የሰሞኑ የግብር ጭማሪ እና የፀረ-ሽብር ሕጉ የአንድ ሣንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው!

እንደሚታወቀው ሰሞኑን ከግብር ተመን ጭማሪ ጋር ተያይዞ በተለያዩ አከባቢዎች ተቃውሞና አድማ እየተካሄደ ይገኛል። በእርግጥ አብዛኞቹ የሀገራችን የፖለቲካ ልሂቃን የተቃውሞው መንስዔ ከፍተኛ የግብር ጭማሪና መፍትሄውም የተመን ቅናሽ ይመስላቸዋል። ነገር ግን፣ የግብር አወሳሰኑ እና የሕዝቡ ብሶትና አቤቱታ የሚያሳየው ሌላ ነገር ነው። የግብር ጭማሪ የተወሰነበት አግባብ የፀረ-ሽብር ሕጉ ከፀደቀበት ጋር ፍፁም ተመሳሳይ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ይህና ሌሎች … Continue reading የሰሞኑ የግብር ጭማሪ እና የፀረ-ሽብር ሕጉ የአንድ ሣንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው!

ወሊሶ: የግብር ጭማሪ ያስነሳው አድማ ለ2ኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል!

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ ከግብር ጭማሪ ጋር በተያያዘ የተነሳው አድማ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ዉሏል። በከተማ ውስጥ ሆቴሎች እና የንግድ ቤቶች ተዘግተዋል። የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የለም። የወሊሶ ከተማ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ በእግር ነው የሚንቀሳቀሱት። ከትላንትነው በተለየ በዋናው አስፋልት ላይ በሚያልፉ መኪኖች ላይ ጥቃት እየተፈፀመ አይደለም። ቁጥራቸው ከወትሮው ያነሰ ቢሆንም የሕዝብና የጭነት ተሸከርካሪዎች ከአዲስ … Continue reading ወሊሶ: የግብር ጭማሪ ያስነሳው አድማ ለ2ኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል!

ኢህአዴግ “ሕዝብን ለአመፅ በማነሳሳት” በሚለው ይከሰስልን!

ትላንት ማታ ሰፈር ካለች አንዲት ግሮሰሪ ቁጭ ብዬ ሞባይሌን እየጎረጎርኩ ሳለ ባለቤቷ መጥታ “ስዬ ዛሬ በግዜ ግባ” አለችኝ። እኔም ነገሩ ገርሞኝ “ምነው? ምን ችግር ተፈጠረ?” አልኳት። “አይ..ነገ ለተቃውሞ እየተዘጋጁ ስለሆነ ማምሸቱ ለአንተ ጥሩ አይደለም” ብላኝ ዕቃዎቿን ማስገባት ጀመረች። ላለፉት ዘጠኝ ወራት በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ተጠፍሮ የከረመ ማህብረሰብ በአስረኛው ወር ላይ ለአመፅና ተቃውሞ አደባባይ ይወጣል ብዬ … Continue reading ኢህአዴግ “ሕዝብን ለአመፅ በማነሳሳት” በሚለው ይከሰስልን!