውም:: ነፃነትን አያቅም, አይጠይቅም, አይሰጥም!! እንዲህ ድህነት የደለበበት ሕይወት ውጤት #ጥገኝነት ነው:: ጥገኛ ሰው የሃሣብና የአስተሳሰብ ነፃነት የለውም:: የግል እሴት የለውም:: ከማጣት ጩኸት የፀዳ የሕይወት ሐሴት አይኖረውም:: በአጠቃላይ ደሃ...ጥገኛ ሰው...የራሱ ሕይወት የለውም:: ግዑዝ ነው:: በሰማይ ቤት ደግሞ … Continue reading “ደሃ” ገነት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ይሻላል!!!